ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆምና መንግስት ህግ እንዲያስከብር ፓርቲዎች አሳሰቡ


ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸም ጥቃት እንዲቆምና መንግስት ህግ እንዲያስከብር አምስት ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ አሳሰቡ፡፡

ፓርቲዎች በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመውን ዘር ተኮር ጥቃት በማውገዝ መንግስት ህግ እንዲያስከብር ጠይቀዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቀቅናቄ (አብን)፣ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣ እናት ፓርቲ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ የፌዴራሉ መንግስትና የየክልሎች መንግስታት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለልተኛ ኮሚሽን በማቋቋም በጥልቀት መርምሮ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በእንዲህ አይነት አገራዊ አደጋ ወቅት በጋራ እንደሚሰሩም በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

በጥቃቶች ላይ በሚሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ እንዲሁም በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት አመራሮች ሆነው በጥቃቱ የተሳተፉትና ኃላፊነታቸውን ያልተወጡን መንግስት በፍጥነት አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል፡፡

በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ዘር ተኮር ጥቃት ለማውገዝና ለማጋለጥ በመላው ዓለም ያሉ ኢትዮጵያዊያን በጋራ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልሎች ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ ማድረግ አለበት ብለዋል፡፡

ጥቃቱን የማስቆምም ሆነ ለተጎጂዎች አስቸኳይ ድጋፍ የማድረግ ኃላፊነት የመንግስት ቢሆንም ለህዝቦች ድምጽ በመሆን መንግስት ላይ ግፊት እንደሚያደርጉ ፓርቲዎች በጋራ አቋማቸውን አሳውቀዋል፡፡

በዋለልኝ አየለ – (ኢ.ፕ.ድ)


 • አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የምታስወጣ ከሆነ 200 ሺ የሚጠጉ ሴቶች ከሥራ ውጪ ይሆናሉ
  አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአጎዋ የምታስወጣ ከሆነ በፋብሪካዎች ተቀጥረው የሚሠሩ 200 ሺ የሚጠጉ ወጣት ሴቶችና እናቶችን ከሥራ ውጪ ይሆናሉ ሲሉ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ፡፡ የምጣኔ ሀብቱ ባለሙያ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት ከሰጠችው ከቀረጥ ነፃ ንግድ ማበረታቻ ዕድል (አጎዋ) ተጠቅመው በአሜሪካ ገበያ ምርታቸውን በሚያቀርቡ ፋብሪካዎችContinue Reading
 • አሜሪካ በትህነግ ላይ ቃታ ሳበች፤ የዜጎች ርብርብ ውጤት አስገኘ
  የጦርነቱ መነሻ ምክንያት የሰሜን ዕዝ ላይ ትህነግ በፈጸመ ጥቃት ሳቢያ መሆኑ ትህነግ ከኦነግ ሸኔ ጋር የፈጠረርውን ጥምረት የለቅድመ ሁኔታ እንዲያፈርስ ህጻናትን ለውትድርና መጠቀምን እንዲያቆም በወረራ ከያዛቸው የአማራ አካባቢዎች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለቆ እንዲወጣ በ H.Res.445 አዋጅ በአሜሪካ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውሳኔ አሳልፏል። የውሳኔው መግለጫContinue Reading
 • ኦፌኮ ብሔራዊ ውይይቱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪና ሸኔ እንዲካተቱበት ጠየቀ
  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ በቅርቡ ይካሄዳል የተባለው የብሄራዊ ውይይት የታጠቁ ሃይሎች ሙሉ በሙሉ እንዲካተቱበት ሲል ጠየቀ። ወንጀል የሰሩና በከፍተኛ ደረጃ የመከላከያ ሰራዊትን ያሳረዱ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲፈናቅሉና በጅምላ እንዲጨፈጨፉ፣ መጤ ተብለው እንዲሰደዱ አድርገዋል፣ አዘዋል፣ አመራር ሰጥተዋል በሚል ህግ ይጠይቃቸዋል የተባሉትን አስመልክቶ መግለጫው ስምና ድርጅት ጠቅሶ አልጠየቀም። ሙሉ መግለጫውን ያንብቡ የኢትዮጵያ ገዥ ፓርቲContinue Reading
 • የትግራይ ነጻ አውጪ ኩታበር ገባሁ አለ፤ መንግስት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ መበተኑና የተቀረውም እየታደነ መሆኑን ገለጸ
  ፎቶ የትግራይ ሃይሎች በወረሯቸው አካባቢዎች የደረሰ ዕህል በደቦ ሲያጭዱ የሚያሳይ፣ ምንጭ የደሴ ወጣቶች መቀለ የሚገኘው የጀርመን ድምጽ ዘጋቢ ትህነግ በሰጠው መግለጫ ኩታበርን መቆጣጠሩን እንደዘገበለት በመጥቀስ በፌስ ቡክ ገጹ አስፍሯል። የጀርመን ድምጽ የኢትዮጵያን መንግስት ዘገባ ለምን እንዳካተተ አላስታወቀም። ይሁን እንጂ መንግስት ማምሻውን ባሰራጨው መግለጫ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ በወሰዱትContinue Reading

Leave a Reply