ኢትዮጰያ ዳይጄስት ያጋለጠው የኢሜል መልዕክት እንደሚያሳየው፤ በደብረጺዮን ገብረሚካኤል ስም የተጻፈው ደብዳቤ እአአ በማርች 12 /2021 ሲሆን ደብዳቤው ተረቆ የተጻፈው በቀድሞ የትግራይ ልማት ማህበር ሰራተኛ በሆነችው ዶክተር ፊዮና ሜሃንና በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከ20 ዓመታት በላይ በሰራችው ጌል ጎርደን አማካኝነት ነው።

እነዚህ ግለሰቦች ደብዳቤው አርቅቀው ከጻፉ በኋላ ለቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ለነበሩትና በአሁኑ ወቅት የጁንታውን ጉዳይ አሜሪካ ሆኖ እየመራ ያለው ለብርሀነ ገብረክርስቶ መላኩን መረጃው አጋልጧል። ሁለቱ ሴቶች፣ ህወሓት ገና በትግል ላይ እያለ ጀምሮ ወዳጆች እንደነበሩ የገለጸው መረጃው፤ በዚህ ወዳጅነታቸውም የተነሳ እንግሊዛዊቷ ጌል ጎርደን በለንደን የኢትዮጵያ ኤንባሲ ውስጥ ተቀጥራ ለበርካታ ዓመታት አገልግላለች ነው ያለው።

በተመሳሳይም ፊዮና የተባለችው የአየርላንድ ዜጋ ሴት ከህወሓት ጋር በረድኤት ድርጅት ስም በቀድሞ የትግራይ ልማት ማህበር ውስጥ አብራ ስትስራ የኖረች ናት ተብሏል። ይህ መረጃ እንደገለጸውም፤ እነዚህ ሁለት ሴቶች ለንደን እና ደብሊን ሆነው የጁንታውን የውጭውን ዓለም የውሸት መረጃ የሚያሰራጩና የሚያስተባበር ቅስቀሳም የሚያካሂዱ መሆናቸው እንደተደረሰበት የዘገበው ኢፕድ ነው

    Leave a Reply