በኢትዮጵያ ከ60 ዓመታት በላይ ስራ ላይ የነበረውን የንግድ ህግ አዋጅ ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ

NEWS

በኢትዮጵያ ለ60 ዓመታት ስራ ላይ የነበረውን የንግድ ህግ አዋጅ ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጸድቋል።

የንግድ ህጉን ማሻሻያ በዛሬው እለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል።

በምክር ቤቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ መሰረት አባተ የንግድ ህጉን ረቂቅ አዋጅ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በዚሁ ጊዜ ባለፉት 34 ዓመታት የንግድ ህጉን ለማሻሻል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ቢደረጉም ማሻሻያው ለምክር ቤቱ የቀረበው በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውሰዋል።

ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ አዋጁን የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በዝርዝር አይቶ ማሻሻያ ማድረጉንም ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት የንግድ እንቅስቃሴ አኳያ ለነጋዴው የተሳለጠ አሰራር መፍጠር ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ሰብሳቢዋ፣ በተለይ አገሪቷ የአለም አቀፉ የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን የምታደርገውን ጥረት ያሳልጣል ብለዋል።

የምክር ቤቱ አባላትም የህጉ መሻሻል በተለይ በንግዱ ዘርፍ የሚታዩ ህገወጥ አሰራሮችን ለማሻሻልና ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት ለመዘርጋት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው በኢትዮጵያና በኡጋንዳ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ መስጠትና በወንጀል ጉዳዮች ላይ የጋራ የፍትህ ትብብር ስምምነትንም አጽድቋል።

ስምምነቱ ወንጀል ፈጽመው ከአገር የሚሸሹ ሰዎችን ለፍርድ ለማቅረብና በሁለቱ አገራት መካከል ሰላምና ጸጥታን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ኢትዮጰያና ኡጋንዳ ያላቸውን የድንበር ዘለል ወንጀል ተጋላጭነት በዘመናዊ የምርመራ ዘዴ መረጃና ማስረጃዎች ሳይጠፉ ምርመራ በማከናወን በፍርድ ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደርጋል ተብሏል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባ የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን ለዝርዝር እይታ ለህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መምራቱን ኢዜአ ዘግቧል።

Related posts:

"መከላከያ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል በሚችልበት አስተማማኝ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል" አብይ አህመድ
መንግስት "በመላው አገሪቱ ቁርጠኛ እርምጃ እየወሰድኩ ነው"- የትህነግ ሰርጎ ገቦች ላይም እርምጃ መወሰዱን አስታወቀ
አቶ ወርቁ አይተነው የገንዘብ ቀውስ እየገጠማቸው መሆኑ ተሰማ
ብ/ጄ ተፈራ ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀረቡ
አውሮፓ ህብረት ያዘገየውን ድጋፍ አስመልክቶ ዳግም ሊመክር ቀጠሮ ያዘ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ

Leave a Reply