የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት በእስር ላይ የሚገኙ አመራሮች በመጪው ምርጫ በዕጩነት መወዳደር የለባቸውም ሲል ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት 1ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት አጸና። የተባበሩት ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ ላይ የተላለፈው ውሳኔም ተደገፈ፤

ውሳኔውን ያጸናው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት 1ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ሲሆን ምርጫ ቦርዱ የሰጠውን ውሳኔ በሙሉ ድምጽ ማጽናቱን ዛሬ ከሰዓት ተገልጿል።የባልደራስ ፓርቲ ሊቀመንበሩን እስክንድር ነጋን፤ ስንታየሁ ቸኮል እና ቀለብ ስዩምን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ አራት አመራሮች ለመጪው ምርጫ በዕጩነት ይቅረቡልኝ ሲል ያቀረበው ጥያቄ በኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ በኩል ተቀባይነት ሳይገኝ መቅረቱን ተከትሎ ፓርቲው ይግባኝ ብሏል።

በመጋቢት ወር ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የ1ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ፓርቲው ይግባኝ ማለቱ ተክትሎ ምርጫ ቦርዱም ምላሽ ሰጥቶበታል። ይህ ዓይነቱ አሰራር የባልደራስ አመራሮቹ ለምርጫ በዕጩነት ቢመዘገቡ በቀጥታ ያለመከሰስ መብት ስለሚኖራቸው እና በእስር ላይ የሚገኙት አመራሮቹ ለምርጫ እንዳይመዘገቡ የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ እና የምርጫ ቦርድ መመሪያ ክልከላ ጥሏል፡፡

በዚሀም መሰረት በእጩነት እንዳይመዘገቡ ተደርጓል ሲል ምላሽ ሰጥቶ ነበር፤ የፓርቲው ይግባኝ እና እና የምርጫ ቦርዱን ምላሽ አግባብነት አለው ወይስ የለውም የሚለውን መከራከሪያ ነጥብ የመረመረው ችሎቱ በአብላጫ ደምጽ የምርጫ ቦርዱ ውሳኔ አግባብነት አለው ሲል አጽንቶታል። በሌላ በኩል በዚሁ ፍርድ ቤት 5ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት የተባበሩት ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲን ማመልከቻ ላይ እና የምርጫ ቦርድ ምላሽ ላይ ፍርድቤቱ እልባት ሰጥቷል።

የተባበሩት ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲው ከአባልነት ምዝገባ መሰረዜ አግባብ አይደለም ሲል ለፍርድቤቱ ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ ምርጫ ቦርድ ከአባልነት ከምዝገባ የሰረዝኩት የናሙና ማጣራት አድርጌ ፓርቲው መስፈርቱን ያላሟላና ከ23 ከመቶ በታች ሆኖ በማግኘቴ ከአባልነት ሰርዤዋለሁ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ፍርድቤቱም የፓርቲው ይግባኝ የመደመጥ መብቱ አግባብ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን እና መረጃ አሰባሰቡስ ተገቢነት አለው ወይ የሚለውን አጣርቶና የማስረጃ ምዘና አደርጎ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ተገቢነት አለው ሲል የቦርዱን የአባልነት ስረዛ አግባበነት አለው ሲል በሙሉ ድምጽ አጽንቶታል።

በታሪክ አዱኛ – መነሻ ዜና ፋና

Leave a Reply