የህወሓት ጁንታ በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም የማይችል ግፍ ፈጽሞብናል – የሰሜን ዕዝ አባላት

“ጽንፈኛው የህውሓት ጁንታ በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም የማይችል ግፍ ፈጽሞብናል” ሲሉ በህክምና ላይ የሚገኙ የሰሜን ዕዝ አባላት ተናገሩ። ምክትል መቶ አለቃ ዳዊት ደርቤ “በወገን ጥቃት ይደርስብናል ብለን ባለሰብንበት ወቅት በሌሊት በመጥረቢያ እጄ ተቆረጠ” ይላል። “ሞቷል ብለው ትተውኝ ስለሄዱ ተረፍኩ፤ ሌሎች የሰራዊቱ አባላት ግን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ” ሲል ይገልጻል።

“ጁንታው በሰራዊቱ ላይ የፈጸመው ግፍ በጽኑ መወገዝ ያለበት ድርጊት ነው” የሚለው ተጎጂው፤ “በወገን ላይ ቀርቶ በጠላት ላይ ሊፈጸም የማይገባ ግፍ ነው” ብሏል። ሌላው የሰራዊቱ አባል ሻለቃ ባሊና ሰሚ ተመሳሳይ ጥቃት እንደደረሰበት ይናገራል። “ሰራዊቱ የክልሉን ህዝብ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ሲያግዝ ቆይቶ ቢሆንም ለውለታው የተከፈለው አሰቃቂና አሳዛኝ ግፍ ነው” ብለዋል።

ቡድኑ በሰራዊቱ አባላት ላይ ከፈጸመው በደል በተጨማሪ በሰሜን ዕዝ ውስጥ የሚገኘው የመቀሌ መከላከያ ሶስተኛ ደረጃ ሆስፒታልን ጨምሮ የሰራዊቱ የተለያዩ ንብረቶችን እንዳወደመ ጠቁመዋል።

ሆስፒታሉ ጉዳት ሳይደርስበት በፊት ለሰራዊቱ፣ ለሰራዊቱ ቤተሰቦችና እና ለአካባቢው ነዋሪዎች እስከ ቀዶ ህክምና ድረስ አገልግሎት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ “ጁንታው ሆስፒታሉን ሙሉ በሙሉ በመዝረፍና በማውደም ለህዝብ ያለውን ንቀት በተግባር አሳይቷል” ብለዋል።

ሻለቃ ዶክተር ከበደ አደለ

በመቀሌ የመከላከያ ሶስተኛ ደረጃ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሻለቃ ዶክተር ከበደ አደለ የሆስፒታሉ ንብረት ሙሉ በሙሉ በጁንታው መውደሙን አረጋግጠዋል። “ሆስፒታሉ 160 አልጋዎች ያሉት ሲሆን ከመከላከያ ሰራዊት በተጨማሪ ለዜጎች አገልግሎት እየሰጠ ነበር” ያሉት ሜዲካል ዳይሬክተሩ፤ መንግስት አስፈላጊውን ቁሳቁስ በማሟላት ሆስፒታሉን ወደ ስራ መመለሱን ገልጸዋል።  (ኢዜአ)

Related posts:

መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”
በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አማራ ክልል ትህነግ ዳግም ጦርነት ስላወጀ የ"ዝግጁነትን" አዋጅ አወጣ
ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

1 thought on “የህወሓት ጁንታ በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም የማይችል ግፍ ፈጽሞብናል – የሰሜን ዕዝ አባላት

  1. ህወሀት ሆስፒታል አወደመ?
    ህወሀት የትግራይን ክልል ህዝብን በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ህይወት ያገዘ የወገኑን ሰው እጅ በመጥረቢያ ቆርጦ እና ሌሎችን በተመሳሳይ መልክ በክልሉ በማገዝ ይኖሩ የነበሩትን የኢትዮጵያ መከላከያ አባላትን ንብረት እያወደመ በአሰቃቂ መልክ ገደለ?

    ይህ አሰቃቂ ድርጊት እንኳን ከህወሀት ቀርቶ ከማንም አረመኔ ጠላት አይጠበቅም።

Leave a Reply