“ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

በዋሉበት የማያድሩ፣ በየጫካው የሚሹለከለኩ፣ ድርጅታዊ ህልውናቸው ያከተመ፣ ነብሳቸውን የሚወዱ፣ መዋቅራቸው የፈራረሰ፣ አገር ለማተራመስ የሚጠቀሙበትን ኢኮኖሚ ያጡ፣ በሌብነት የተሰማሩ፣ ከጁንታነት ወርደው ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ ሲሉ ነው የገለጿቸው። በጥቅሉ ”

ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነና በህግ የሚፈለጉት እየተያዙ ነው” ነው ያሉት። በግል በደረሱበት ያገኙትን እያፈኑ ለዝርፊያ የሚጠቀሙ ደመኞች፣ ወጣቶችን በማስገደድ ሲደመሰስ የሚተካ፣ ሲስተሙ የፈረሰ፣ ግዳጅ መስጠት የማይችል፣ ግዳጅም የሚቀበል ሃይል የሌለው፣ የጥቂት ተስፈኛና ነብሳቸው ወዳድ ግለሰቦች ሲሉ ነው ቀሪዎቹን ጥቂት የገለጿቸው።

ከሶስት ደራሲዎቻቸው በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን በአክተሮቻቸው አማካይነት ገጣጥመው መከላከያ ሰራዊት ነጹሃንን እንደገደለ በማስመስለ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን በማይመጥን እውቀት ዓለምን እያታለሉ፣ ሚዲያዎቹም ጥቅመኛ ስለሆኑ ሃሰት መሆኑንን ቢያውቁም ሆን ብለው ይህንኑ ድርሰት ሲያሰራጩ መክረማቸውን አመላክተዋል።

ድርሰቱንም መከላከያ ሰራዊት “በትግራይ ክልል ንጹሃንን ፈጅቷል ” በሚል በጁንታው ተላላኪዎች የሚናፈሰው የተቀነባበረ የሃሰት ወሬ ብለውታል። ሰራዊቱ ቀሪ ርዝራዦች በማደን ይዞ ለህግ ለማቅረብ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑንን አካተው ገልጸዋል። ኢዜአ የሚከተለውን ዘግቧል።

ይህንኑ የፈጠራ ወሬ በሚመለከት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀው ቪድዮም በጁንታው ተላላኪዎች በውሸት ተቀናብሮ ህዝብ ለማደናገር የተሰራ መሆኑ ተገልጿል።የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህንን ያብራሩት።

በመግለጫቸውም የመከላከያ ሰራዊቱ ባካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ ጽንፈኛውን የህወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደመሰሱን ገልጸዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም አንዳንድ የጁንታው ርዝራዦች የሸፋታነትን ባህሪ ለመላበስ በጫካ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መኖራቸውን ጠቅሰዋል።

በዚህም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በአሳቻ ስፍራ ላይ እየተገኙ በህዝቡ ላይ ዘረፋ፣ እንግልትና ግዲያ እየፈፀሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።የጁንታው ርዝራዦች ሰላማዊ ሰዎችን በመጨፍጨፍ አገርና ህዝብን እየጠበቀ ባለው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተፈፀመ ለማስመሰል እየጣሩ መሆኑን አብራርትዋል።የፅንፈኛ ቡድኑ ተላላኪዎች በጁንታው ታጣቂ ሃይል የተፈፀመውን ግዲያ የምስል ቅንብር በመስራት የሀገር መከላከያ ሰራዊት የመፈፀመው አስመስለው ማሰራጨታቸውን ሜጀር ጀነራል መሀመድ አስታውስዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በከፍተኛ ስነ ምግባር የተገነባ ህዝባዊ መሰረት ያለው የህዝብ ልጅ በመሆኑ ህዝብን የሚጎዳ ተግባር አይፈፅምም ነው ያሉት።የህወሃት ጁንታ ዘራፊ ቡድን ጫካ ውስጥ ሆኖ ትርክቶችን በማስተላላፍ በህይወት እንዳለ ለማስመሰል ልዩ ልዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛልም ብለዋል።በውጭ ሃይሎች ተቀባይነትን አግኝተናል እያሉ በማደናገር ወጣቶችን ለእኩይ አላማቸው ለማሰለፍ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱን አብራርትዋል።

በተለያዩ ቦታዎች መሽጎ የሚንቀሳቀሰው ቀሪ የጁንታው ቡድን የሎጀስቲክ እና ሌሎች መሰረታዊ አቅርቦቶች ስለሌላቸው ህዝቡን በማስፈራራትና በመዝረፍ ህይወታቸውን ለማቆት እየጣሩ መሆኑንም ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተናግረዋል።

በአሁኑ ጊዜም ቀሪ የጁንታው ርዝራዥ በትግራይ ክልል የህዝብ ተቀባይነት ስለሌለው በዜጎች ላይ የዘረፋና ግዲያ ወንጀሉን ቀጥሏል ብለዋል።በክልሉ ቀሪ የጁንታውን ርዝራዦች ለማደን በሚደረገው ጥረት ህዝቡ እስካሁን ለሰራዊቱ ያደረገውን ድጋፍ ያደነቁት ሜጀር ጀነራል መሀመድ በቀጣይም እንዲጠናከር ጠይቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።መከላከያ ሰራዊት ቀሪ ርዝራዦች በማደን ይዞ ለህግ ለማቅረብ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ጀነራሉ ይፋ አያድርጉትና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በተለያዩ ግንባሮች በተደረገ ማጥቃትና ከበባ በሺህ የሚቆጠሩ ሲማረኩ፣ በሺህ የሚቆጠሩ ተገድለዋል። የመከላከያ መረጃ የሚያገኙ በግልጽ እንደገለጹት ጀነራሎች ተገድላለዋል። መኮንኖች ወደው እጃቸውን ሰጥተዋል።


Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply