ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ” አይቻለሁ” ሲል ራሱን ቄስ አድርጎ ምስክር የሆነው ሚካኤል በርሄን ህግ ፊት እንዲቀርብ ታዘዘ

የአክሱም ጽዮን ማርያም ቄስ በመምሰል ወይም ” ነኝ ” በማለት “በአክሱም ከተማ በክርስትያኖች ላይ ጭፍጨፋ ሲፈጸም በአይኔ አይቻለሁ” በማለት በታማኝ የዓይን ምስክርነት ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል መረጃ የሰጠው ሚካኤል በርሄ ወደ በህግ እንዲጠየቁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መመሪያ ሰጠ።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሰሜን፣ ደቡብ አሜሪካና የካእቢያን አገሮች ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አምሳደር ዶክትር ገበየሁ ጋንጋ ፊርማ የወጣው ደብዳቤ እዳለው ሚካኤል በርሄ የኢትዮጵያ ዜግነት ካለው በሰጥቶ መቀበል መርህ ተላልፎ እንዲሰጥ፣ የአሜሪካ ዜግነት ካለውና የአሜሪካ መንግስት እሱን አሳልፎ ለመስጠት ፈቅደኛ ካልሆነ ደግሞ በአገሪቱ ህግ እንዲጠየቅ የዲፕሎማሲ አግባብ ተጠቅሞ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚቻል ይገልጻል። አያይዞም የዓለም ዓቀፍ ህግ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል ስለ አካሄዱ የሰጠውን የህግ ሰነድ አያይዞ መላኩን አመላክቷል።

ሚካኤል ለአምነስቲ ምስክርነቱን ከሰጠና አምነስቲ መረጃውን ይፋ ካደረገ በሁዋላ፣ ምስክሩ ሃሰተኛ መሆኑና የቦስተን ነዋሪ እንደሆነ በመጥቀስ መንግስት ቢቃወምም አምነስቲ ይቅርታ እንዳልጠየቀ ይታወቃል።

ለመረጃ ያህል – ከአዲስ ዜና

ይህ ሰው የሚተውንበት ቪዲዮ ቀደሞ በዩቲዩብ ላይ የተለቀቀው በትግራይ ሚዲያ ሀውስ አማኻኝነት ነው። ትግራይ ሚዲያ ሀውስ በትግራይ ጉዳይ ላይ አተኩሮ የሚሰራ የኦንላየን ሚዲያ ሲሆን፣ ራሱን ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በማለት ይገልጻል።

ይህ ቪዲዮ ግን ፕሮዲውስ የተደረገው በመርሃዊ ዌልስ ቦግ እና ስታንድ ዊዝ ትግራይ የተሰኘው ቡድን መስራች በሆኑት ሉዋም ግደይ እና ራህዋ ግደይ ጋር በጥምረት ነው። በዚህ ቪዲዮ ላይ መርሃዊ እና ልዋም ዳይሬክተሮች መሆናቸውም ተጠቅሷል።

በዘጋቢ ፊልሙ ላይ እንደ ቄስ በመሆን የተወነው እና በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን መነጋገሪያ የሆነው ሚካኤል በርሄም በዘጋቢ ፊልሙ ላይ የተሳተፉ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ታከትቶ ይታያል።

መርሃዊ በኦንላየን ላይ በስፋት የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ነው። ከተለያዩ እንግዶች ጋር በመሆንም በየሳምንቱ በቀጥታ በትግራይ ስላለው ግጭት ይወያያል። በታህሳስ ወርም በርሄ ቋሚ እንግዳ በመሆንም ይቀርብ ነበር። መርሃዊ በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ዘጋቢ ፊልሙ የተዘጋጀው ቦስተን በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መሆኑን ጽፏል። ራሱንም ሲገልጽ የማህበረሰብ አደራጅ (community organizer)ብሎ ነው።

See also  ኢትዮጵያ የመላውን ጥቁር ሕዝብ ትግል እያካሄደች ነው

” ይህንን ነገር ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ሚካዔል በርሄ ቄስ አይደለም፤ እንደ ቄስ በመሆን የተወነ ነው” ሲል ስለ ሁኔታው ለቢቢሲ አብራርቷል።

“ሆሊውድ እንዲህ ዓይነት ነገሮችን ሁሌ ይሰራል። ሆሊውድ ስለ ኢየሱስ ክርስተስ ቪዲዮዎችን በመስራት መጠመዱን አታውቁምን? ኢየሱስ ክርስቶስን በመሆን ይተውናሉ ነገር ግን አይደሉም፣ ትወና ነው።”

ልዋም እንዳለችው ይህንን ቪዲዮ ያዘጋጁት ታሪካቸውን ለመናገር መንገድ ለሌላቸው ተጎጂዎች ድምጽ ለመሆን በማሰብ ነው። ቢሆንም ግን በመንግሥት እና በተቺዎች ግብረ መልስ መገረሟን አልሸሸገችም።

ከመንግሥት ወገን ይህንን አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች የተመለከቱት ዘጋቢ ፊልሙን ለማስተዋወቅ የተሰራውን አጭር ቪዲዮ ብቻ እንደሚሆን እንደምታምን አክላ ገልጻለች።

በተጨማሪም “ማስታወቂያውን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስናጋራ አርብ ለእይታ እንደሚበቃ ገልፀን ነበር፣ ስለዚህ በርካታ ሰዎች፣ የሚጠሉንን ሰዎች ጨምሮ፣ ምናልባት ሙሉ ቪዲዮው ያ ብቻ መስሏቸው ሊሆን ይችላል” ብላለች።

” የማይክን (ሚካኤል በርሄን) ስክሪንሾት በማምጣት ልክ ቦስተን እንደሚኖር ፣ ቄስ አለመሆኑን እንደደረሱበት አስመስለው አቀረቡ። በጣም አስቂኝ አስተያየቶች አሉ ልክ በጥይት ተመትቶ በሕይወት እንደተረፈ እና እንደሚናገር ያለ።”

ራህዋ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተጠቃሚዎች፣ እነርሱን በማካተት በርካታ አስተያየቶች እንደደረሳቸው ትገልፃለች። “ካነበብኳቸውና ካሳቁኝ መካከል ቄሱ ቆዳውን ለመንከባከብ የሚቀባው ምን እንደሆነ ትነግሩናላችሁ፤ የሚለው ነው ይህ በጣም ነው ያሳቀኝ” ትላለች። ሲል አዲስ ዜና ለጀርባ መረጃነት ጽፏል።

አዲስ ዜና የጠቀሰው የቢቢሲ ማስተባበያ

ከአምንስቲኢንተርናሽናል ጋር ግንኙነት ነበረው?

መርሃዊ የእነርሱ ዘጋቢ ፊልም የአምንስቲ ሪፖርት ከወጣበት ቀን ጋር መገጣጠሙ “ያጋጣሚ ጉዳይ ነው” ይላል።

” ወቅቱ በመግጠሙ ሰምሯል። ስለአክሱም ጭፍጨፋ ሪፖርት እንደሚወጣ አናውቅም ነበር ፤ እና ቪዲዮውን ለቅቀን ግንዛቤ እንፍጠር የሚለው ሃሳብ ብቻ ነው የነበረን” ሲል አክሏል።

የአምነስቲ ቃል አቀባይ ለቢቢሲ ከዘጋቢ ፊልሙ ጋር ምንም የሚያገናኛቸው ነገር አለመኖሩን አረጋግጠዋል።

ኮኖር ፎርቹን ከቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ “አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደ ቄስ በመሆን ከተወነው ግለሰብ ጋር ወይንም ደግሞ ቪዲዮውን ከሰሩት ግለሰቦች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም። በምንም ዓይነት ቪዲዮውን የተጠቀምንበት ወይንም ያጣቀስንበትም አጋጣሚ የለም” ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

See also  በሱዳን ዳርፉር የጦር ወንጀል ተጠርጣሪዎች በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው

“የማህበራዊ ሚዲያ ሴራ ተንታኞች ከእኛ ጋር አገናኝተው እስኪናገሩ ድረስ እና በሚገርም ሁኔታ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም ያንኑ ተቀብሎ እስኪያስተጋባ ድረስ ስለመኖሩም ምንም የምናውቀው ነገር አልነበረም”

ራህዋ ግደይ እነርሱ በዘጋቢ ፊልሞቻቸው ውስጥ ታሪካቸውን የተጠቀሙት ሰዎች ለአምንስቲም ምስክርነታቸውን ሰጥተው ሊሆን እንደሚችል ታምናለች። ነገር ግን ይህ በስራቸው ውስጥ ጥልቅ ጥናት ማካሄዳቸውን እንደሚያሳይ ገልጻለች።

“በእኛ ቪዲዮ ውስጥ ካለ ባለታሪክ ጋር ተመሳሳይ ታሪክ ያለው አይቻለሁ፤ ያ ማለት እኛ ጥናታችንን አካሂደናል። ቀድመን ነበር እንዲሁም በትግራይ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንዳለ እያንዳንዱን ነገር እየተከታተልን ነው” ስትል ታክላለች።

” አሜሪካ ስለምንኖር ምስክር መሆን አንችልም ነገር ግን ጥናት እንሰራለን፤ በስፍራው ካለ ሕዝባችን ጋር እጅና ጓንት ሆነን እንሰራለን” ትላለች

ልዋም ግደይ የእነርሱን ቪዲዮ ላይ ዘመቻ የተከፈተበት ምክንያት ትኩረትን ለማስቀየር እንደሆነ እንደምታምን ገልጻ ነገር ግን የበለጠ ግፊት ሰጥቶናል ብላለች።

“አሁን ወደፊት መገስገስ መቀጠል አለብን” ስትልም ሃሳቧን ትቋጫለች።

  • የተጠልፈቸው ጸጋ በላቸው ነጻ ሆነች፤ ጠላፊው አልተያዘም
    ወይዘሪት ፀጋ በላቸውን ከተጠርጣሪው ግለሰብ ማስጣል መቻሉን የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የሲዳማ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዮስ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በተደረገው የተቀናጀ የፀጥታ ኦፕሬሽን በተጠርጣሪው ግለሰብ የተጠለፈችውን ወይዘሪት ፀጋ በላቸውን ማስጣል መቻሉን ተናግረዋል። ግንቦት 15 ቀን 2015 ከመደበኛ ስራዋ ወጥታ ወደቤቷ ስታቀና ተጠርጣሪው ግለሰብContinue Reading
  • ፌደራል ፖሊስ ሆን ብለው ሐሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ አካላት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል አለ
    ሆን ብለው ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ሐሰተኛ መረጃ በሚያሰራጩ ግለሰቦች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ተቋሙ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ መንግስት ለህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈፀምበት የነበረውን ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራን መዝጋት መሆኑንና ይሄንን ተከትሎ በፖሊስ የወንጀል ምርመራ ስራ ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበትContinue Reading
  • ኢሰመኮ ሁለት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የጸጥታ ሃይሎችን ጨምሮ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታወቀ
    በሸገር ከተማ ከመስጊዶች መፍረስ ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን እና የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በተለይም በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድ ውስጥ እና በተወሰኑ አካባቢዎች በሸገር ከተማ በመንግሥት አካላት ከፈረሱ መስጊዶች ጉዳይ ጋር ተያይዞ የተነሱ ተቃውሞዎችን ተከትሎ የደረሰውን የሰዎች ሞት እና ጉዳቶችን በተመለከተContinue Reading
  • አዲስ አበባና በሸገር ከተሞች የፈረሱትን ቤቶችና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ ኢሰመኮ መገለጫ አወጣ
    በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተሞች እየተካሄደ ነው ባለው የቤት ፈረሳ እና የግዳጅ የማስነሳት ሂደት 111 ሺህ 811 ቤቶች መፍረሳቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) አስታወቀ። ኢሰመጉ ይህንን የገለጸው ከጥቅምት 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በጉዳዩ ላይ ያካሄደውን የምርመራ ሪፖርት ግንቦት 23/2015 ዓ.ም. ይፋ ባደረገበት ጊዜ ነው። ኮሚሽኑ ይህንን አሃዝ ይፋContinue Reading

Leave a Reply