370 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ- ትጥቅና ስንቅ ሲያቀርቡ የነበሩ 183 የጁንታው የህወሓት አባላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል

ባለፈዉ 1 ወር ኦነግ ሸኔ ላይ በተወሰደ እርምጃ 370 የኦነግ ሸኔ አባላት ተደመሰሱ

ኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ባለፈዉ አንድ ወር ኦነግ ሸኔ ላይ ሲወስድ በነበረዉ እርምጃ 370 የኦነግ ሸኔ አባላት መደምሰሳቸው ተገለፀ፡፡ እንዲሁም 176 የቡድኑ አባላት ሲማረኩ፤ 154 በህዝቡ መያዛቸዉን የኦሮሚያ ፖሊስ ህዝብ ግንኙነት አስታዉቋል፡፡

በዚሁ ወቅት ትጥቅና ስንቅ ለሽፍታዉ ሲያቀርቡ የነበሩ 183 የጁንታው የህወሓት አባላትም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በሎጂስቲክ በኩል 4 ብሬኖችን ጨምሮ 1 ሺህ 585 ጠመንጃዎች፣ 10 ሺህ 902 ጥይቶች፣ 605 የቁም ከብቶች፣ 353 ፍየሎች፣ 54 የጋማ ከብቶች፣ 48 ግመሎች፣ 682 ሺህ 680 ብር እና 204 ሺህ 400 የሀሰት ገንዘብ መያዙን ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

FBC

Leave a Reply