“የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በአገሪቷ ላይ የተከፈተውን ተገቢ ያልሆነ ጫና ለመመከትእየሰራ ነው”

NEWS

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአገሪቷ ላይ የተከፈተውን ተገቢ ያልሆነ ጫና ለመመከት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ገለጸ።

መንግስት በትግራይ ክልል ከወሰደው የሕግ ማስከበር እርምጃ ጋር ተያይዞ ምክንያታዊ ያልሆኑ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠረ እየሰሩ ያሉ አንዳንድ አለም አቀፍ ተቋማትና መገናኛ ብዙሃን መኖራቸው ይታወቃል። በዚህም የኢትዮጵያን መልካም ስም በሚያጎድፍና በሚያጠለሽ መልኩ ሀሰተኛ መረጃ ሲነዛ ቆይቷል ብሏል ኤጀንሲው።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለኢዜአ እንደተናገሩት ዳያስፖራው ማኅበረሰብ ይህንኑ ተገቢ ያልሆነ ጫና ለመቀልበስ ጥረት እያደረገ ነው። መንግስት በትግራይ ክልል የትኛውም ቡድን የከፋ ጉዳት እንዳይገጥመው አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሠብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ እያደረገ እንደሆነም ጠቅሰዋል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ትክክለኛ መረጃ ለዓለም እያደረሱ አይደለም ብለዋል።

በመሆኑም ኤጀንሲው ዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንዲይዝ ዳያስፖራውን የማስተባበር ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ወይዘሮ ሰላማዊት ገለጻ ኤጀንሲው ይህን ተገቢ ያልሆነ ጫና ለመቀልበስ በተለያዩ ዓለምዓቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያንን በማስተባበር እየሰራ ነው።

በተጨማሪም የሚዲያ ባለቤቶችና ለሚዲያ ቅርብ የሆኑ ሰዎች፣ የዳያስፖራ ሚዲያዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያዊያን የትግራይ ክልልን የተመለከቱ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲመክቱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚሁ መሰረት በአሜሪካ፣ በካናዳና በጄኔቫ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሠላማዊ ሠልፍ በማካሄድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲከበር መልዕክት ማስተላለፋቸውን አስታውሰዋል። የሠላማዊ ሠልፎቹ መልዕክት በዋናነት ማንም ሶስተኛ ወገን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል ያመላከተ እንደሆነም ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ የዳያስፖራው ማሕበረሰብ ሠልፍ ከማድረግ ባለፈ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዓለምዓቀፍ ተቋማትና ለመንግስታት እውነታውን እንዲረዱ ፊርማ አሰባስበው መላካቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያዊያን ዳያስፖራዎች በፈረንሳይኛ፣ በእንግሊዝኛና በዓረብኛ ቋንቋዎች ወቅታዊ ሁኔታዎችን የሚያንፀባርቁ ጽሁፎችን እየጻፉ መሆኑንም ጠቁመዋል። በቀጣይም የዳያስፖራው ማሕበረሰብ በጋራ በመሆን በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የሶስተኛ ወገን ጫና ለመመከት መትጋት እንዳለበት አስገንዝበዋል።


Related posts:

አማራ ክልል የሕግ ማከበር ዘመቻውን በሚያስተጓጉሉ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቀ፤ "ዘመቻው በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል"
አብይ አሕመድ "ጠላትም፣ ባንዳም ይወቅ" ሲሉ አስተማማኝ ሰራዊት መግንባቱን አስታወቁ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ

1 thought on ““የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በአገሪቷ ላይ የተከፈተውን ተገቢ ያልሆነ ጫና ለመመከትእየሰራ ነው”

  1. The agency should do all it can to help the Ethiopian born legal residents in Yemen who are currently being heavily injured by Yemenis , also having problems getting medical attentions .

Leave a Reply