የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 137.35 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ሰጠ

ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 137.35 ሚሊዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት መስማማቱንና ይህንኑ ስምምነት በፊርማ ማረጋገጡን መንግስት ኣስታወቀ። ርዳታው ለትምህርትና ኮቪድ 19 ላስከተለው ችግር የሚውል አንደሆነ ታውቁል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሪት ያስሂን ወሀብራቢና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬከተር ኦስማን ዲዮን ተፈራርመውታል። ስምምነቱ ዓለም አቀፍ አጋርነት ለትምህርት በተሰኘው ማእቀፍ አማካኝነት የተደረገ ነው፡፡

ከዚህ ውስጥ 14 ነጥብ 85 ሚሊየን ዶላሩ በዓለም አቀፍ አጋርነት ኮቪድ19 በትምህርቱ ዘርፍ ላስከተለው ተፅዕኖ ምላሽ ለመስጠት የሚውል ነው ተብሏል፡፡ በዚህም በቫይረሱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት እንደገና ማስቀጠልና በቀጣይም ከቫይረሱ ለማገገም የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ቫይረሱን ለማቆጣጠር የሚሰሩ ተግባራትን ለማገዝ የሚውል ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም ቀሪው 122 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላሩ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝና ለመደገፍ የሚውል መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ via FBC

See also  "አብይን አስወግደው አለኝ" - በቁጭት እየወጡ ያሉ ሚስጢሮች

Leave a Reply