የአሜሪካ መንግስት የ550 ሚሊዮን ዶላር በጀት ማጽደቁን የአሜሪካ የአለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ዩ.ኤስ. አይ.ዲ የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ሲን ጆንስ አስታወቁ። በራሳቸው፣ በአሜሪካ ህዝብና መንግሥትን ስም አገራቸው የምትከተለውን አቋም ይፋ ማድረጋቸውን አመልክተዋል። ዜናው ኢትዮጵያ ላይ የነበረው ጫና እየተላዘበ ለመምጣቱ አመላካች እንደሆነ ተመልክቷል።

ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ ስራዎቹን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ከኢትዮጵያ መንግስታና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እጅ ለጅ በመያያዘ እንደሚሰሩ ሲናገሩ ዋና ዓላማው የምግብ ምርት ራስን የማስቻል ዓላማን ለምሳካት መሆኑንን አመለክተዋል።

በአሜሪካ ህዝብ እና መንግስት የሚታገዘው ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም (PSNP) ለመጭዎቹ አምስት አመታት በኢትዮጵያ ተጠናክሮ ይቀጥላል እንደሚቀጥል የተናገሩት አስረግተው ነው። ለዚህ ፕሮግራምም የአሜሪካ መንግስት 550 ሚሊየን ዶላር እንደመደበም ይፋ አድረገዋል።

ፕሮጀክቱ ዘጠኝ ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚ የሚያደርግ እንደሆነ አመልክተዋል። ሃላፊው ሁሉን ካሉ በሁዋላ የኢትዮጵያን መንግስት ላለው የአመራር ቁርጠኛነት (commitment and leadership) የአሜሪካ መንግስት አድናቆት እንዳለው ሳይሸሽጉ ገልጸዋል። የሁለቱ አገራት ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አጽንዖት ሰጥተው አስታውቀዋል።

ዜናው ኢትዮጵያ ላይ ተከፍቶ የነበረው ዘመቻ መላዘቡን የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ልዩነት ወደ ነበረበት እየተመለሰ ለመሆኑ አመካች እንደሆነም የጠቆሙ አሉ።


Leave a Reply