ትህነግን በጉያቸው ይዘው በመንግስት ስም የዲፕሎማሲ ትንቅንቅ እንደሚያደርጉ ሲናገሩ የነበሩት ዲፕሎማት አገር መክዳታቸውን በገሃድ እስከተናገሩበት ቀን ድረስ ለትህነግ ይሰሩ እንደነበር የአሜሪካ ዲፕሎማት ለኢትዮ 12 የአሜሪካ ተባባሪ ጠቆሙ። የሰውየው ሹመት መንግስት ራሱን በራሱ ሲያርድ እንደነበር ማሳያ ነው ተብሏል።

የቀድሞ የወይዘሮ አዜብ ባለቤት የነበሩት አቶ ብርሃነ ኪዳና ማሪያም ከትህነግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው የተባረሩት በሜይ 2016 ነበር። የቀድሞ ባለቤታቸው ስብሰባ ረግጠው ክትህነግ ስራ አስፈጻሚነት ስልጣንና ከኤፈርት ስራ አስኪያጅነታቸው ሲባረሩ ቆንስላ የሆኑት አቶ ብርሃነ በመቸረሻ አካባቢ ከአቶ ስብሃት ጋር ከመጋጨታቸው ውጪ የትህነግ ታማኝ አገልጋይ እንደነበሩ በቅርብ የሚያውቋቸው ይነገራሉ። ሃብታም መሆናቸውንም ያውቃሉ።

አቶ ብርሃነ “በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት ጦርነት እና መንግሥት በሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚያደርሰውን ጭቆናና ውድመት ተቃውሜ ነው” ሲሉ አገር መክዳታቸው ይፋ ሲያደርጉ በተመሳሳይ ሰዓት ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ሊያወገዙ አደባባይ ወጥተው ነበር።

Related stories   UNDP Memo Echoes Ethiopian Talking Points on Tigray

በአሜሪካን የሰልፍ ታሪክ እጅግ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ትህነግ በሃሰት መረጃ የሚከፈላቸውን ዲፕሎማቶችና ሚዲያዎች በመጠቀም ዓለምን እያሳተ እንደሆን በአንድነት በሚያስተጋቡበት ወቅት ዜናውን ለማስቀየር የተመረጠ ጊዜ ጥብቀው አገር መክዳታቸውን ይፋ እንዳደረጉ ነው ዲፕሎማቱ የገለጹት።

በኤምባሲ ደረጃ ባሉ ግንኙነቶች ለተሳሳቱ መረጃዎች ኢትዮጵያን ወክለው እንደ እውነት በመቀበል ስማቸው እንዳይጠቀስ እየጠየቁ መረጃ ይሰጡ እንደነበር ዲፕሎማቱ አመልክተዋል።

አሜሪካ ካሉ የትህነግ ነባር አባላት ጋር ግንኙነት የሚያደርጉት አቶ ብረሃነ አገር መክዳታቸውን ይፋ እስካደረጉበት ሰዓት ድረስ በተሰጣቸው ሃላፊነት አማካይነት ከዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች፣ እንዲሁም አገሮች ጋር ትህነግ ለከፈተው የቅጥፈት ዘመቻ ደጋፊ ስራ ሲሰሩ እንደነበር መንግስት በማወቁ ከሳምንት በፊት ታግደው እንደነበር ምንጩ አመልክተዋል።

Related stories   

የትህነግ ታሳሪዎች – ከበረሃ ከተማረኩ ጀምሮ ሰብአዊ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑንን፣ ሲያዙ ተኩስና ማስፈራራት እንደነበር ገለጹ

እግዱ ጸንቶ ደብዳቤ ሳይደርሳቸው አስቀድመው በግጥምጥሞሽ በተመረጠ ቀን የክህደት ደብዳቤ በማሰራጨት ወደ ድርጅታቸው ዓላማ አስፈጻሚነት መዛወራቸውን ይፋ ያደረጉት አቶ ብርሃነ ከዚህ ቀደም ሲያገለግሉ ከነበሩባቸው ቁልፍ የሚዲያና የንግድ ሞኖፖሊ ተቋም አሃአልፊነታቸው አንጻር በኢትዮጵያ መለያ ለትህነግ ሲጫወቱ መቆየታቸው አስገራሚ እንዳልሆነ ዜናውን የሰሙ ገልጸዋል። እነደውም ዜናው መንግስት እሳቸውን በዚህ ከፈተኛ ቦታ ላይ አስቀምጦ ራሱን ሲያርድ መቆየቱ እንደሆነም ተመክቷል።

አቶ ብርሃነ ኪዳነ ማርያም የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ሃላፊ ነበሩ፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል። ከአቶ አሰፋ ማሞ ሞት በሁዋላ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን መርተዋል። የትህነግን ታላቅ የንግድ ተቋም ኤፈርትን ከቀድሞ ሚስታቸው ወ/ሮ አዜብ ስር ሆነው በስራ አስኪያጅነት አስተዳድረዋል።

ኪዳነ ማርያም ማህረት በሚል ስያሜ የሚታወቁት እኚህ ሰው ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ስራ አስፈጻሚነት ሲበረሩ በሎሳንጅለስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሆነው ተመድበዋል። ወዲያው ለውጡ ተጣድፎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ መሪነት እንደመጡ አቶ ካሳ ከዋሽንግቶን ኤምባሲ ሲለቁ ቆንስላነቱንና አምባሳደርነቱን ደርበው ሰርተዋል። አቶ ፍጹም በኦፊሳል የሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲሾሙ እሳቸው ምክትል አምባሳደር ሆነው በቋሚነት ተመደቡ።

\Related stories   ዓለም ባንክ ተከተለ – ግብጽ ሚስጥሩን ይፋ አደረገች

በሌላ ቋንቋ አቶ ኪዳነ ማርያም የኤምዳሲው አንደኛ ጸሃፊና የፖለቲካ ጉዳዮችን የሚከታተሉ ባለስልጣን ነበሩ። የኢትዮ 12 የቅርብ መረጃ እንዳሉት በትህነግና በመንግስት መካከል ያለውን የዲፕሎማሲ ውዝግብ መንግስት ሆነው በዋናነት የሚከታተሉት እሳቸው ነበሩ። በትህነግ

Leave a Reply