ለኤርሚያስ ለገሰ ቅጥፈት የተሰጠ መልስ! « የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም»

[ እዮብ መሳፍንት ]

የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርሚያስ ለገሰ ሆን ብሎ በቁጥር ሊጫወት ሞክሯል፡፡ አላማው ኢዜማ የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደማይችል አስመስሎ መሳል ነው፡፡ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ሆኖበት ነው፡፡

የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም፡፡ ምናልባት እንዲገባው ከዚህ በፊት ከነበረው የተቃዋሚዎች ዕጩዎች ቁጥር በ11% እድገት አሳይተናል እንበለው ይሆን?? ምንም እንኳን [ለእንደዚ አይነቱ አውቆ አበድ መፍትሄው] ንቆ መተው ቢሆንም ያቀረበውን የተንኮል መረጃ እንደ እውነት ሊወስዱ የሚችሉ ቅኖችን ከስህተት ለማዳን ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡

ምርጫ የሚደረገው በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ፦

#በአዲስ_አበባ – ለክልልም ሆነ ለተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ ዕጩዎችን ያስመዘገበው ብቸኛው ፓርቲ ኢዜማ ብቻ ነው፡፡ (ከአብን እና ከመኢአድ ጋር በጋር ዕጩዎችን አቅርቦ በስሙ የሚወዳደሩት ባልደራስም ሆነ ገዢው ፓርቲ ሙሉ ዕጩዎችን አላቀረቡም!)
#በደቡብ_ክልል – በፌደራልም ሆነ በክልል ምክር ቤት በሁሉም ወንበሮች እንወዳደራለን።
#በአማራ_ክልል – በፌደራልም ሆነ በክልል ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ እንወዳደራለን።
#ጋምቤላ – ያለው የክልል ም/ቤት ወንበር 155 ነው በ114 የክልል ም/ቤት ተወዳዳሪ አቅርበናል የተቀሩት 41 ላይ በምዝገባ ችግር ስለተፈጠረብን ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርበናል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ እንወዳደራለን።
#ሀረሪ – 36 ወንበር ነው ያለው – በአንደኛው ምርጫ ክልል ሙሉ 18 ዕጩዎች ያቀረብን ሲሆን በሌላኛው ምርጫ ክልል ለአደሬ ብሄረሰብ ብቻ የተተወውን 9 ወንበር ጨምረን ዕጩ አቅርበናል የጎደለን 4 የክልል ምክር ቤት ዕጩ ብቻ ነው፡፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ለአደሬ ብሔረሰብ የተተወውን ወንበር ጭምር ዕጩ አቅርበንበታል፡፡
#ሲዳማ – ካሉት 19 ወረዳዎች በ16ቱ አብላጫውን ዕጩዎች አቅርበናል በተቀሩት በ3ቱም ዕጩ ብናዘጋጅም በምርጫ ቦርድ ምክኒያት አልተመዘገቡም ቅሬታ ለምርጫ ቦርድ አስገብተናል።
#አፋር – በተቃዋሚዎች ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ለክልል ምክር ቤት 50 ሲደመር 1 ወንበር ማሸነፍ የሚያስችል ዕጩዎች አቅርበናል በሕዝብ ተወካዮ ምክር ቤትም አባላ ከምትባል ወረዳ እና በትግራይ ድንበር አካባቢ ካለ አንድ ወረዳ ውጪ በሁሉም ዕጩ አቅርበናል።
#ቤኒሻንጉል_ጉምዝ – በፀጥጻ ችግር ምክኒያት በ4 ወረዳዎች ዕጩ ማቅረብ አልቻልንም በ5 ወረዳዎች የተወካዮ ምክር ቤት እና ከፊል የክልል ምክር ቤት ዕጩ አቅርበናል።
#ኦሮሚያ – በሕዝብ ተወካዮችም ሆነ በክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞናል ለምርጫ ቦርድ በዝርዝር ቅሬታ ያቀረብን በመሆኑ መልስ ስናገኝ ዝርዝሩን እመለስበታለሁ።
#ሱማሌ – ለክልል ምክር ቤት ያቀረብናቸው ዕጩዎ 50 ሲደመር አንድ አይሞሉም ለፓርላማም ያቀረብናቸው 11 ዕጩዎን ብቻ ነው። (13 ቦታ ላይ ዕጩ አላቀረብንም)

በክልል ምክርቤት ብቻችንን የክልል መንግስት የመመስረት ዕድል የሌለን በኦሮሚያ፤ በሶማሌ እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ብቻ ነው፡፡ እነሱንም የፀጥታው ችግር ሲስተካከል አሻሽለን በሚቀጥለው አናሻሽላለን፡፡

ሰውን ተስፋ አስቆርጦ በምርጫው ተስፋ እንዲቆርጥ ለማድረግ ያደረከው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ ከቻልክ ከቻልክ የራስህን ፓርቲ ለማጠንከር ሞክር፤ የእኛን ለኛ ተውልን፡፡

ኢዜማ የተስፈኞች ቤት ነው፡፡ እንኳን ባንተ አይነቱ ከሩቅ ተኳሽ አጠገባችን ባሉት ገዳዮቻችን እንኳን ተስፋ አንቆርጥም፡፡

Related posts:

ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”

3 thoughts on “ለኤርሚያስ ለገሰ ቅጥፈት የተሰጠ መልስ! « የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም»

  1. ለኤርሚያስ የመከራከር ፍላጎቱ የለኝም ። ራሱን መግለጽ የሚችል ሰው ስለሆነ ስለ ኤርሚያስ ኤርሚያስ ይመለስ ።
    ግን ኤርሚያስ በጣም ግልጽ የሒሳብ ስሌት ነው ያቀረበው በሒሳብ ስሌት ለማሸነፍ ከምክር ቤት መቀመጫዎች ለ 51% መወዳደር ኣለባቹ ። የት ላይ 51% ያቀረባችሁት ?
    በምርጫ ቦርድ ሪፖርት መሰረት ከአማራ ክልል እና ኣዲስ ኣበባ በስትቀር በቀሪዎቹ ክልሎች ላይይ ያቀረባችሁት ከ 51 % በታች ነው ።

    1. የግል አስተያየት ነው። ለማመላከት የፈለከው ሃሳብ ይገባናል። ከሁሉም ወገን አናግረን እንመለስበታለን

Leave a Reply