የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ልክ ትህነግና ኦነግ ይጠይቁት እንደነበረውና በሚዲያ ኢትዮጵያ ላይ አነጣጥረው ዘመቻ የከፈቱት በስተመጨረሻ አቋማቸውን ይፋ እንዳደረጉት የሽግግር መንግስት ይመስረት የሚል ይዘት ያለው ጥሪ አቀረቡ።

ኮሚሽነሩ በአርት ቲቪ በአርትስ ወቅታዊ ፕሮግራም እንግዳ ሆነው “የተወላገደ አቋም ተይዞበታል” በሚል ኮሚሽናቸው በሚወቀስበት የማይካድራ ሪፖርት መዘገየት ጉዳይ ለተጠየቁት የሰጡት ምላሽ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። ይህን አነጋጋሪ አስተያየት ተከትለው ያቀረቡት የሽግግር መንግስት ይዘት ያለው ጥያቄ ግራ እንዳጋባቸው በርካቶች እየጠቆሙ ነው።

በወለጋ የተፈጸመውን አስነዋሪና ትርጉም አልባ ጭፍጨፋ ተከትሎ ዶክተር ዳንኤል በሚመሩት ኮሚሽን የፌስ ቡክ ህጋዊ ገጽ ላይ “ሰፊና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ እቅድ መንደፍ ይኖርበታል” ብለዋል። እጅግ አጭርና አሻሚ ትርጉም ባለው መልዕክታቸው “ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት” ሲሉ እነማንን እንደሆነ፣ “ መጠነ ሰፊ” ሲሉ የሰየሙት እቅድም እምን ድረስ እንደሆነ ግልጽ አላደረጉም።

“በምእራብ ወለጋ በትላንትናው እለት በነዋሪዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ አለመሻሻሉንና ይልቁንም በክልሉና በአዋሳኝ አካባቢዎች እየተስፋፋና ተያያዥ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያስከተለ መሄዱን ያሳያል:: የፌዴራል መንግስት አካባቢውን ለማረጋጋት በጊዜያዊነት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች በተጨማሪ ነዋሪዎች በየትኛውም ክልል በሰላም የመኖር መብታቸውን በሚያረጋግጥ መልኩ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር መጠነ ሰፊና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ እቅድ መንደፍ ይኖርበታል“

የኮሚሽነሩ ሙሉ መልዕክት ከፌስቡክ የተወሰደ
Bilderesultat for wolega massacre ethiopia

አክቲቪስ ስዩም ተሾመ “ የዚህ ሰው ነገር አላማረኝም ” በሚል ቀድሞውኑ ጥንቃቄ እንዲወሰድ በሚያሳስብ መልኩ ሃሳብ ሰንዝሮ እንደነበር የሚጠቅሱ “ የኮሚሽነሩ ጥያቄና የጥያቄያቸው እንደምታ ሙሉ በሙሉ ትህነግና ኦነግ እንዲሁም አገሪቱ ወደ ከፋ ቀውስ ታመራለች በሚል እያስፈራሩ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ከሚጠየቁትና ዛሬ በህግ ጥላ ስር ካሉ ክፍሎች አቋም ጋር፣ እንዲሁም በተቀናቃኝ ፖለቲከኛ ስምና ተናበው አገር በማመስ ተግባር ከተሰማሩ ሚዲያዎች አቋም ጋር አንድ ሆኗል” ሲሉ ይናገራሉ።

በአገሪቱ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመና ንጹሃን እየታረዱ ባለበት፣ ሴት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መቀለ እንስሳት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ ታግተው በጅምላ መደፈራቸውና አስነዋሪ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው እየተናገሩ ሳለ ኮሚሽኑ በክብር፣ ባማረ ህንጻ ተቀምጠው ጉዳያቸው በህግ ለሚታይ የትህነግ አመራሮች ቅድሚያ መስጠቱ ኮሚሽኑንን ግምት እንዲወድቅ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል ቅድሚያ የሚይዙ ጉዳዮች እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ።


ተጨማሪ ያንብቡ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን “የግፍ ደረጃ መዳቢ” – የማይካድራ ምርመራ ላይ ደባ እየተሰራ መሆኑ ተሰማ፤ ኮሚሽኑ ምላሽ ከለከለ


በተጨባጭ በማይካድራ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ በግልጽ አካባቢውን ሲያስተዳድር፣ በነበረው ወይም በወቅቱ ስራ ላይ በነበረው ሃይል ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎችና ሳምሪ በሚባል የወጣቶች ቡድን ወይም ኢመደበኛ አደረጃጀት እንደተፈጸመ በመጀመሪያ ደረጃ የኮሚሽናቸው ሪፖርት መገለጹን ለአርት ቲቪ ጠያቂ በማብራራት ሪፖርቱ እንዳልዘገየ የጠቆሙት ዶክተር ዳንኤል፣ “… ከህወሃት መመሪያ በቀጥታ ተሰጥቷቸው ነው ወንጀሉን የፈጸሙት ለሚለው …” መረጃ እንደሌለ አመልክተዋል። እንደ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች ያለ መረጃ መናገር እንደማይችሉ ጠቅሰው በማይካድራ ጭፍጨፋ የትህነግ አመራሮች ይኑሩበት አይኑሩበት እንደማያውቁ በይፋ ማስታወቃቸው አሁንም ኮሚሽነሩን ያሳጣ ጉዳይ ሆኗል።

“ ትህነግ በኢትዮጵያ በህዝብ ተመርጬ የማስተዳድር ብቸኛ የህዝብ ተወካይ እኔ ነኝ” በማለት አደባባይ የሚናገረውን ጉዳይ ዶክተሩ እንደገለበጡት የሚናገሩ እንዳሉት “ ትህነግ በሚመራው ክልል ውስጥ ወታደር፣ ፖሊስ፣ ሚሊሺያና ወጣቶችን ያደራጀው የትኛው የጎረቤት አገር ፓርቲ ነው?” ሲሉ ይጠይቃሉ። ኮሚሽነር ዳንኤል ይህን ሃቅ እንዲያብራሩ አለመጠየቃቸው በጃቸው እንጂ ከዛም በላይ ሄደው የትህነግን አመራር ነጻ ለማውጣት ይሞክሩ እንደነበር ይገልጻሉ።


ተጨማሪ ያንብቡ ዶ/ር ዳንዔል- በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ የለም


በትግራይ ተፈጽሟል የተባለው የስብአዊ መብት ጥሰት በሙሉ ሊመረመር እንደሚገባው የሚያምኑ በርካታ ገለልተኛ ወገኖች እንደሚሉት፣ አክሱም ለተሰራ ወንጀል መንግስት ላይ ማላከክ፣ ማይካድራ፣ ራያና ድፍን ወልቃይት ላይ ለተፈጸመ ጥቃትና ዘመን ያስቆጠረ ግፍ “ ትህነግ በቀጥታ መመሪያ ስለመስተቱ መረጃ የለም” በሚል መቅለስለስ አግባብ እንዳልሆነ ይናገራሉ።

ትርምስን በኢትዮጵያ በውክልናና በባንዳነት በማስፋት መንግስትን ለመጣል ያለመው የትህነግ አጀንዳ ባይመክን ኖሮ የአማራ ክልልና በመውረር፣ ኦነግ ኦሮሚያን እንዲቆጣጠር በማድረግ፣ በደቡብ ያደራጇቸውን በማነቃነቅ የሽግግር መንግስት ለማቋቋም እንደሆነ በመረጃ መረጋገጡን ያወሱ እንዳሉት፣ “አገሪቱን ለማተራመስ አጀንዳ የተቀበሉ ቀውሱን እያባባሱ ያሉት በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ መሆኑ እየታወቀ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይህንኑ ሃሳብ በስተመጨረሻ ማራመዱ አንድም ሃላፊነቱ አይድለም፤ ሁለትም የነጮቹ አገለጋይ በሆኑንን አደባባይ ያሳየበት ነው”

በሺህ በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ በተፈጸመ ዘግናኝ ወንጀል፣ በሚሊዮኖች በሚቆጠር የሃብት ውድመት፣ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ተፈናቃዮች፣ ለማየትና ለመስማት በሚቀፍ የግድያ ወንጀል የተሳተፉ አካላትን የመሩ፣ ያስተባበሩ፣ ይረዱና ያደራጁ አካላት ነጻ ሆነው ሁሉ አቀፍ ንግግር ወይም “ ሁሉን ያካተተ የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚል ጥያቄ ማቅረብ በጅጉ አሳፋሪ ነው” ሲሉ ኮሚሽኑ አቋሙን እንዲመረምር በርካቶች እየጠየቁ ነው።

በተመሳሳይ ዜና በኦሮሚያ “ የዲቃላ ፖለቲካ” ፕሮግራማቸው ከምርጫ የገፋቸው አካላት የወለጋውን እልቂት ተከትሎ መግለጫ በማውጣት “ መንግስት ዜጎቹን ሊጥበቅ ይገባል” ብለዋል። በውል የማይታወቀው የኦነግ ሸኔ የምዕራብ ግንባር ሃላፊ ጃል መሮም እንዳሻው ሃሳቡንና ስሙን በሚቀያይርበት ቪኦኤ ቀርቦ “መንግስት ዜጎችን ሊጠብቅ ይገባል” ሲል ተናግሯል።

ጃል መሮ “ የሚከሰሰው ኦነግ ሸኔ እኔ የኦሮሞ ነጻነት ጦር መሪ ነኝ። ለምን እጥየቃለሁ” በሚል ስላቅ መንግስት ዜጎችን እየገደለ እንደሆነ በድጋሚ ተናግሯል። ሰለሞን “ ሞተሃል ይባላል” በሚለው የማስተባበያ ወለል ላይ እንዲጨፍር ያመቻቸለት ጃል መሮ “ የኦነግ ሰራዊት አንድም ንጹህ ዜጋ አይገድልም” ሲል አልሞገተውም። አሁን ብቻ ሳይሆን ለውጡ ከመጣ ጀምሮ የሚጨፈጨፉት ወገኖች “ ኦነግ ሸኔ ጨፈጨፈን” እያሉ ሲመሰክሩ እንዳልነበር ፣ኦነግ ሸኔም በኩራት ቪዲዮ እየቀረጸ ጀግነቱን ሲያሳይ፣ መሪው ጃልመሮን ሬሳ ላይ ቆሞ ሲያመሰግን እንዳልታየ ቪኦኤ እንዲህ ዓይነት የተሳከረ መረጃ ማቅረቡ በርካቶችን አበሳጭቷል። ጉዳዩን ለታሪክ የተውም አሉ።


Leave a Reply