የመቀለ ከንቲባ ከተጠመደ የቦንብ አደጋ ተረፉ፤ ቪኦኤ የጠ/ሚ አብይን ንግግር በደቂቃዎች ልዩነት ሁለት ጊዜ በትህነግ አስተቸ

የመቀለ ከተማ ከንቲባ ቁርስ በልተው ወደ መኪናቸው ሲገቡ መኪናቸው ላይ የተጠመደ ቦንብ እንደፈነዳ ታወቀ። በፍንዳታው መኪናዋ ላይ ጉዳት ሲደርስ ከንቲአባው ሳይጎዱ ቀርተዋል። ቪኦኤ በትናትናው ምሽት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ንግግር በደቂቃዎች ልዩነት ሁለት ጊዜ በትህነግ የውጭ አገር አመራሮች ማስተንተኑ ዓላማው እንዳልገባቸው ታዛቢዎች ጠቆሙ።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርና የኮማንድ ፖስት አመራር አባልና የመቀሌ ከንቲባ አቶ አትክልት ሃ/ስላሴ ከቦንብ ጥቃት የተረፉት ዛሬ ረፋድ 11፡05 አካባቢ ነው። ዜናውን በማህበራዊ ገጹ ይፋ ያደረገው አርአያ ተስፋ ማሪያም እንዳለው  ከንቲባውን በስክል አግኝቶ አደጋው መድረሱን አረጋግጧል።አቶ አትክልት ስለተፈጠረው ሁኔታ  “በመቀሌ ሃድነት ክ/ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርተን ነበር። በጥሩ መንፈስ ከህዝቡ ጋ ስንወያይ አረፈድን። 5:05 ሰአት ሲሆን ቁርስ ለመብላት ማእበል ሬስቶራንት አመራን” ሲሉ አስረድተዋል።

ከንቲባው ቁርስ ጨርሰው ወደ መኪናቸው ሲገቡ ከመኪናው ፊት ለፊት ቦንብ ተጠምዶ ኖሮ ፈነዳ። በፍንዳታው የመኪናው የፊት ሁለት ጎማዎች ተፈንጥረው በሃይል ሲወጡ መመልከታቸውን የገለፁት ከንቲባው የመከላከያ ሰራዊት ልዩ ኮማንዶ ጥበቃዎች አቶ አትክልትን አውርደው በፍጥነት ከአካባቢው መሄዳቸውን ጠቁመዋል።በፍንዳታው የሬስቶራንቱ ዘበኛ ፍንጣሪ እንደመታው ሲታወቅ፣ “መኪናው ላይ ቦንብ ሲጠመድ ዘበኛው ምን ይሰራ ነበር?” የሚለው አጠያያቂ በመሆኑ የክልሉ ጥበቃ ሃይል ዘበኛው ተባባሪ ሊሆን ይችላል ሲል መጠርጠሩም ከዜናው ጋር አብሮ ተመልክቷል።

“ቦንቡን ያጠመደውና ከንቲባውን ለመግደል የሞከረው የጁንታው ሃይል ስለ መሆኑን አያጠያይቅም “ያሉት የክልሉ ኮማንድ ፖስት ሃይል አባላት “ቦንቡን ያጠመዱና ጁንታው ያሰማራቸውን ሃይሎች  በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል” አንድ ከፍተኛ የጦር አዛዥ አነጋግሮ “ጁንታው ወደ አሸባሪነት መውረዱን የዛሬው የሙከራ ድርጊት ያስረዳል፣ በቅርብ ጊዜ የተቀሩትን የጁንታ ሽርፍራፊ አመራሮች ለቃቅመን እንይዛለን፣ ወይም እርምጃ እንወስዳለን” ማለታቸውን አርአያ አክሎ ገልጿል።

ይህ በንዲህ እንዳለ በትናትናው እለት ቪኦኤ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የፓርላማ ንግግር ተከትሎ ሶስት ሰዎችን ጋብዞ ሲያሟግት ነበር። በሙግቱ አንድ ኤርትራዊ ምሁር፣ አንድ መንግስትን የሚደግፉና አንድ የትህነግ የውጭ ስራውን የሚሰሩ አመራር መሆናቸውን ያስታወቁ ተካተው ነበር። አወያዩ አጅንዳ እያሰጠነና በየፊናቸው ሁሉም የመሰላቸውን ሲናገሩ ቆይተው ዘግጅቱ ዛሬ እንደሚቀጥል አስታውቆ ተቋጨና አዳነች ፍስሃዬ ተጋበዘች።አዳነች ፍስሃ አስገዶም የሚባሉ የቀድሞ ዲፕሎማት ጋብዛ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ንግግር ቃል በቃል እያሰማች ለስድብ እንዲመች አድርጋ ስታቀርብ ነበር።

ተቺው ዛሬ ጫካ ገብቶ በሽብር ስራ የተሰማራውን ሃይል የሚያሰማሩ ከመሆናቸውም በላይ፣ ለትችት የሚጠቀሙበት ቃል የሚዲያውንም ደረጃ የጠበቀ አልነበረም።አዳነች እያንደረደረቻቸው ሲዛለፉ የነበሩት የትህነግ የውጭ አካል አመራር ቀደም ሲል አሉላ ሰለሞን ካቅረባቸው የተመጣተነ ክርክር ተጨማሪ ለምን እንዳስፈለገ ዝግጅቱን የተከታተሉ ግልጽ እንዳልሆነላቸው ገልጸዋል። ማስተቸትና መስተንተን አግባብ ያለው ጉዳይ ሆኖ ሲያበቃ በአንድ ፕሮግራም በቡድን ትህነግ ተወክሎ እየተከራከረ ቆይቶ፣ እንደገና በግል መድረክ የሚዘጋጅበት ምክንያት እንዳሳዘናቸው የገለጹ ጥቂት አይደሉም።

አዳነች የመትባለዋ ሪፖርተር በቁጭት ስሜት የተቅላይ ሚኒስትሩይን ንግግር ቃል በቃል እያሰማች ስታስተነትን የዘነዘናና የሙቀጫውን ምሳሌ፣ የዱቄቱን ታሪክና የአሜሪካ ሲናተር አዲስ አበባ ደርሰው መመለሳቸውን አላነሳችም። ተቺው የኤርትራ ወታደሮችን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተናገሩበት አግባብ ውጪ ሌላ መልክ በመስጠት የገለጹ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በገሃድ መውጣታቸውን መናገር እንዳለባቸው ተናገረዋል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ከቀድሞ በበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቶቻቸው አማካይነት መግለጻቸውን የአዳነች እንግዳ እንዳልወደዱትም አመልክተዋል።


 • African Union Suspends Sudan’s Participation in Organisation’s Activities
  MOSCOW (Sputnik) – The African Union (AU) has suspended Sudan’s participation in the activities until the country’s civilian transitional government is restored.In a statement, the AU said that its Peace and Security Council decided to suspend Sudan’s participation in all activities of the organization. Sudanese military detained Prime Minister AbdallaContinue Reading
 • ጌታቸው ረዳ የማያውቃቸው የጄ. ይልማ መርዳሳ ንሥሮች
  …. SU-27 ሆዬ 100KM ላይ ኢላማውን አረጋግጦ ሚሳይልና ቦምቦቹን አራግፎለት ተመልሷል። በዚህ ቅፅበት የጌቾ ሰዎች ፍንዳታ እና እሳትን እንጂ SU-27 መምጣቱንም ማወቅ አይችሉም። ጌቾ ፍንዳታውን በተመለከተ መረጃ ሳይደርሰው/ በማይሰማበት ቅፅበት ጄቱ ሚሳይሉን ካስወነጨፈበት የ 100KM ርቀት አፍንጫውን ወደ ደብረ ዘይት መልሶ ከድምፅ ሁለት እጥፍ በላይ ተወንጭፎ ወደ ጦር ሰፈሩ ለማረፍContinue Reading
 • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
  የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
 • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
  “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading

Leave a Reply