ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የጁንታውን ሃይል በከፍተኛ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቁ። ” ጁንታው ካሁን በኋላ ሰራዊትና ጠባቂ ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም” ሲሉ ተናግረዋል።

May be an image of 1 person and standing
ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ

በትግራይ ክልል በስምንት አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረው የጁንታው ቡድን ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ያመለከቱት ሌተናል ጀነራል ባጫ፣ የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ቴኮሎጂ ለመጠቀም የተገደደው ጁንታው መደበኛ ዋጋ የመቋቋም አቅም ስላለው ሳይሆን የሰው ሃይል ኪሳራ እንዳይኖር ለማድረግ ታቅዶ መሆኑንን አመልክተዋል።

ያለፈው ሳምንት የሰራዊቱ እንቅስቃሴንና የግዳጅ አፈጻጸም አስመልክተው ጥቅል መረጃ የሰጡት ጀነራሉ፣ የተንጠባተበ ሃይል ሲጠቀምባቸው የነበሩ ትንንሽ ማሰልጠኛዎች እና የጁንታው መሪዎች ጠባቂዎችን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፣ እንደተመቱና በማያገገሙበት መልኩ መደምሰሳቸውን አስታውቀዋል። ስም ዘርዝረው ግን አለተናገሩም።

“ጁንታው ከአሁን በኋላ ሌላ ሰራዊትና ጠባቂ ይዞ ሊቀጥል አይችልም” ሲሉ ስለ ተዋጊነት አቅሙ ያብራሩት ጀነራሉ፣ ይህንን ለማድረግ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን አገልግሎት ላይ መዋሉን አመልክተው በዚህም ስኬታማ ውጤትና የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን አስረድተዋል። በወገን ሰራዊት ላይ ኪሳራ እንዳልደረሰም ገልጸዋል።

“ጁንታው በስምንት አካባቢዎች ለመቆየት የመረጠው መቐለና ወደ መቐለ የሚወስዱ መንዶችን በመዝጋት የህብረተሰቡን የዕለት ተዕለት ደራሽ ዕርዳታ እና አገልግሎት ለማጨናገፍ ነበር ” ሲሉ ጀነራል ባጫ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ዘመናዊ የጦርነት ግብአቶችን በመጠቀም አስፈላጊ ምላሽ ተሰጥቷል።

ዛሬ ጁንታው ብቻውን መቅረቱን ያመከቱት ጀነራል ባጫ፣ በሱዳን በኩል ለማምለጥ ይችላሉ በሚል የሚናፈስ ስጋት መኖሩን አንስተው ማብራሪያ አቅርበዋል። በማብራሪያቸው እቅዱንና የዕቅዱን ዓይነት፣ እንዲሁም የቦታ ስም ጠቅሰው ባይናገሩም ” መከለከያ ሰራዊታችን በሁሉም አቅጣጫ በቂ ዝግጅት አድርጓል” ብለዋል። አያይዘውም “መከላከያ ሰራዊታችን በሁሉም አቅጣጫ በቂ ዝግጅት ያደረገ በመሆኑ ጁንታው ሱዳን እንደ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን እንደ መቐለም እንዲርቀው እናደርገዋለን” ሲሉ ስጋት እንደሌለና በበቂ ጥናትና ዝግጅት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

ከሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በስምንት ግንባሮች የጅንታውን ሃይል እርምጃ እየተወሰደ አንደሆነ ለህዝብ ይፋ አድረገው ነበር። የደመና ማዝነብ ሙከራ መሳካቱን ይፋ ባደረጉበት ንግግራቸው አያይዘው ጁንታው በየአቅጣጫው ተከቦ እንደሚመታ ይፋ ከማድረግ ውጪ ሌላ ዝርዝር ነገር አልተናገሩም ነበር።

“ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

“በዋሉበት የማያድሩ፣ በየጫካው የሚሹለከለኩ፣ ድርጅታዊ ህልውናቸው ያከተመ፣ ነብሳቸውን የሚወዱ፣ መዋቅራቸው የፈራረሰ፣ አገር ለማተራመስ የሚጠቀሙበትን ኢኮኖሚ የተነተቁ፣ በሌብነት የተሰማሩ፣ ከጁንታነት ወርደው ዝርፊያ ላይ የተሰማሩ የስንዴ ሌቦች” ሲሉ የጁንታውን ወቅታዊ ቁመና የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ  ገልጸው ነበር ::

በሌላ በኩል ከክልሉ መንግስትነት ወርዶ ጫካ የገባውና በርካታ አመራሮቹን ያጣው ትህነግ፣ ድል መጎናጸፉን ደጋፊዎቹ ሲያሰሙ ነበር። ትግራይ ሚዲያ ሃውስ ከፈተኛ ቁጥር ያላቸውን ወታደሮች መደምሰሱን በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን አውጆ ነበር። ይህንኑ ተከትሎ በተላያዩ የሚዲያ አውታሮች ደስታ ሲሰማ ከርሞ ነበር።

ዜናው የፋና ሲሆን አስቀድሞ የተባሉትን ዜናዎች አካተናል።


Leave a Reply