ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን በሚዘጋጀው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ፕሬዚዳንቷ በማህበራዊ ትስስር ገጸቸው ባስተላለፉት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት “ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማጣሪያን አለፈ!እጅግ ደስ ብሎናል! ውጤቱ እንደታወቀ በመዲናችን የመኪና ጥሩምባ እየተስተጋባ ነው!! መላው የኢትዮጽያ ሕዝብ ከቡድናችን ጋር ነው፤ ተናጠል ሳይሆን ሕብረት ዓላማን ያሳካል፤ በርቱ!” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፏ የተሰማቸውን ደስታ በክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ ስም ገልፀዋል። ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፋቸው ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋሊያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ታላቅ ፍልሚያ ሲያደርጉ ነበር ብለዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በመልዕክታቸው እንደገለጹት ዛሬ የተገኘው አጋጣሚ በርካቶቻችንን ያስደሰተ ተግባር በመሆኑ በቀጣይ ለሚጠብቀው ወርቃማ አጋጣሚ ብርታት እንደሚፈጥርለት ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

ለሀገራችን ብሎም ለክልላችን ህዝቦች እንኳን ደስ ያላችሁም ብለዋል፡፡ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ እንኳን ደስ አለን ብለዋል።በተመሳሳይም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሕዝብና መንግስት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ በማለፉ የተሰማቸው ደስታ ገልጸዋል።

መላው ኢትዮጵያዊያንም እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ድሉ ኢትዮጵያን ለአፍሪካ ዋንጫ ከማሳለፍ ባለፈ፣ ለብሔራዊ አንድነትና መግባባት ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ነው፡፡ኢትዮጵያን ለዚህ ታላቅ ድል ያበቁት የሀገራችን አግር ኳስ ተጫዋቾችም ከፍ ያለ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋለ፡፡

ena


Leave a Reply