ደራርቱ ቱሉ ዳግም አበራች!! ደራርቱ ዳግም ደመቀች

የባርሴሎናዋ ተንሳፋፊ ልዕት፣ የራክ ላይ ቀዛቪ፣ እንደ ዋና የምትምዘገዘግ፣ እንደ አቡሸማኔ በቁጣ ተፎካካሪዎቿን የምትነዳ ደራርቱ ዛሬ አገሯ አክብራታላች። ፍልቅልቋ ደራርቱ ቱሉ በሚኒቦገቦግ እልህ በሄደችበት ወርቅ እየለበሰች የአገሯን ባንዲራ ከፍ ሲል በሃሴት አንብታ የታላቅስ፣ እንባዋና ኩራቷ ልብን የሚነዝር የኢትዮጵያችን እንቁ ናት።

ደራቱ ሁሉን እንደ ዓመሉ የምትይዝ፣ የተቸገሩትን የንትዳብስ፣ ሰብአዊነት የነገሰባት፣ ሽርና ተንኮል የማያልፍባት የምትጎዳ እንጂ ጉዳትን የማታውቅ የቀናዎች ምሳሌ ናት። ደራርቱ አልቅሳ ሰላም እንዲወርድ የምትማጸን በአደባባይ ያልተሾመች የሰላም አምባሳደርም ናት


➥ የ 2021 አዲስ ሞዴል ኔክሰስ መኪና በኮሚቴው አስተባባሪነት በባለሀብቶች ተሸለመች።

➥ ፌደራል ማረሚያ ❶ኛ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠ የክብር ኒሻን ሽልማት ሸለማት።

➥ አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ሁለት ሚሊየን ብር ( 2,000,000) ሰጣት

➥ ኦሮሚያ ክልል አምስት ሚሊየን ( 5,000,000) እና
ሱሉልታ ያለ የስፓርት አካዳሚ በስሟ ተሰየመላት።

➥ 350 ግራም የክብር ኒሻን በኮሚቴው አስተባባሪነት በባለሀብቶች ተሸለመች።


አልቃሻዋ ደራቱ ከሰላሳ ሰባት ዓመት በፊት በባርሴሎና ድካምን ድል ነስታ በመጨረሻዎቹ ዙሮች ስትፈተለክ ወገን በደስታ ፈንድቋል። በዛ ታላቅ የልዕትነት ሞገስ የጀመረችውን ድል በሲዲኒ ደግማ በደስታ አስቧርቃናለች። ከባልደረቦቿ ምርጥ አትሌቶች ጋር በመሆን ተፎካካሪዎቻቸውን እየቆሰቆሱ ሲማግዱ፣ አንድ ላይ ሲተሙና አንድ ላይ አሸንፈው ባንዲራ ሲለብሱ … ደራርቱ ምሳሌ ሆና ብርካቶች ዱካዋን እንዲከተሉ አድርጋለች። ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያ ስም የሚጎመራበትን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እየመራች ነው። ደራርቱ !!

ዛሬ ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ 350 ግራም የሚመዝን ሀገር አቀፍ የክብር የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበረከተ። ሽልማቱን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አበርክተውላታል።ከኒሻኑ በተጨማሪም 2021 ሞዴል ሌክሰስ ቪ8 መኪና በአገር አቀፍ ደረጃ ተበርክቶላታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አያት አደባባይን በስሟ ሰይሞ ለማልማት መወሰኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፕሮግራሙ ላይ ገልጸዋል። ይህ የሆነው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በኦሊምፒክ እና በሌሎች የስፖርት መድረኮች ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ላደረገችው ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ አገር አቀፍ የእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም በተካሄደበት ወቅት ነው።

የከተማ አስተዳደሩ አደባባዩን ለማልማትም 2 ሚሊዮን ብር መድቧል ብለዋል።በሌላ በኩል በአዳማ ከተማ የሚገኘውን ትልቁን አደባባይ በኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ መሰየሙን ያስታወሱት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ በአንድ ቢሊዮን ብር የተገነባው የሱሉልታ አካዳሚንም በስሟ መሰየሙን አብስረዋል። ዛሬ ከተካሄደው ፕሮግራም ተያይዞ ደግሞ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት 5 ሚሊዮን ብር መሸለሙን የኢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። አትሌት ደራርቱም ለተደረገላት ክብር ምስጋናዋን አቅርባለች።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ በተለይ እ.አ.አ. በ1992 በተካሄደው የባርሴሎና ኦሊምፒክ ላይ በ10 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሆናለች። በእውቅና እና የምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት የሥራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች፣ አርቲስቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply