አፍሪካ እና ሩሲያ ባህላዊ ትስስራቸውን መልሰው በመገንባት ወዳጅነታቸውን ማጠናከር ይገባቸዋል – ጠ/ሚ ዐቢይ

NEWS

 አፍሪካ እና ሩሲያ ባህላዊ ትስስራቸውን መልሰው በመገንባት ወዳጅነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ “የሩሲያ-አፍሪካ፣ ባህልን መልሶ መገንባት” በሚል መሪ ሃሳብ  በተካሄደው አለም አቀፍ የፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በበይነ መረብ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም “ባህላዊ ትስስርን መልሶ በመገንባትና ወዳጅነታችን በማጠናከር እንዲሁም በጊዜ ሂደት የተፈተነውን አብሮነት በማጽናት የህዝቦችን መሰረታዊ ጥያቄ ለመመለስ ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ አካላትን መመከት ያስፈልጋል” ብለዋል። ጉባኤው መሪ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሌሎች ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገራዊ ፖለቲካ መረጋጋትና ለአለም አቀፍ ትብብር ያላቸውን ሚና በግልጽ የሚያሳይ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የሩሲያ ፌዴሬሽን የበርካታ ፈላስፎች መኖሪያ መሆኗን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዚህም ለአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና ህዝባቸው ነጻ የሆነችና በኢኮኖሚ የበለጸገች አፍሪካን ለመፍጠር ህልም አንግበው እንዲነሱ መነሳሳት ፈጥረውባቸዋል ብለዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመንግስትን አስተዳደር የተመለከቱ የፍልስፍና አስተምሮቶችን በመከተል በኃላፊነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

ዛሬ ላይ ሁሉም በእውነት ላይ የተመሰረተና ግለሰባዊ ብቃትንና የጋራ የሆነ መልካም ስብዕናን ለመፍጠር የሚያስችል ውጤታማ የሆነ የፍልስፍና እሳቤ ለማራመድ መልካም አጋጣሚ ተፈጥሮላቸዋል ብለዋል፡፡ “እኔም ይህንን እሳቤ የሚያራምደውን የብልጽግና ፓርቲ በሊቀመንበርነት በመምራት ላይ እገኛለሁ“ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

እንደ አጠቃላይ አፍሪካ እና ሩሲያ ባህላዊ ትስስራቸውን መልሰው በመገንባት ወዳጅነታቸውን በማጠናከር የህዝባቸውን ጥያቄ መመለስ አለባቸው ብለዋል። የተባበሩት የሩሲያ ፓርቲ ጄኔራል ካውንስል ምክትል ፀሐፊና የሩሲያ ፌዴሬሽን ሴናተር ኪልሞቭ አንደሬይ በበኩላቸው የጉባኤው ትኩረት በዝግጅቱ ላይ በሚቀርቡ ርዕሶች፣ በሰላምና ደህንነት ፣ ጣልቃ ገብነትን በመመከት ላይ ያተኩራል ብለዋል፡፡

ሩሲያ ኮቪድ 19ን በመከላከል ረገድ ልምዷን ለማካፈልና ክትባቱን ለማቅረብ ዝግጁ መሆኗንም አረጋግጠዋል። እኤአ በሰኔ 2010 “ሩሲያ አፍሪካ፣የትብብር አድማስ” በሚል መሪ ሃሳብ በሞስኮ አለም አቀፍ የፓርላማዎች ጉባኤ መካሄዱንም አስታውሰዋል። የዛሬው ጉባኤ በተባበሩት የሩሲያ ፓርቲ አማካኝነት መዘጋጀቱ ታውቋል።

Related posts:

"መከላከያ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በሚችልበት አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል" አብይ አህመድ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Leave a Reply