በሃላይደጌ አሰቦት እጩ ብሄራዊ ፓርክ በተከሰተ የእሳት አደጋ እስካሁን ከ100 ኪሎ ሜትር ስኩየር የሚገመት ሳርና ቁጥቋጦ

በሃላይደጌ አሰቦት እጩ ብሄራዊ ፓርክ በተከሰተ የእሳት አደጋ እስካሁን ከ100 ኪሎ ሜትር ስኩየር በላይ የሚገመት ሳርና ቁጥቋጦ መውደሙን የፓርኩ አስተባባሪ አስታወቁ።

ባለፈው ሀሙስ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ቀትር ላይ በፓርኩ ሰሜናዊ ክፍል የተከሰተውን የእሳት አደጋ በአብዛኛው መቆጣጠር እንደተቻለ የፓርኩ አስተባባሪ አቶ መሐመድ እድሪስ ለኢዜአ ተናግረዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር ባለፉት ሶስት ቀናት ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር የአፋር ክልል እሳት አደጋ መከላከያ ቡድን፣ የክልሉ የልማት ድርጅቶች፣ የአሚባራና ሃሩካ ወረዳ አመራሮችና ነዋሪዎች እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከፍተኛ ተሳትፎና ጥረት ማድረጋቸውን አመልክተዋል።

“ይሁንና በአካባቢው ባለው ከፍተኛ ንፋስና ሙቀት ቃጠሎውን ፈጥኖ ለመቆጣጠር አላስቻለም” ሲሉ የቁጥጥር ጥረቱ ፈታኝ እንደነበር አስረድተዋል።

እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በነበረባቸው አካባቢዎች እሳቱን ለማጥፋት በተደረገ ጥረት አብዛኛውን ክፍል መቆጣጠር እንደተቻለ አስታውቀዋል።

ዛሬም በፓርኩ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተበታትነው የሚገኙ አነስተኛና ቀላል እሳቶችን የማጥፋት ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው፤ አደጋው በቁጥጥር ስር የሚውልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸዋል።

ለሶስት ቀን በዘለቀው ቃጠሎ ከ100 ኪሎ ሜትር እስኩየር በላይ የሸፈነ ሳርና ቁጥቋጦ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አመልክተው፤ በቃጠሎው በዱር እንስሳትና አእዋፎች ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁመዋል።

የእሳት አደጋው መንሰኤ ሰው ሰራሽ መሆኑን ያመለከቱት አስተባባሪው፤ ዝርዝር የአደጋው መንስኤና የጉዳት መጠን በሚመለከታቸው አካላት ተመርመሮ የሚገለጽ መሆኑን አመላክተዋል።

ከ1965 ዓ.ም ጀምሮ በጥብቅ የዱር እንስሳት ክልልነት ተዋቅሮ በ2006 ዓ.ም ወደ እጩ ብሄራዊ ፓርክነት ያደገው ሃላይደጌ አሰቦት ፓርክ በአፋር ክልል ገቢ-ረሱና በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ሃረርጌ ዞኖች ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ፓርኩ ትልቁ የሜዳ አህያ፣ የሜዳ ፍየልና ሳላ ጨምሮ የዱር እንስሳትና አእዋፍ መጠለያ መሆኑን አቶ መሐመድ አስታውቀዋል።

Related posts:

መንግስት የኑሮ ወድነትን ለማሻሻልና የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ተከታታይ እርምጃ አንደሚወስድ ተገለጸ
ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት መኖር እና የሚያስከትለው ውጤት
በመኪና አደጋ አራት የጤና ባለሙያዎችን ህይወት አለፈ
የሞት ቅጣት የሚያሰጋቸው ጀማል እና ሀሰን
"ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት ●●●
የአቅመ ደካሞችን ጣሪያ መድፈንም ያስወግዛል?
በኦሮሚያ ቦረና ዞን - ገበሬዎች ራሳቸው ሞፈር እየጎተቱ እያረሱ ነው
ከደሴ ከተማ ቤተ-እምነቶች እና ህዝባዊ ተቋማት ህብረት የተሰጠ መግለጫ
«በትግራይ መንግሥት እርዳታ በትክክል ለተጠቃሚዎች እንደሚደርስ ይቆጣጠራል»
የአስር ዓመት ልጅን በሽተኛ በማስመሰል በሶስት ሚኒባስ ተደራጅተው ሲለምኑ የነበሩ ተያዙ
ከ33 ሺህ በላይ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
“ምግቤን ከጓሮዬ”
“ባለፉት 6 ወራት ብቻ 231 ሀሰተኛ የሰነድ ማስረጃዎች ተይዘዋል”
የረሀብ ተጋላጭነቷን ለመቀነስ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር ገለጸ
ሥርዐት አልባው ንግድ እና ስጋት የፈጠረው የኑሮ ውድነት!

Leave a Reply