የሃጫሉን ግድያን ተከትሎ በተከሰተዉ ሁከት የግድያ ወንጀል የፈጸሙ እንደየተሳትፏቸው ከአንድ እስከ 22 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው

የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በተከሰተዉ ሁከት የግድያ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች እንደየተሳትፏቸው ከአንድ ዓመት እስከ 22 ዓመት በጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ አካባቢዎች የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በተከሰተዉ ሁከትና ብጥብጥ ዉስጥ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን በፈጸሙ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ በማድረግ በ6 ዞኖች በሶስት ሺህ 373 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ በመመስረት በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል፡፡

ከላይ ከተጠቀሰው የተከሳሾች ቁጥር 90 በመቶ በሚሆኑት ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ከተሰበሰቡት ማስረጃዎችም መካከል ከ90 በመቶ የማያንሱ ምስክሮች በችሎት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን መስጠት ችለዋል፡፡ በህግ ማስከበር ሂደት ውስጥ የተከናወኑ ተግባርትን እና የተገኙ ውጤቶችን ክስ ስንመሰርት እንዳደርግነው ሁሉ በቅርብ ቀን ሰፊ መግለጫ የምንሰጥ ሲሆን ከወንጀል ድርጊቶቹ መካከል አንዱን በተመለከተ ፍርድ ቤት የሰጠውን የቅጣት ውሳኔ እንደሚከተለው አመላክቷል፡፡

በተከሳሾች እነጂሎ በዳሶ (35 ሰዎች) መዝገብ ከቀረቡት 11 ተከሳሾች መካከል 2ኛ ተከሳሽ (ሀቢብ በሪሶ)፣ 5ኛ ተከሳሽ ( አማን አቤ)፣ 6ኛ ተከሳሽ (ሙስጠፋ ዋሪሶ) እና 8ኛ (ሮባ ኤዳኦ) በወንጀል ህግ አንቀጽ 240/3፣ 539(1ሀ) እና 690(1ለ) መሰረት በኦሮሚያ ብ/ክ/መ ምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ 01 ቀበሌ በቡድን በመሆን በቀን 23/10/2013 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ሲሆን የሟች አቶ ገለታዉ አዉላቸዉ መኖሪያ ቤት ቅጥር ጊቢ ሰብሮ በመግባት በአምስት የቤተሰብ አባላት ላይ የግድያ ወንጀል በመፈጸም እና በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንጀል ተሳትፈዋ በሚል እንዲሁም 7ኛ ተከሳሽ (ሮባ አማን)፤ 14ኛ ተከሳሽ (ከድር ራበቶ)፣ 16ኛ ተከሳሽ (አለሙ ነጋሽ) እና 17ኛ ተከሳሽ (ሚኪ ጉዬ) በወንጀል ህግ አንቀጽ 240/3 እና 690(1ለ) ስር ተከሰዉ ክርክር ሲደረግ ከቆየ በኋላ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቀን 17/07/2013 ዓ.ም. በዋለዉ ችሎት የጥፋተኝነት ዉሳኔ በመስጠት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ እንደ ወንጀል ተሳትፎአቸው፡-2ኛ ተከሳሽ (ሀቢብ በሪሶ) በ 20/ሀያ/ ዓመት ጽኑ እስራት ፣ 5ኛ ተከሳሽ (አማን አቤ) በ 22/ሀያ ሁለት/ ዓመት ጽኑ እስራት፤ 6ኛ ተከሳሽ (ሙስጠፋ ዋሪሶ) በ 20/ሀያ/ ዓመት ጽኑ እስራት 8ኛ ተከሳሽ (ሮባ ኤዳኦ) በ 18 /አስራ ስምንት/ ዓመት ጽኑ እስራት ፤ 7ኛ ተከሳሽ (ሮባ አማን) እና 14ኛ ተከሳሽ (ከድር ራበቶ) በወንጀል ህግ አንቀጽ 488/1 እና 690/1ለ ስር እያንዳንዳቸዉ በአንድ ዓመት ከስምንት ወር ጽኑ እስራት እና 1000 ብር የገንዘብ መቀጮ፣ 16ኛ ተከሳሽ (አለሙ ነጋሽ) እና 17ኛ ተከሳሽ (ሚኪ ጉዬ) በወ/ህግ አንቀጽ 488/1 / እና 690/1ለ/ ስር እያንዳንዳቸዉ በ 2 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሙሉ ድምጽ ዉሳኔ መሰጠቱን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል፡፡

በምስክርነት በመሳተፍ ለፍትህ ስርዓቱ ጉልህ ሚናችሁን ላበረከታችሁ ሁሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ ምንጭ አቃቤ ህግ


Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ጋብቻ ሳይፈፀም እንደባልና ሚስት መኖር እና የሚያስከትለው ውጤት
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ

1 thought on “የሃጫሉን ግድያን ተከትሎ በተከሰተዉ ሁከት የግድያ ወንጀል የፈጸሙ እንደየተሳትፏቸው ከአንድ እስከ 22 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደባቸው

  1. እድሜ ልክ ወይም የሞት ቅጣት ቀረ ወይስ ምን ማለት ነው ወይስ ምን ማለት ነው ሃያ ሁለት አመት ብቻ መፍረድ እነዚህ ወንጀለኞች ላይ?
    እያንዳንዳቸው ከአምስት ሰው በላይ በህብረት ተባብረው ገድለው ፣ ንብረት አውድመው ፣ ከጭፍጨፋው የተረፍነውን ለእድሜ ልክ ህመም ፣ ለስደት እና ለበሽታ ጥለውን ሃያ ሁለት አመት ብቻ መታሰር ያንሳቸዋል። ከስደት ሆነን በድጋሚ እንድንመሰክር እድል ይሰጠን። ይህ ፍርድ ሌሎችን ወንጀለኞች ግፉበት ግደሉ ብትያዙ እንኳን ቅጣቱ ትንሽ ነው እንደማለት ነው መታየት ያለበት ከተፈፀመብን ግፍ አንፃር።

Leave a Reply