የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከብልጽግና ጋር ተቀናጀ፤

ብልፅግና ፓርቲና ከሲዳማ አርነት ንቅናቄ / ሲአን / ጋር በመጪው አገራዊ ምርጫ በጋራ ለመወዳደር ያስችላል ያሉትን ቅንጅት መመስረታቸው ከጓሮ ወደ አደባባይ በማምጣት ይፋ አድርገዋል።

የፊታችን ግንቦት ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ሁለቱ ፓርቲዎች ቅንጅት መስርተው ለመወዳደር ከሚያስችላቸው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ይፋ ያደረጉት በጋራ በሰጡት መግለጫ ነው። በመግለጫቸው እንዳሉት ለመቀናጀት ላለፉት ሰባት ወራት አብረው ሲሰሩ ነበር። በመቸረሻም በአብዛኞቹ ነጥቦች ላይ በቅንጅት ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ብልጽግና ከሲአን ጋር ቅንጅት መመስረቱ አስመልክቶ ኢትዮ 12 ያነገራቸው እንዳሉት፣ የሲዳማ ክልል ህዝብ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የሲአን ደጋፊ በመሆኑ ብልጽግና መንግስት ሆኖ ለመቀጠል የክልሉን ድምጽ ሙሉ በሙሉ እንደሚያገኝ ከወዲሁ ማረጋገጫ መሆኑንን ጠቁመዋል።

See also  የሶማሌ ክልል ካቢኔ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅር እንዲገቡ የቀረበውን ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ደገፈ

Leave a Reply