አልሲሲ «የግብፅን ውሃ አንዲት ጠብታ እነካለሁ የሚል ይሞክር… ይህ ለግብፅ ቀይ መስመር ነው»

የግብፁ ፕሬዝዳንት አልሲሲ «የግብፅን ውሃ አንዲት ጠብታ እነካለሁ የሚል ይሞክር:: የግብፅን ውሃ አንዲት ጠብታ ለመንካት የሚደረግ የትኛውም ሙከራ አጠቃላይ ቀጠናውን ያተራምሰዋል:: ይህ ለግብፅ ቀይ መስመር ነው:: >> ብሏል:: አክሎም << ይህን ስል ግን ለማስፈራራት ሳይሆን የህዳሴ ግድብን አሞላል እና ኦፕሬሽን በሚመለከት ህጋዊ ስምምነት ላይ እንደርሳለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ:: ምርጫችን ድርድር ነው:: ወደ እርምጃ ከገባን ግን አስጠሊታ ነው»ብሏል::

በርግጥ ማስፈራሪያ ቢሆንም ትንሽ ግን የተምታታ ነው:: ግራ የገባው ነገር አለ:: ዛቻውን እየዛተ መልሶ ደግሞ ለማስፈራራት አይደለም ይላል:: ብቻ ምንም ይሁን ምን ከዚህም በላይ ክፉ ነገር ቢል አለያም ሊያደርግ ቢሞክር ሊገርመን አይገባም:: ያው ግብፅ ነች:: ታሪካዊ ጠላት::

ሰሞኑን ደግሞ አውሮፓ ህብረት ለማደራደር ትልቅ ጉጉት አሳይቷል:: መሃል ለመግባት ቋምጧል:: ያሰሉት ስሌት እንዳለ ግልፅ ነው:: ለዚያም ነው በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ፈልገው ይተውት:: ገምተን ነበር:: ግምታችን ልክ ነው:: አሁን ነገሮች የበለጠ ግልፅ እየሆኑ ነው:: በኢትዮጵያ ላይ ያ ሁሉ ሲወርድባት የከረመው አለም አቀፍ ጫና ውሉ እየለየለት ነው:: አሜሪካ በሉት አውሮፓ በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው አቋም አንድና ያው ነው:: ከድህነት እንድንወጣ አይፈልጉም:: አሻንጉሊት መንግስት አስቀምጠው በሪሞት ማዘዝ ነው የሚሹት:: ይህ ግን ጊዜውን አይመጥንም:: የሃገራችን መንግስትም እንደዛ እንዳልሆነ አይተውታል::

ጉዳዩ ግን ይህ ብቻም አይደለም:: ኢትዮጵያ እና ቻይና እንዲሁም ራሽያ እና ኤርትራ እየሄዱበት ያለው ግንኙነት ስጋት ውስጥ አስገብቷቸዋል:: በዚህ አያያዝ የአፍሪካ ቀንድንም ሆነ መላውን አፍሪካ እንደሚያጡት አውሮፓ እና አሜሪካ ያስባሉ:: ስለዚህ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ላይ በሰበብ አስባብ ጫና ማሳደሩን ተያይዘውተ ከርመዋል:: ቢችሉ ሊያተራምሱንም ይሻሉ:: ካልሆነም በዛቻቸው ሊያስቆሙን ይፎክራሉ:: በዚህም የቻይናን እና የሩሲያን አካሄድ መግታት አንዱ አላማቸው ነበር:: ምኞታቸው ግን የተሳካላቸውም አይመስልም:: ይሄ ዛቻም በህዳሴው ግድብ ዙሪያ እነሱ ወደሚፈልጉት የአደራዳሪነት ሚና ለማምጣት መሆኑን መገመት አይከብድም::

ብቻ ከትላንቱ ይልቅ ሁሉም ነገር ግልፅ እየሆነ ነው:: ጠላቶቻችን በተለያየ ዘዴ እንደሚመጡ ይጠበቃል:: አንዱ ሲዘጋ ሌላኛውን በር ይሞክራሉ:: አልሲሲም ተስፋ የቆረጠ ይመስላል:: ዛቻውን በግልፅ መናገር ጀምሯል:: ዛቻን እንዲህ መግለፅ የዲፕሎማሲ ተሸናፊነት እንጅ ያሸናፊነት ምልክት አይደለም:: በርግጥ ያበሳጫል!!!

See also  በርካቶች ወደ አማራ ክልል በሚፈልሱበት አቅጣጫ የትህነግ ተዋጊዎች እጅ እየሰጡ ነው

ውሃውን እንዳንሞላ የሚከለክል አንዳች አለም አቀፍ ህግ እንደሌለ ምሁራን አረጋግጠዋል!!! ድርድሩንም አፍሪካ ህብረት ቀዳሚውን መብት ተቆናጧል:: አፍሪካዊ መፍትሄ ለአፍሪካ ችግር የሚለው ገዥ መርህም እጅግ ቅቡል ነው!!! ለመጭዋ አፍሪካም አንድምታው ብዙ ነው!!! መንግስታችንም እዚህ ላይ አጥብቆ ይዟል!!! ትክክለኛ እርምጃ መሆኑም ተመስክሮለታል!!!! ግብፅ እና ሱዳን ከፈለጉ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሚደረገውን ድርድር ይቀበሉና ይደራደሩ:: አውሮፓ ህብረት አሜሪካ አለም ባንክ ወዘተ የሚባለው ዝባዝንኬ ኢትዮጵያ እንደማትቀበል በአምባሳደር ዲና ተገልጿል:: ሌላ ኮተት አንሻም!!!

ውሃችንን እንሞላለን!!!! ብርሃናችን ይፈጥናል!!! ጉዞ ራስን ወደመቻል!!!! የጠላቶቻችን ዛቻና ማቅራራቱም ያልፋል!!! እኛ ግን አንድነታችንን ብቻ እናጥብቅ!!!! ለግድቡ አስፈላጊውን እገዛ እንስጥ!!!! የዲጂታል ዲፕሎማሲያዊ ይጠናከር!!!! በውጭ እየተቋቋሙ ያሉት የሎቢ ቡድኖች ይጠናከሩ!!!! ጥያቄያችን ፍትሃዊ ነውና አምላክ ያግዘናል!!!! ኢትዮጵያ ታሸንፋለች!!!!

By Dejene Assefa

Leave a Reply