በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአብን የተሰጠ መግለጫ፤» አብን ታሪካዊ ጥሪውን ያቀርባል»


የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬና አጎራባች አካባቢዎች የጥላቻ ኃይሎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በሕዝባችን ላይ መክፈታቸውን አረጋግጧል። በዚህም ምክንያት የበርካታ ወገኖቻችን ሕይወት ጠፍቷል፣ አካል ጎድሏል እንዲሁም ከፍተኛ ንብረት ወድሟል።

ጥቃቱ የተከፈተውና እየተፈፀመ ያለው በመሀል የአማራ አካባቢዎች ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ የነበሩ ጥቃቶች ቀጣይ ክፍል ሆኖ ሲሆን በተለይ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚኒሻ የትሕነግን አሸባሪ ኃይል ለመመከት፣ ሕዝቡን፣ ክልሉንና አገሩን ለመከላከል ወደ ክልሉ ምዕራባዊና ደቡባዊ ግዛቶች በሰፊው መንቀሳቀሱን ተከትሎ መሆኑ ብዙ ነገር ይገልጣል።

አብን ቀደም ብሎ መረጃው በደረሰው ወቅት ጉዳዩን በቅርበት በመከታተልና ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማሳሰብ አጥፊዎቹ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት አፋጣኝ እርምጃ ተወስዶ የሕዝባችን ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ ጠይቋል፤ አሁንም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ ይገኛል።

ጥቃቱ በተከፈተበትና በሌሎች ቅርበት ባላቸው አካባቢዎች የምትገኙ ወገኖቻችን በተለይም ወጣቶች የተለያዩ የጥፋት አጀንዳ ባላቸው አካላት ሕዝቡን ለማሸበር ታስበው ከሚለቀቁ ሐሰተኛ መረጃዎች በመቆጠብ፣ ከመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመተባበርና ውስጣዊ አንድነታችሁን በማጠናከር ለሕዝባችን ደህንነት መረጋገጥ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ አብን ያሳስባል።

የአማራ ክልል መንግስትና ገዢው “የአማራ ብልፅግና” የአመራሩን ውስጣዊ አንድነት ከመቸውም ጊዜ በላይ በማጠናከር፣ ለሰርጎ ገቦችና ሴረኞች እንዲሁም አገራችን ኢትዮጵያ እንዳትረጋጋ አበክረው የሚሰሩ የውጭ ኃይሎችና ሚዲያወች በከፈቱት የተቀነባበረ ፕሮፖጋንዳና ወከባ ሳይንበረከክ በሕዝባችን ላይ በየአቅጣጫው የተከፈተውን ዘር ተኮር ጥቃት በብቃት መመከት እንዲችልና ለዚህም ሁሉንም የአማራ ኃይሎች ከጎኑ የማሰለፍ የማስተባበር ሚናውን በቁርጠኝነት እንዲወጣ አብን ታሪካዊ ጥሪውን ያቀርባል።

በአሁኑ ጊዜ የፌደራሉ መንግስት ከበዛ ቸልተኝነት፣ ከታዳሚነት አልፎ አመራሩና መዋቅሩ ለጽንፈኛ ኃይሎቹ በምሽግነትና በድጋፍ ሰጭነት እያገለገለ መሆኑ የተረጋገጠና በራሱ በመንግስት በተደጋጋሚ የታመነ ኃቅ ሆኗል። ስለሆነም መንግስት አገርንና ሕዝብን ወደፊት አንድ እርምጃ ማሻገር ቢሳነው እንኳ ላልተቋረጠ የኋሊዬሽ እንሽርት ዳርጎ ለመቀጠል ያለውን ፍላጎት ደጋግሞ እንዲያጤነው በአፅንኦት እንጠይቃለን።

በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙትን ዘር ተኮር ጥቃቶች በዘላቂነት ማስቆም ካልተቻለና በአጥፊዎቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ የማይወሰድ ከሆነ በቀጣይ ግንባር ቀደም የአገር ኅልውናን አደጋ ላይ የሚጥል ችግር መሆኑ እንደማይቀር ያለንን ስጋት ለመግልፅ እንወዳለን።

Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply