ባይደን የላኩዋቸው ሴናተር ክሪስ ከውይይቱ በፊት የትህነግን የተደበቀ ግፍና ወንጀሎች በምስል ያያሉ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቀጥታ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር እንዲገናኙና እንዲነጋገሩ የመረጡዋቸው የአሜሪካ ምክር ቤት አባል የሆኑት ክሪስ ኩንስ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ለሕዝብ አደባባይ ይፋ ያልሆኑ የምስል ማስረጃ እንደሚቀርብላቸው ተሰማ።

አዲሱ የአሜሪካ መሪ ጆ ባይደን የቅርብ ወዳጃቸው እንደሆኑ የሚነገርላቸውን ሴናተር በትግራይ ስለደረሰው ሰብአዊ ቀውስና አጠቃላይ ሁኔታ፣ ከሱዳን ጋር ስላለው የድንበር ጉዳይ፣ በተላኩበት አግባብ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር እንደሚነጋገሩ ነው ከዋይት ሃውስ የወጣው አጭር የፕሬስ መረጃ የጠቆመው። ሴናተሩ ከአፍሪካ ህብረት ጋርም በተመሳሳይ ጉዳዮች እንደሚመክሩ በመግለጫው ተመልክቷል።

የሴናተሩ ወደ ኢትዮጵያ መላክ መሰማቱን ተከትሎም አሜሪካ በትግራይ ለደረው የሰብአዊ ቀውስ የሚውል 52 ሚሊዮን የአገሯን ገንዘብ መስጠቷን በህግና በገለልተኛ ወገን ባልተረጋገጠ ዘመቻ ሰላባ ኢትዮጵያን የወነጀሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ይፋ አድረገዋል። መንግስትም ብሊንከን መስመር የለቀቀ ውንጀላ መሰንዘራቸውን ጠቅሶ ተመጣጣኝ ምላሽ ቢሰጥም ወዲያውኑ እርዳታ ለማድረግ አገራቸው ላደረገችው ድጋፍ አድናቆቱን አቅርቧል።

ሴናተሩ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ኢትዮጵያ “ ተከፈተብኝ “ የምትለውንና ዜጎቿ ከዳር እስከዳር የፈጠራ ዜናዎችን በመቃውሞ ዓለም ወደ ቀለቡ እንዲመለስ ለተማጸሙት ድጋፍ የሚሆን መረጃ መዘጋጀቱን ዝግጅት ክፍላችን ሰምቷል።

ኢትዮ 12 እንደሰማቸው ከሆነ ሴናተር ክኒስ ክኑስ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር የፈጸመውን ግፍ የሚያሳይ፣ በጦርነት ሲሸነፍና ሲሸሽ የተገደሉ አመራሮች እንዳይታወቁ አንገታቸውን ያረዳቸውን ምስሎች ጨምሮ በርካታ መረጃዎች ይቀርብላቸዋል።

የዜናው ሰዎች እንዳሉት ሴናተሩ እንዲያዩዋቸው የሚደረገው በዋናነት የተንቀሳቃሽ መረጃ ሲመለሱ ለፕሬዚዳንቱና ኢትዮጵያን በስማ በለው ክስ ለፈረጁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቂ መረጃ እንዲያቀብሉ እንደሚረዳ ታስቦ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በውይይቱ ወቅት የሚነሱ ቁም ነገሮችን ለመቀበል እንዳይቸገሩ በሚል ነው።

በተመሳሳይ በትግራይ የጅምላ መቃብር የሚባሉት ቦታዎች የመከላከያ ሰራዊትን ገጥሞ የተመታ የትህንግ ሃይል በጅምላና በጥድፊያ የተቀበሩባቸው ትኩስ የቀብር ቦታዎች እንደሆኑ መረጃና ምስክር መኖሩ፣ ይህም በመረጃው መካተቱ ታውቋል።

ጆ ባይደን ወዳጃቸው የሆኑትን ሴናት የመላካቸው ዜና ከመሰማቱ ሳምንት በፊት የመከላከያ ሰራዊት ኦፕሬሽን ቁጥር ሁለት መጀመሩንና በርካቶች ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ይህ ዘመቻ መጀመሩን ተከትሎ ቀደም ሲል ሰብአዊ ቀውሱን አቅጣጫ በማሳት ተጎጂዎችን በማይጠቅም መልኩ ሲያሰራጩ የነበሩ ሚዲያዎች “ ምስራቅ አፍሪቃ ልትፈርስ ነው” በሚል የታላላቅ አገሮች ጣላቃ ገብነት “ ሳይመሽ ይሁን” ሲሉ ነበር።

See also  ግደይ እናመሰግናለ! አትሌቲክስ በልዩ ታክስ ፎርስ ይመርመር

አሁን ላይ ባለው መረጃ መከላከያ የመጨረሻ ያለውን ዘመቻ እያጠናቀቀ ሲሆን፣ ከማይፈለጉት በስተቀር የተቀሩት በሰላም ወደ ቄያቸው እንዲገቡ፣ የሚፈለጉትም ቢሆን ኪሳራ ለመቀነስ ሲሉ እጃቸውን እንዲሰጡ የሳምንት ጊዜ ገደብ ሰጥቷል።

ቀደም ሲል ዘመቻው እንደሚከፈት መረጃ የሰጡት ወገኖች እንዳሉት ይሙቱ ይዳኑ በይፋ ያልታወቁት ቀሪ የትህነግ መሪዎችና አዋጊዎች ሙሉ በሙሉ ተከበዋል። ከሳምንት በሁዋላ እጃቸውን ካልሰጡ ኦፕሬሽኑ የመቋጫ ተግባሩን ይጀምራል። መረጃውን የሰጡን አክለው እንዳሉት መንግስት ይህን ከማለቱም በፊት ጀምሮ በጥቅሉ ከ2500 በላይ የትህነግ ሃይል ወዶና ተገዶ እጁን ሰጥቷል።

Leave a Reply