ግብፅና ሱዳንን ፀጥ የሚያሰኘው የኢትዮጵያውያ ጀግና – ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው

Se kildebildet

በህዳሴ ግድብ በስሜት ጋልበው” ኡኡ “የሚሉትን ግብፅና ሱዳንን ፀጥ የሚያሰኘው ያልተዘመረለት ጀግና – ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው

የዶክትሬት ማዕረግ ያላቸው ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን አሉ ። ግማሹ ሀገሩን እረስቶ በብሄር ተቧድኖ አንደ አፍላ ጎረምሳ ሲሰዳደብ ይውላል። ከፊሉ ምንም ሳይሰራበት ዶክትሬት ዲግሪ አለኝ እያለ ሲፎክር ይውላል። ግማሹ የተሻለ ብር ለማግኘት በNGO ውስጥ ተሰግስጎ አንድ ትምህርቱን አንኳን በቅጡ ያልጨረሰ ፈረንጅ ወረቀት ኮፒ አድርግ ፣የሚረዳ ሰው ቁጥር መዝግበህ ስጠኝ ሲለው ይውላል።
የዚህ አይነት ሰው በጥሩ መኪና ፣በጥሩ ቤት ስለታጀበ ይሄን ምስኪን ዶክተር ከእወቀቱ በታች አየሰራ እውቀቱ ባክኖ እየኖረ መሆኑን ብዙ ሰው አይገነዘብም ።
እንዲህ መሆንስ በእርግጥ የሚገርም አይደለም ።አንደኛ ባለ ደሀ ሀገር ብዙዎቻችን ምንደክመው መሰረታዊ ፍላጎታችንን ለሟሟላት ነው ።የተመረቅንበት ነገር ተግባር ላይ ዋለ አልዋለ ብዙም ግድ የለንም ።
ለእንቁ እንጂነራችን ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው ይሄ ብዙ ቦታ የለውም ። የቀድሞ የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ዲን ትልቅ ዶላር ማግኘት የሚችላባቸውን አለም አቀፍ ተቋማትን ትቶ ከመሞቴ በፊት በህዳሴ ግድብ አንድ ነገር ለሀገሬ ልስራ ብሎ በየስብሰባው የግብፅና የሱዳን ባለስልጣናትን ” ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ግድብ ሰርታ የማደግ መብቷን ” ልትነፍጓት አትችሉም በማለት ሽንጡን ገትሮ የሚከራከር ሰው ነው ።

ስለሺ በአፍሪካ ኦኮኖሚክ ኮሚሽን ፣ በተባበሩት መንግስታት ደርጅት ውሃና የውሃ ኤሌትሪክ ሀይልን በተመለከተ ብዙ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳትፏል ። በመሰል ጉዳዮች ላይ ከ30 አመት በላይ ልምድ ያለው ኢትዮጵያ አንደ እንቁ የምታየው ምሁር ነው።
ስለሺ ስለ ውሃ የለ እውቀት ይገርምካል ። ቀን ሙሉ ቢያወራልክ አይሰለችህም። ስለ ኢትዮጵያ ፣ስለ አፍሪቃ፣ስለ አለም ወንዞች ታሪካዊ ዳራቸው ፣ሰለ ሚሰጡት ጥቅም በውስጣቸው ስላለው የፖለቲካ ሴራ ያስረዳሀል።

ዶ/ር ስለሺ ቆቅ የሆነ ሰው ።አስቀድሞ ነገሮችን የሚረዳ አስቀድሞ ነገሮችን የሚተነብይ ሰው ነው። የህዳሴን ግድብ አንድ ወላጅ ልጆቹን ከሚከታተል በላይ ይከታተለዋል ።
በኢትዮጰያዊነት የሚኮራ ሀገሩን ከልቡ እየሰራ የሚያገለግል ሰው ነው።
በእያንዳንዱ የህዳሴ ግድብ ድርድር ግብፆች ምን ይዘው ሊከራከሩ አንደሚችሉ ይገምታል ። ብዙን ግዜ የግብፅ ተደራዳሪዎች አንድ የተለመደ ተግባር አላቸው ።የድርድሩን አጀንዳ በመተው በሌላ ጉዳይ ጉንጭ አልፋ ክርክር እየጮሁ አጀንዳ ማስቀየስ ።ስለሺ ይሄን ስለሚያውቅ ከእነሱ እኩል አየጮኸ “በዚህ ጉዳይ ለመወያየት አልተቀጣጠርንም ” በማለት ይናገራል ።
በስብሰባው ላይ የሚሰማው የግብፃዊያን ጩኸትና” እንከሳለን “የሚል ማስፈራሪያ ከቁብ አይቆጥረውም ። እንደውም አንዳንዴ በቁጣ ሲናገር የግብፅም የሱዳንም ባለስልጣናት ሲደነግጡ ይታያል።
አብዛኞቻችን በፌስ ቡክ በምንጠመድበት ሰአት ስለሺ ስለ አባይ ግድብ ቀጣይ ድርድር እቅድ ያወጣል ።ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያለውን ነገር ያስረዳል።ግድቡ አልቆ ሙሉ ለሙሉ ስራ የሚጀመርበትን ቀን አንዲት አርጉዝ ልጇን ወልዳ ለማየት አንደምትናፍቀው ይናፍቃል።

ሰውዬው ብልጥ ነው ። ይኸው በድርድር መሀል የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ሙሌት ላይ አንዲደርስ አድርጎታል ። ብዙዎቻችን ሳይገባን ግድቡ ተሽጧል ብለን ግን ለፍለፈናል።

ግብፆች በህዳሴ ግድብ ሙሌት ሂደት ላይ አሜሪካን እና አለም ባንክን ይዘው ኡኡ ሲሉ ” ለግድባችን ሙሌት የማንንም አገር ፍቃድ ማግኘት “አያስፈልገንም ብሎ ኢትዮጵያን ያኮራ ግብፅና ሱዳንን በህዳሴ ግድብ ላይ ከኢትዮጵያ ጋር ተስማምቶ ከመስራት ውጪ ምን አማራጭ እንደሌለ ያሳያ ብልህ ሰው ነው።ያልተዘመረለት ጀግና – ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው

Via Tesfaye Getenet

Leave a Reply