ሕዝቡ ትእግስት በተሞላበት አግባብ ተደራጅቶ አካባቢውን መጠበቅ እንዳለበት የአማራ ክልል ሠላምና ደኅንነት ቢሮ አሳሰበ፡፡

NEWS

የአማራ ክልል ሠላምና ደኅንነት ቢሮ ኀላፊ ሲሳይ ዳምጤ በሰሜን ሸዋ ዞን የተከሰተውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ ቀደም አጣዬ፣ ሸዋሮቢትና ሰንበቴ አካባቢዎች ተደጋጋሚ የጸጥታ ችግር ይከሰት እንደነበር በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ ቀደም ብሎ በጸጥታ ችግሩ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል፡፡ በቅርቡም ከሕዝቡ ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጓል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም ምሽት አንድ ግለሰብ በጥይት መገደሉን ተከትሎ የጸጥታ ችግር መከሰቱን ተናግረዋል፡፡ “የተደራጀ ቡድን” ያሉት ኃይል የቡድን መሳሪያ ተጠቅሞ ጥቃት ማድረሱንም ኀላፊው አንስተዋል፡፡ በዚም ሰዎች ሞተዋል፤ ቆስለዋል፤ ሀብትና ንብረትም ወድሟል፤ የመንግሥት ተቋማትም ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው ያሉት ኃላፊው፡፡

ድርጊቱ የፖለቲካ መዋቅሩን፣ የፖለቲካ መሪዎችን እና ሕዝቡንም ያሳዘነ ነው ብለዋል፡፡ በአካባቢው የጸጥታ አካላት ለመመከት ጥረት መደረጉንም አስታውቀዋል፡፡ ነገር ግን ጥቃቱ በቡድን መሳሪያ የታገዘ በመሆኑ ባለው ኀይል ብቻ መመከት እንዳልተቻለም ጠቅሰዋል፡፡ ተጨማሪ የጸጥታ ኀይል እስኪገባ ግን የአካባቢው ፖሊስ፣ ሚሊሻና የአማራ ልዩ ኀይል ጥቃቱን ለማስቆም ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

አሁን ግን ተጨማሪ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና የፌዴራል ፖሊስ መግባቱን የገለጹት አቶ ሲሳይ ትናንት (መጋቢት 11/2013 ዓ.ም) አጣዬ አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ጥረት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የታጠቀው ቡድን እስካሁን ድረስ ተኩስ መግጠሙን ያመላከቱት አቶ ሲሳይ ጥቃቱን ወደ ማጀቴ፣ ሰንበቴና ሸዋሮቢት አካባቢዎች ለማስፋት እሞከረ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የክልሉ የጸጥታ መዋቅር ወደ ቦታው አቅንቶ ከሰሜን ሸዋ የሥራ ኀላፊዎች ጋር እየሠራ አንደሆነም ገልጸዋል፡፡ አቶ ሲሳይ እንዳሉት በሽብር ቡድኑ ላይ ሕግ የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ እጃቸው ያለበትን አካላት ለሕግ አቅርቦ ተጠያቂ ለማድረግም እየተሠራ ነው፡፡

ቢሮ ኀላፊው እንዳሉት ሁኔታዎችን በአግባቡ መምራት ያስፈልጋል፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል በስሜት ሳይሆን በሰከነ መልኩ ወቅቱን መሻገር እንዳለበትም መክረዋል፡፡ “ሆደ ሰፊ እንሁን ስንል የአማራ ሕዝብን አሳልፈን እንስጥ ማለት አይደለም” በማለትም ሕዝቡ ትእግስት በተሞላበት አግባብ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ቢሮው በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጠረውን ችግር ማን እንደፈጠረው፣ ምን ጉዳት እንደደረሰ በቀጣይ እያጣራ ለሕዝብ እንደሚገልጽ አስታውቀዋል፡፡

ዘጋባው የአብመድ ነው። የአማራ ክልል ሠላምና ደኅንነት ቢሮ

Related posts:

አማራ ክልል የሕግ ማከበር ዘመቻውን በሚያስተጓጉሉ ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታወቀ፤ "ዘመቻው በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል"
አብይ አሕመድ "ጠላትም፣ ባንዳም ይወቅ" ሲሉ አስተማማኝ ሰራዊት መግንባቱን አስታወቁ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ

Leave a Reply