ፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ተፎካካሪ ፖርቲዎችን ማከራከር ጀመረ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያዘጋጀው የመጀመሪያው የፓርቲዎች የክርክር መድረክ በፌዴራሊዝም እና ብዝሃነት ላይ በማተኮር በዛሬው እለት ተካሂዷል።

በክርክር መድረኩ ላይ የብልፅግና፣ ኢዜማ፣ ህብር ኢትዮጵያ እና መኢአድ አመራሮች የፓርቲዎቻቸውን አቋም አንፀባርቀው ነው ክርክሩን ያደረጉት።

ብልፅግና ፓርቲን በመወከል የተገኙት አቶ ፍስሃ ይታገሱ፤ ህወሃት ልዩነትን መሰረት ባደረገ ትርክት የፌዴራሊዝም ምሰሶ የሆኑትን ራስን በራስ የማስተዳደር እና ለጋራ ጉዳዮች በአብሮነት መቆምን ሲያፈራርስ መቆየቱን ተናግረዋል።

ብልፅግና ፓርቲም እነዚህን ስህተቶች አርሞ ያለፉትን ድሎች ማለትም ህዝቦች ቋንቋ እና ማንነታቸው ተከብሮ የሚኖሩበትን የፌዴራሊዝም ስርአት ይገነባልም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማን ወክለው የተገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው፤ በዘር ላይ የተመሰረተው የፌዴራሊዝም ስርአት ብዝሃነትን ማስፈን አልቻልም ብለዋል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ “በየክልሉ የሚገኙ ዜጎችን መጤ እና ነባር እያለ ከፍተኛ የሰው ህይወት እና የንብረት ጥፋት አስከትሏል” ይላሉ።

የፌዴራል ስርአቱ ብሄራዊ መግባባትን ከማምጣት ይልቅ ክልሎችን እርስ በርስ ለጦርነት የሚፈላለጉ አድርጓቸዋልም ነው የሚሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ።

ፓርቲያቸውም የኢትዮጵያን አንድነትና ሉአላዊነት የሚያላላ ሳይሆን የሚያጠናክርን የፌዴራሊዝም ስርአት ለመገንባት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የህብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ተወካዩ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ በኢትዮጵያ በብሄር ላይ የተንጠለጠለው የፌራሊዝም ስርአት የዜጎችን ነፃነትና እኩልነት፤ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በሚገባው ደረጃ ማረጋገጥ አልቻለም ብለዋል።

ህብር ኢትዮጵያ የፌደራል ስርአቱ አወቃቀር ባህልን፣ የህዝብ ስነልቦና፣ ስነ ምህዳር፣ ምጣኔ ሀብት እና ሌሎችን መሰረት እንዲያደርግ በማኑፌስቶው ማስቀመጡንም ነው ያብራሩት።

መኢአድን ወክለው በክርክሩ የተሳተፉት አቶ ሰማኸኝ አብርሃም በበኩላቸው፤ የፌዴራሊዝም ስርአቱ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ባይተዋር እንዲሆኑ አድርጓል፤ በማንነታቸው ምክንያት ለተፈፀሙ ጥፋቶችም አወቃቀሩ ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑ ከፍተኛውን ደረጃ ይይዛል ነው ያሉት።

ህገመንግስቱ ተሻሽሎ የፌደራል ስርአቱ የተዋቀረበት መንገድ ካልተስተካከለ የዜጎችን መብት እና ነፃነት ማስከበርም ሆነ ራስን በራስ ማስተዳደር ማረጋገጥ አይታሰብም ባይ ናቸው።
ፓርቲዎቹ በቀጣይ ድምፅ አግኝተው መንግስት ከመሰረቱ የሚከተሉትን የፌዴራል አወቃቀር በተመለከተም ክርክር አድርገዋል።

የፌዴራል የስራ ቋንቋ እና የክልሎች ልዩ ሃይልን በተመለከተም ፓርቲዎቹ አቋማቸውን አንፀባርቀው ተከራክረዋል።

በፋሲካው ታደሰ – (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Related posts:

125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ
ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ስጋት የገባው ኢሰመኮ የማስጠንቀቂያ ጥሪ አሰማ
"ህሊናን የሚፈታተን" የተባለ ሪፖርት ይፋ ሆነ - አማራ ክልል በተወረረበት ወቅት ግብረርሰዶም መፈጸሙ ተገለጸ

Leave a Reply