” አባትህን ገድለነዋል ና እየው ” ትህነግ ለ13 ዓመት ልጅ የአናቱን አስከሬን ሲያሳይ ከተናገረው!! ለዚህ ግፍ ማን ይጩህ?

በርካታ ግፍ ስለመፈጸሙ ጥርጥር የለም። የመከላከያሰራዊት አባላት መሳሪያ ካወረዱ በሁዋላ ታግተው እያለ ታርደዋል። ተጭፍጭፈዋል። ሴት ጀግኖቻችን ግዳጅ ላይ እያሉ በተመሳሳይ ታርደዋል ተጭፍጭፈዋል። መሳሪያ ካወረዱና ከታገቱ በሁዋላ በዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ አጉረው የፈጸሙባቸው ጉድ ለመጻፍ ይከበዳል። ይህ ሁሉ የሆነው ” አገሬ” ብለው ከሞት ተርፈው ድንበር ሲጠብቁ 22 ዓመታት በኖሩባት ትግራይ ነው። ትህነግ ግፍ አያልቅም የመከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገጽ ላይ እምኞች ከትግል ሜዳ የሚልኩትን ደብዳቤ ያትማሉ። የ13 ዓመት ልጅና ታናኙን የአራት ዓመት ሕጻን ያለ አባት ያስቀረው ትህነግ፣ ለ13 ዓመት ሕጻን ” አባትህን ገለነዋል። ናና እየው” ብለውታል። ከፌስ ቡኩ ላይ የተወሰደውን እንዳለ አንብቡት።

አባታቸውን ለሀገር የሰጡ ልጆች… የአራት አመቷ ህፃን ፤ ዛሬም ድረስ እናትና አባቷ በህይወት እንዳሉ ሁሉ ፤ የሰዎችን ድምፅ በሰማች ቁጥር ወላጆቿን እንባ ባዘለ የልጅ አይኖቿ ትፈልጋለች ።

የ13 አመቱ ታላቅ ወንድሟ ግን መፃኢ ዕድልና ዕጣ ፋንታው ምን ላይ እንደሚጥለው አይወቅ እንጂ ጥሩ እንደማይሆን ይገምታል ፤ እናትና አባቱ በወራቶች ልዩነት ወደማይቀርበት ሰማያዊው አለም መሄዳቸውን አይቷልና ጨቅላ አዕምሮው አምኖ ተቀብሎታል ።እነኚህ ሁለት ህፃናት እናታቸውን በህመም የዛሬ ዘጠኝ ወር ፤ አባታቸውን ደግሞ በፅንፈኛው ጁንታ የግፍ አገዳደል የዛሬ አምስት ወር ገደማ ነው ያጡት ።

የ13 አመቱ ታደጊ ጁንታው አባቱን ከገደለበት በኋላም ፤ አባትህን ገድለነዋል ና እየው ተብሎ የአባቱን በደም የተነከረ አሰከሬን በግድ እንዲያይ የተደረገ ፤ የተሰዋ ወታደር አባቱን አይቶ ሲያለቅስም በጁንታው ልዩ ሀይል በሰደፍ ተመቶ የአባቱ አስከሬን ላይ የወደቀ ታዳጊ ነው ።የነዚህ ልጆች አባት ከመሰዋቱ በፊት ፤ ጁንታው ከልጆቹና ከሀገሩ አንዱን እንዲመርጥ ሶስት ጊዜ እድሉን ሰጥቶት ነበር ።

እሱ ግን ሀገሩን መረጠ ። እንዲህም አለ ።” ልጆቼ ያለ እኔ ማንም ፤ ምንም የሌላቸው የሙት ልጆች ናቸው ። እግዚአብሄር ከፈቀደና ከጦርነቱ ከተረፍኩ አገኛቸው ይሆናል ። አሁን ግን ምርጫዬ ሀገሬ ናት !! “እንዳለውም ፤ ይኸው ግለሰብ ለስምንት ቀናት ያህል ከሚመራቸው ጥቂት አባላት ጋር በጀግንነት ሲዋጋ ቆይቶ በዘጠነኛው ቀን ለሚወዳት ሀገሩ ክቡር መስዋዕትነትን ከፍሏል ።ሀገርን ሲወዱ እንዲህ ነው ። ቤተሰብ አልባ ፤ ቤት አልባ ፤ መሄጃ አልባ ልጆች ቢኖሩንም እንኳን ፤ ሀገር በተጠቃች ጊዜ ለክብሯ መሞት !!

ነጻነት ሸዋንግዛውፎቶግራፍ ነጻነት ሸዋንግዛው – ከመከላከያ ሰአርዊት የፌስ ቡክ የተወሰደ


 • ጃል መሮ በትግርኛ – ከትህነግ ጋር ሲመክር ተጠለፈ ” 70 ከመቶ ጨርሰናል አዲስ አበባ ነው የቀረን”
  የአሜሪካ ድምጽ ማንነቱን ሳይጠይቀውና ሳያውቅ ሰፊ ቃለ ምልልስ በተደጋጋሚ ሲያደርገልት የነበረው ጃል መሮ በትግርኛ ከትግራይ ስሙ ካልተገለጸ ባለስልጣን ጋር ስለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ሲመክሩና መረጃ ሲቀባበሉ የሚያስረዳ ድምጽ ሆነ። ሌላው ቢረሳ በኢሬቻ ብቻ ከስምንት መቶ ሰዎች በላይ ሰዎችን የጨረሰ ትህነግ ከመላው ኦሮሞ ጋር ህብረት እንደሌለው በማስረዳት በተዘጋጀው ዶክመንታሪ ዝርዝሩን ይመልከቱ። ኦሮሞ በሃዘንናContinue Reading
 • “ወታደራዊውን ጉዳይ ለእኛ ተውልን” ሌ/ጄ አበባው ታደሰ
  “እናንተ ደጀን በመሆን ከጀርባችን ሁኑልን እንጂ ወታደራዊ ጥበቡን ለእኛ ተውልን” የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታምዦር ሹም ሌ/ጄ አበባው ታደሰ ማስታወቃቸው ተሰምቷል። መከላከያ ሰራዊትንም ሆነ ደጀኑንን ሕዝብ በወሬ ለማተራመስ ተከፍሏቸው የሚሰሩ፣ አገር ወዳድ መስለው የሚቀስቀሱና በባንዳነት አገር እያስመቱ ያሉ ላይ ሕዝብ እርምጃ እየወሰደ መሆኑም ተሰምቷል። ጠላትንም ለመመከት ህዝብ እየጎረፈ ነው። “ኢትዮዽያ እየሞትንContinue Reading
 • አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች
  አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች። “ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲውContinue Reading
 • የሽብርተኛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ የሠራዊታችንን የድል ግስጋሴ አይገታውም !
  ሽብርተኛው ከሚታወቅባቸው ስልቶቹ መሀል አንዱ ቅጥፈቱ ነው ፡፡ ጉልበት ሲያንሰው ምላሱ ይረዝማል ፤ ያልሆነውን ሆንኩ ፣ ያላደረገውንም አደረኩ…ይላል ፡፡ ይህ ደግሞ ጥርሱን የነቀለበት እና ተወልዶ ያረጀበት ባህሪው ነው ፡፡ አንድም ቀን ከአፉ እውነት ተገኝታ የማታውቀው ይህ ሽብርተኛ ፣ ሽንፈቱን የሚሸፍነው የሠራዊታችንን ስም በማጠልሸት ነው ፡፡ ደጋፊዎቹ ኪሳራውን እንዳያወቁ ፣ ሰላማዊውContinue Reading

Leave a Reply