አምባሳደር ኢቨግኒ በሩሲያና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ማሳደግ እንደሚገባ ተናገሩ፤ አቶ ደመቀ አመሰገኑ

NEWS

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቨግኒ ታሪኪንን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት አምባሳደሩ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ማደግ እንዳለበትና አገራቸው ከፍተና ፍላጎት እንዳላት ማስታወቃቸው ተገለጸ።

አቶ ደመቀ ሩሲያ መርህ ላይ ተመስርታ ከኢትዮጵያ ጎን በመቆሟ ከፍ ያለ ምስጋና ማቅረባቸውን የዘገበው ፋና ነው። ፋና በዘገባው አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ከሩስያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸውን በማስታወስ በቅርቡም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታ ጥበቃው ምክርቤት ሰብሰባ ላይ ሩስያ  ለወሰደችው መርህን መሰረት ያደረገ አቋም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሚኒስተሩ በትግራይ ክልል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ ለአምባሳደሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመንግስት በኩል የሰብኣዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶችና የሚዲያ ተቋማት በክልሉ ተገኝተው ስራቸውን እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታዎች የተፈጠሩ መሆኑን ገልፀው የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም ለማጣራት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም በመሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ያላገናዘቡ ወቀሳዎች መቀጠላቸውን አስረድተዋዋል።

በቅርቡ በተካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ጸጥታው ምክር ቤት ሰብሰባ ላይ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን ለአምባሳደሩ ገልጸዋል። በዚህም በትግራይ ክልል የሚነሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የአፍሪካ ህብረት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በጋራ ምርመራዎችን እንዲያካሂድ መንግስት ያለውን ፍላጎት መገለጹን አንስተዋል።

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ምርመራ ለማድረግ በመንግስት በኩል ያለውን ዝግጁነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸውን አቶ ደመቀ አብራርተዋል። አምባሳደር ኢቨግኒ ታሪኪንን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

የተፈረሙ ስምምነቶችን ወደ ስራ በማስገባት እንዲሁም በሂደት ያሉ ስምምነቶች እንዲፈረሙ በማድረግ በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በውይይቱ መግባባት ላይ ተደርሷል ተብሏል። አቶ ደመቀ በኢትዮጵያ እና ሩስያ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት አውስተው፤ በቀጣይም ሁለቱ ሀገራት በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

Related posts:

"መከላከያ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በሚችልበት አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል" አብይ አህመድ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Leave a Reply