የሰላም ሚንስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ከቅጥር ነብሰ ገዳዮች አመለጡ፤ ” እኔ ውስጥ እናንተ፣እናንተ ውስጥ እኔ አለን”

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከትህነግ የቅጥረ ነበሰ ገዳይ ቡድኖች ቀለበት ማምለጣቸው ተሰማ። ግድያው የከሸፈው የአገር ደህንነት ቀድሞ መረጃ አግኝቶ ይሁን አይሁን አልታወቀም። መንግስትም በይፋ አላሳወቀም። ትግራይ በስለም ኮንፍረንስ ላይ ” እኔ ውስጥ እናንተ፣እናንተ ውስጥ እኔ አለን” በሚል እንባ እየተናነቃቸው ያስተላለፉት የሰላም ጥሪ ለሚኒስትሯ እንደ ታላቅ ታሪካዊ ሰነድ ሆኖ የተያዘ ንግግር መሆኑ አይዘነጋም።

ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ በሁዋላ በትግራይ የሚላስ የሚቀመስ መጥፋቱ በትግያ ተወላጆች ከፈተኛ ጩኸትና ተቃውሞ የቀረበበት ጉዳይ ነበር። መንግስት ለጉዳይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ወ/ሮ ሙፈሪያትን ወደ ትግራይ ልኮ ለሶስት ሳምንት ያህል እዛ ሆነው ከዓለም ዓቀፍ እርዳታ ተቋማት ጋር ሲሰሩ እንደነበር ይታወቃል።

ከዓለም የምግብ ድርጅት ባለስልጣናት፣ ከተለያዩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ የአውሮፓና አሜሪካ ተወካዮች እንዲሁም ከተለያዩ ለጋሽ አገሮች ጋር በመቀሌ ሆነው አብረው ሲሰሩ እነደከረሙ ዜናዎች ሲሰራጩ ነበር። በትክክል ያለውን መረጃ በአካል በመገኘት በማስረዳት ሰፊ ስራ የሰሩትና በርካታ ሪፖርቶች እንዲላዘቡ ሃቅ ያስጨበጡት ወ/ሮ ሙፈሪያት፣ ከህግ ማስከበሩ ዘመቻ በፊት ጀምሮ እያለቀሱ ሰላም እንዲወርድ ሲማጸኑ  ተግባራቸው አልተወደደላቸውም ነበር።

በርካታ የትህነግ ደጋፊዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ” ኮበለሉ” ከሚለው የሃሰት ዜና ጀመሮ ከፍተኛ ስድብ ሲያወርዱባቸው ነበር የሰነበቱት። አንዳንዶቹ ዛቻም ያሰሙ ነበር።

ወ/ሮ ሙፈሪያት ታስቦበት ይሁን በድንገት ባስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ጥሪ የደረሳቸው በቀጥታ ለሳቸው እንደነበር የዛጎል መረጃ አቀባይ አስታውቀዋል። መረጃው በደረሳቸው ቅጽበት በመከላከያ ሰራዊት እይታ ውስጥ ሆነው አውሮፕላን ተሳፈሩ።

እሳቸው ወደ አዲስ አበባ ካመሩ በሁዋላ በትግራይ ለእሳቸው በተመደበቸው ተሽከረካሪ ላይ ጥቃት ተሰነዘረ። መረጃውን ያጋሩት እንዳሉት ሁለት ሰዎች ተጎድተዋል። ማንነታቸውን ግን ለጊዜው ማወቅ አልቻሉም።

” መተናኮስ አገርን ከመከፋፈል የተለየ አይደለም” ሲሉ መቀለ በሰላም ኮንፈራንስ ላይ ንግግር አድረገው ነበር። በዛው ንግግራቸው እብሪት፣ንቀት፣ እኔ ከሌላው እበልጣለሁ ማለት እንዴት እንደመጣ፤ በለው፣ ፈለጠው፣ ቁረጠው … የሚለው ፉከራ እንዴት ሊመታ ቻለ በሚል እያለቀሱ ሰላምን ሲማጸኑ እንደነበር ይታወቃል።

መረጃ ካቀበሉን ውጪ ዜናውን የመንግስትም ሆነ የትግራይ ክልል አላረጋገጡም። ትግራይ ክልል የሚኖር የማህበራዊ ገጽ ተባባሪያችን ለማጣራት አንድ ሃላፊ ጋር ደውሎ ለማናገር ቢሞክርም ሃላው ምንም ለማለት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጸው ስልካቸውን ዘግተዋል። ይሁን እንጂ ጥያቄውን ስምተው አላስተባበሉም።


Related posts:

መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”
በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አማራ ክልል ትህነግ ዳግም ጦርነት ስላወጀ የ"ዝግጁነትን" አዋጅ አወጣ
ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Leave a Reply