ሕወሓት ከመቐለ እስከ አዲስ አበባ የዘረጋው ወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛ ተደምሰሰ

defense

ሕወሓት በእንደ አባጉና ተራራ ላይ ከመቐለ እስከ አዲስ አበባ የሚደርስ የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛ ዘርግቶ ቢንቀሳቀስም እኩይ ተግባሩ በአጭሩ ተቀጭቶበታል ሲል የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ገጽ ካይ የወጣ ዘገባ አመለከተ።

ተራራው ሠው መውጣት የማይችልበት አስቸጋሪ ተራራ ሲሆን ሕወሓት ሰሜን ዕዝን እንዳጠቃ የዕዙን መገናኛ መስመር ውስጥ ባሉት ተላላኪዎች አማካኝነት ከጥቅም ውጪ ካደረገ በኋላ በተራራው ላይ የሚገኘውን ሬዲዮ ሲጠቀም ቆይቷል።

የ12ኛ ክፍለ ጦር ጁንታው ለእኩይ ዓላማው ማስፈፀሚያ ለብዙ ዓመታት አቅዶ የዘረጋውን የሬዲዮ መገናኛ አስከ ተራራው ጫፍ በመውጣት አውድመውታል።

ከሀዲው ሕወሓት በእንደ አባጉና ተራራ ላይ መሽጐ የመጨረሻ አቅሙን አሟጦ የተዋጋበት ሲሆን በ12ኛ ክፍለ ጦር ተመትቶ ወደ መቃብር ወርዷል ።

በ12ኛ ክፍለ ጦር ሥር የሚገኙ የብርጌድ አመራሮች እንደሚናገሩት ፣ ሠራዊቱ በተራራ ሥር ከፍተኛ ምሽግ ቆፍሮ ተዘጋጅቶ የነበረን ጠላት በመደምሰስ ያሳዩት ጀግንነት የሚደነቅ ነው።

ውብሸት አንበሴ  – ፎቶግራፍ ውብሸት አንበሴ

See also  በሰሜን ጎንደር የጅምላ ጭፍጨፋ ተፈጸመ፤ 120 በላይ ተገለዋል

Leave a Reply