“የመተከል ዞን ግብረሃይል እስካሁን ውጤታማ ተግባራትን ቢያከናውንም አሁንም ቀሪ ስራዎች ይጠበቁበታል”

በመተከል ዞን የተቋቋመው የተቀናጀ ግብረሃይል እስካሁን ውጤታማ ተግባራትን ቢያከናውንም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቀሪ ስራዎች እንደሚጠበቁበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚኒሰትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎችን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል የመንግስት የስራ ሃለፊዎችን ያካተተ ልኡክ በመተከል ዞን የኮማንድ ፖስቱን ክንውን ገምግሟል።

በቆይታቸው የኮማንድ ፖስቱን ስራዎች ከመገምገም በተጨማሪ ከተለያዩ አመራሮች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና የዞኑ ነዋሪዎች ጋር ጠቃሚ ውይይቶች ማካሄዳቸውን አቶ ገዱ ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመው ግብረ ሃይል የዜጎችን ሞት፣ መፈናቀልና ንብረት ውድመት በማስቆም ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ማስፈን ቀዳሚ ተልዕኮው መሆኑንም አንስተዋል።

ለዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና ንብረት ውድመት ምክንያት የሆነው የታጠቀ ሽፍታ ላይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ረገድ ግብረሃይሉ ጥሩ ስራ ማከናወኑንም አቶ ገዱ ገልጸዋል።

ከታቀደው ግብ አኳያ ግብረ ሃይሉ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን የገለጹት አቶ ገዱ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ቀሪ ስራዎች ይጠበቁበታል ብለዋል።

በሌላ በኩል በሰላማዊ አማራጭ ችግሩን ለመፍታት በሀገር ሽማግሌዎች ጥረት ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ የተሰራው ስራም ትልቅ ግምት የሚሰጠው መሆኑን አንስተዋል።

የታጠቀውን ሃይል በድርድር ወደ ሰላም እንዲገባ በማግባባት ከ3 ሺህ 400 በላይ ታጣቂዎች እንደተመለሱም አስታውሰዋል።

ከዞን እስከ ቀበሌ ፈርሶ የነበረውን የመንግስት መዋቅር አዲስ አደረጃጅት መፈጠርና ህብረተሰቡ ራሱን በራሱ እንዲጠብቅ ሚሊሻ በማሰልጠን ጭምር የተከናወነው ስራም የኮማንድ ፖስቱ የጥረት ውጤት መሆኑን አቶ ገዱ ገልጸዋል።

ያም ሆኖ ታጣቂውን ሃይል ትጥቅ በማስፈታትና መልሶ በማቋቋም እንዲሁም የሰለጠነውን ሚሊሻ መዋቅሩን በማጠናከርና ትጥቅ በማሟላት ውስንነቶች አሉ ብለዋል።

በመተከል ንጹሃን ዜጎች በከፍተኛ ደረጃ የጉዳትና የመፈናቀል አደጋ ደርሶባቸዋል ያሉት አቶ ገዱ፣ የተመሰቃቀለውን አካባቢ ወደ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ማምጣት የግብረሃይሉ ያደሩ ቀሪ ስራዎች ናቸው ብለዋል።

እንደ አጠቃላይ የመተከል ዞንን መከላከያ ሰራዊት ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ወደ ቀደመ ሰላምና መረጋጋት እንዲመለስ ያደረገው ጥረት ትልቅ ዋጋ እንደሚሰጠው አቶ ገዱ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዞኑ ወደ ሰላም የተመለሰውን ሃይል አሰልጥኖ በፍጥነት ወደ ሰላማዊ ኑሮው እንዲገባ የማቋቋም እንዲሁም ትጥቅ ባለመፍታት የሸፈተውን ሃይል የማደን ስራው በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

የመተከል ሰላምና መረጋጋት በመከላከያ ሰራዊት ጥረት ብቻ እውን ስለማይሆን ህብረተሰቡ፣ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

በዚህ ዙሪያ በተለይ የአማራ ክልል ከቤኑሻንጉል ጉሙዝ ክልልና ከኮማንድ ፖስቱ ጋር አብሮ መስራት ይገባዋልም ብለዋል።

የጉሙዝም ሆነ የሌላው ማህበረሰብ የጋራ ጠላት የሆነው የታጠቀ ሽፍታ እንጂ የህዝቡ አብሮነትና የጋራ እሴት እንዳለ መሆኑን መገንዘብም ይገባል ብለዋል አቶ ገዱ።


(ኢ ፕ ድ)

Related posts:

መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ
ፊንላንድ 3.6 ሚሊዮን ሕዝብ የሚይዙ ዋሻዎች አዘጋጀች - ለኢትዮጵያውያን ጠቃሚ የጥንቃቄ መረጃ
"አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንና የጥፋት ኃይል ዳግም ከሞከረ የማያዳግም ቅጣት ይጠብቀዋልʺ
ሻዕቢያና ትህነግ - ሰሞኑን ይህ ሆነ
ትህነግ ጦርነት እንደሚከፍት ይፋ አደረገ፤ አማራ ክልል "ለክተት ተዘጋጁ"አለ፤ መከላከያ በተጠንቀቅ ላይ ነው
ወልቃይት "የወር ስንቅህን አዘጋጅተህ ለክትተ ጥሪ ተዘጋጅ”
በሶማሊያ በሚንቀሳቀሰው አልሸባብ የሽብር ተልዕኮ የተሰጣቸው ስድስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አማራ ክልል ትህነግ ዳግም ጦርነት ስላወጀ የ"ዝግጁነትን" አዋጅ አወጣ
ኡጋንዳ ፀረ-ኢትዮጵያ ለሆኑ ሃይሎች ከለላና ድጋፍ እንደማታደርግ አስታወቀች፤ የሚወራው ሃሰት ነው አለች
በአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ
በዳኝነት ስርአቱ ላይ የሚታዩ የሙስና ተግባራትን ለመከላከል የሚያስችል ስትራቴጂ ይፋ ሆነ

Leave a Reply