ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 በሚያዙና እና በጽኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗ ተገለጸኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ አስታወቁ። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ምጣቱን አመለከቱ።

ዶክተር ሚዛን ኪሮስ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፣ ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በጽኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሀገሪቱ የኮቪድ -19 ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡

በሽታው ያለባቸው እና በጽኑ ህክምና ላይ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በየጊዜው እየጨመረ መምጣት የበሽታው ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ፡፡ ይህም የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቋሚ ነው ብለዋል፡፡

የምርመራ ውጤቶች ከቀን ቀን የሚሊያዩ ቢሆንም ባለፉት ሶስት ሳምንታት በተለይ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡን አመልክተው፣ በሚፈለገው ልክ ምርመራዎች እየተካሄዱ ባለመሆናቸው እንጂ በሌሎች ክልሎችም የበሸታው ስርጭት እየጨመረ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ምልክቶች እንዳሉ አመልክተዋል። የቫይረሱን አጠቃላይ ትክክለኛ ስርጭት ለማወቅም በቅርቡ ሰፊ ሀገራዊ ጥናት እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply