አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ – ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

ትህነግ አስከሬኖች ከተቀበሩበት እየወጡ በአንድ ጉድጓድ እንዲቀበሩ ማዘዙን እንደሰሙ የአክሱም ነዋሪ የነበሩና አሁንም ቤተሰቦቻቸው እዛ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ለኢትዮ 12 አስታወቁ። ሜ/ጄ ክንዱ ቀደም ሲል “ ጁንታ” ሲሉ የጠሩት አካል ተመሳሳይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ያናገራቸው የአክሱም ተወላጅ አዲስ አበባ የሚኖሩ ሲሆን ቤተሰቦችና በርካታ ወዳጆች አክሱምን ጨምሮ የተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች አሉዋቸው። አዲስ አበባም ቢሆን በርካታ የትግራይ ልጆች ወዳጆች አላቸው። የገናኛሉ። የደዋወላሉ። መረጃ ይቀያየራሉ።

https://fb.watch/4MumMPwlZE/

እኙህ ሴት እንዳሉት ከሶስት ሳምንት በፊት “ አስከሬን እንዲለቀም ተብሏል” በሚል ከበረሃ የወረደ ትዕዛዝ እንዳለ አክሱም ከሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው ሰምተዋል። አዲስ አበባ ካሉ ወዳጆቻቸው ጋር በጭንቀት ሲነጋገሩ መመሪያው በየአቅጣጫው እንዲፈጸም መታዘዙን እንደሰሙ ተረድተዋል።

“ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ እምዬ” የሚሉት እናት አስከሬን እየተሰባሰበ አንድ ቦታ እንዲቀበር የታዘዘበትን ምክንያት ግን ለይተው እንደማያውቁ ገልጸዋል። መፍትሄው ግራ ስለገባቸው ሌት ተቀን እንደሚጸልዩ፣ በሚሰሙት በርካታ ጉድ መሰላቸታቸውና አልሰማም ቢሉ እንኳን እንደማይችሉ ገልጸዋል።

ሜ/ጄ ክንዱ በሰጡት መግለጫ ተስፋ የቆረጠው፣ ካሁን በሁዋላ ተዋግቶ የማሸነፊያ ምክንያትም ሆነ አቅም የሌለው፣ ከሁለት መቶ በላይ ታንክ ያሰለፈ፣ አጭርና መካከለኛ ሮኬቶች የታጠቀ፣ መድፋና ዘጠና ሺህ የሚገመት ስራ ላይ የነበረ ሰራዊት ያሰለፈ፣ ከሃጂዎችን ጨምሮ በጡረታ የተገለሉ ያካተተ ሃይል ይዞ ሶስት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዳይሆን የሆነው ሃይል አስከሬን እንዲለቀምና አንድ ጉድጓድ እንዲገባ ማዘዙን አመልክተዋል።

ግፍ የማይጠግብ፣ እሱ ከሚፈልገው በስተቀር ሌላ ምንም የማይታየው፣ እሱ የሚፈልገውን ካጣ ትግራይም ሆነች ኢትዮጵያ ምኑም የማይመስሉት ስልጣንና ጥቅም ያሰከረው ቡድን በየአካባቢው የተቀበሩ አስከሬኖች እንዲለቀሙና በአንድ ጉድጓድ እንዲለቀሙ ያዘዘው ለሁለት ጥቅም እንደሆነ ሜ/ጄ ክንዱ አስረድተዋል።

“ከኢትዮጵያ መከላከያም ሆነ ከሽፍታው ሃይል የወደቁትንና መከላከያ ማንነት ሳይለይ በክብር የቀበራቸውን አጽማቸውን በማውጣት አንድ ላይ እንዲቀበሩ አዟል” ሲሉ የትህነግን ሴራ የገለጹት ጄነራሉ፣ መረጃውን ሙሉ በሙሉ ይፋ ያደረጉት እድል አግኝተው እጅ የሰጡና የተማረኩ ወገኖች እንደሆኑ ገልጸዋል።

በየአካባቢው ሰፋፊ የመቃብር ቦታ በማዘጋጀት ወደፊት ወጣቶች እሱን እያዩ እንዲቀሰቀሱበትና ወደ በረሃ እንዲገቡ፣ ከዛ በዘለለ ደግሞ መከላከያ በጅምላ ጭፍጨፋ እንዳካሄደ በማስመሰል የጅምላ መቃብሮችን በዘጋቢ/ ዶክመንታሪ ፊልም በማዘጋጀት ለዓለም ለማሳየት ታልሞ መመሪያው መውረዱን ነው ምርኮኞቹ ይፋ ያደረጉት።

“ ስም መጥራት ሙያዊ ስነ ምግባር አይደለም” በማለት ሜ/ጄ ክንዱ ሲናገሩ የጁንታው መሪዎች ባህሪያቸው ሁሉ ክፉ ተግባር በመፈጸም እንደሚገለጽ አመልክተዋል። አያይዘውም እንደዚህ ዓይነቱን ትዕዛዝ የሚሰጡትን በሬዲዮም እንደሚሰሟቸው አመልክተዋል።

የትግራይ ህዝብ ጨዋ በመሆኑ በአስከሬን ለሚቆመር ቁማርና በሙታን ለሚሰራ የፖለቲካ ንግድ “ አይሆንም” ማለት እንዳለበት ገልጸዋል። አያይዘውም የትግራይ ህዝብ ወደ ሰላማዊ ህይወቱ ሊመለስ እንደሚገባው መክረዋል።

እጅ ለሚሰጡ ጁንታው እንደሚለው ሳይሆን አስፈላጊው እንክብካቤ እንደሚደረግ ሜ/ጄ ክንዱ ተናግረዋል። ጁንታው ከተማረኩ እንደሚገደሉ የሚናገረውና የሚቀሰቅሰው ሁሉ ፍጹም ስህተት መሆኑንን ገልጸዋል። “ እንኳን ወገናችን በፖለትካ ሰካራሞች ተወናብዶ ጫካ የወረደውን፣ የአልሸባብ ሰራዊት ሲማረክ አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ የተመሰከረልን ነን” ሲሉ ቤተሰብም ሆነ በግዳጅ ሳያውቅ የተነዳው ወጣት እጁን በሰላም እንዲሰጥ ጥሪ አሰምተዋል።

እግረመንገዳቸውንም ቀደም ሲል ግፍ የተፈጸመበት ሰራዊት ዘንድ “ ገለውናል” የሚል ቁጣ እንደነበር ያልሸሸጉት ሜ/ጄ ክንዱ፣ በቂ ውይይት፣ ተግሳጽና እርምጃ ተወስዶ ያ ስሜት መወገዱን አውስተዋል።

“ መጣን” እያሉ አጉል ፕሮፓጋንዳ የሚያሰሙትን ሽርፍራፊ የጁንታው አካላት የተመቱበትን ከፍተኛ አመራሮች “ አንገት እየቆረጠ በፎርማሊን እያደረቀ ይሰውራል” ሲሉ “ እንዲህ ያለው ለራሱ ወገኖች እንኳን ሃዘኔታ የሌለውን ክፉ አትመኑ” ሲሉ እንኳን ሊመጣ የራሱን ሰዎች እንገት የሚቀላ፣ ተስፋ የቆረጠ፣ ማንም ይደፍረዋል ተብሎ በማይታመነው የተከዜ በረሃ በደንብ የተመታና ተበታትኖ ስንዴ የሚለምን ሃይል መሆኑንን አመልከተዋል።

“ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ ሲሉ ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ መናገራቸው ይታወሳል። እሳቸው እንዳሉት ይህ “ ጁንታ “ መባል እንኳን የማይችለው ሃይል በዋለበት የማያድር ሽፍታ ነው።

ሜጀር ጀነራል ክንዱ እንዳሉት ይህ አሁን አጽም እየተቆፈረ ለፖለቲካ ቁማር እንዲውል ያዘዘው ክፍል ጥቅሙ የቀራበት፣ ሲሆን ያጀቡት ደግሞ በዩሉንታ “ ምን እባላለሁ” በሚል የገቡ፣ ላለፉት 20 ዓመታት በመከላከያ ሰራዊት ጥበቃ አንድም ጥይት ሳይሰማ ያደገና ጠላት ተፈጥሮለት ሲሰበክ የኖረ ወጣት ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻዎችና ጡረተኞች  ናቸው። እነዚህ ሃይላት ቀሪ ህይወታቸውን በስለማ እንዲኖሩ ደጋግመው ጥሪ አቅርበዋል። መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቆና ከፈተኛ ሰራዊት ገንብቶ ተረት ከሆነ ሃይክ ተስፋ ሰላምይተበቅ በስብከት ከመነዳት ቀሪው የትግራይ ህዝብ ወደ መደበኛ ህይወቱ እንዲመለስ በንግግራቸው መጨረሻ አመልክተዋል።


 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
  ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸዉና ከምትከበርባቸዉ ሀገራዊ ልዩ እሴቶቿ ዉስጥ አንዱ የዘርፈ ብዙ ልዩነቶች የመቻቻል ምድር መሆኗ ሲሆን ህዝቦቿ በፈረሃ አምላክ የሚመሩ ናቸዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን የሀይማኖት ብዝሃነትን […]
 • Ethiopia tows 2.3bln USD remittance a year less
  ADDIS ABABA – Ethiopian Diaspora Agency disclosed that the country has secured 2.3 billion USD in remittance from the Diaspora over the past eight months. Agency Director-General Selamawit Dawit told the […]
 • Ethiopia, World Bank seal 200 mln USD loan agreement
  ADDIS ABABA—Ethiopia and World Bank signed 200 million USD loan agreements to support the implementation of Digital Foundation project. As to the information obtained from the Ministry of Finance and […]
 • የቆዳ ዋጋ መውደቅና አገራዊ ኪሳራው
  ድሮ ድሮ በደጋጎቹ ዘመን “ጮሌዎቹ” በግ ከአርሶ አደሩ በስሙኒ ገዝተው ቆዳውን መልሰው በስሙኒ በመሸጥ ስጋውን በነጻ “እንክት” አድረው ይበሉ ነበር ይባላል። ታዲያ የስጋን ያህል ዋጋ ያወጣ የነበረ የቆዳ ዋጋ ከቅርብ […]

Categories: NEWS

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s