ኢትዮጵያ በተራራ የተከበበች መሆኗ ዳመና አዝናቢ ኬሚካልን ወደ አየር ለመልቀቅ ምቹ መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ በተራራ የተከበበች አገር መሆኗ ዳመና አዝናቢ ኬሚካልን ወደ አየር ለመልቀቅ የተሻለ ዕድል እና ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አመለከቱ።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ክንፈ ኃይለማርያም በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፣ ኢትዮጵያ የመልክአ ምድሯ መለያየት የሚታይባት፤ ተራራማ አካባቢዎች የሚበዙባት መሆኗ ዝናብ አምጪ ኬሚካሎችን ወደ ደመና ልኮ ለማበልጸግ ምቹና ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።

አገሪቱ ከቦታ ቦታ የተለያየ የአየር ጸባይ ያላት እንደመሆኗ ፣ አንዳንድ ጊዜ በበልግም አልያም በክረምት በቂ ደመና እያለ ዝናብ የማይዘንብባቸው ጊዜያት አሉ ያሉት አቶ ክንፈ፣ አንዳንዴም ክረምት ሆኖ ዝናቡ በበቂ ሁኔታ ላይገኝ የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል። በክረምትም ደረቃማ የአየር ሁኔታ የሚፈጠርበት ጊዜ አለ። ቴክኖሎጂው በእነዚህ ወቅቶች ደመናውን ወደ ዝናብ ለመቀየር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል።

እስከ አሁን ቴክኖሎጂውን ከ50 የማያንሱ አገራት ተግባራዊ እያደረጉት እንደሚገኙ ያመለከቱት አቶ ክንፈ፣ ከዚህ አንጻር እኛም ወደዚህ ቴክኖሎጂ ለመግባት ጉዞ መጀመራችን ወሳኝና አስፈላጊ ነው ብለዋል ።«ይህ ቴክኖሎጂ እንደ ታዳጊ አገር ብሎም በምግብ እህል ራስን ለመቻል ጥረት ላይ እንደመሆናችን ጥቅሙ ከፍተኛ ነው፤ ውሃ የብዙ ነገሮች መሠረት ከመሆኑ አንጻር ይህንን ቴክኖሎጂ በማበልጸግና በማሳደግ ለግብርና ሥራ ለመስኖ አቅርቦት እንዲሁም የውሃን ክምችት ለማሳደግ ወሳኝ ነው፤ ለአገራችን ልማትና ብልጽግና የጎላ ሚናን እንደሚጫወት ሃላፊውን ጠቅሶ የዘገበው ኢ ፕ ድ ነው።


 • ትህነግ- በኤርትራ ስደተኞች ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እንዲቆም አሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ተነፈሰች
  የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች በትግራይ በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያቆሙ አሜሪካ አሳሰበች በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ በህወሃት ታጣቂዎች እየደረሰባቸው ያለው ጥቃት እና ማስፈራራት እንዲቆም የአሜሪካ መንግሥት አሳሰበ። በትግራይ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ስደተኞች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን እየተገደሉ፣ እየተደፈሩና ንብረታቸው እየተዘረፈ መሆኑን የማይፀምሪ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አስተባባሪ አቶContinue Reading
 • በታደሰ ወረደ ፃድቃን ገ/ትንሳኤን ጨምሮ በ74 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ
  ዐቃቤ ሕግ በእነ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ጀነራል ገብረፃድቃን ገ/ትንሣኤን ጨምሮ በ74 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን በይፋ ማህበአዊ ገጹ ይፋ አድርጓል። ሰነዶችንም አያይዟል። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ክስ የመሰረተዉ ተከሳሾች የፌዴራል መንግስትን በሀይል ለመለወጥ በማሰብ በሽብርተኝነት ከተፈረጀዉ ከህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራሮች ተልእኮ በመቀበል ጥቃት ለማድረስ የሚችልContinue Reading
 • U.S. calls for halt to violence against Eritreans in Tigray
  The United States is deeply concerned about reported attacks against Eritrean refugees in Ethiopia’s Tigray region, a U.S. State Department spokeswoman said on Tuesday, calling for the intimidation and attacks to stop. “We are deeply concerned about credible reports of attacks by military forces affiliated with the Tigray People’s LiberationContinue Reading
 • ትህነግ ቅድመ ሁኔታ አንስቶ ድርድር ጠየቀ፤ “ክተቱ ለትህነግና ለኢትዮጵያ ጠላቶች እንጂ ለትግራይ ሕዝብ አይደለም”
  አዲስ አበባ በሁለት ሳምንት ለመግባት የሚያግደው አንዳችም ሃይል እንደሌለ በይፋ ያስታወቀውና በቃል አቀባዩ ጌታቸው አማካይነት ትናንት ጎንደርና ወልቃይት በአሸባሪው ትህነግ እጅ መውደቁን ያወጀው ቡድን ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ትቶ ድርድር እንደሚፈልግ ማስታወቁ ተሰማ። ለዚሁ ተግባር አዲስ አበባ የገቡ አሜሪካዊ አማላጆች መኖራቸውን ታውቋል። ቀደም ሲል ስምንት ቅደመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ የነበረው የትግራይ ሕዝብContinue Reading

Leave a Reply