“የግብፅ መሠረታዊ ችግርም ያለው ሱዳን ከግድቡ ለምን ትጠቀማለች ከሚል የሚመነጭ ነው”

 • በአሸረቅ S24 ቴሌቪዥን ሱዳናዊ ምሁርና ባለስልጣን የሰጡት ሐሳብ ነው።

° ጋዜጠኛው — “ለዚህ አባባልዎ ማስረጃ አለዎት?”
“ብዙ አለ ። ዋናው መሠረታዊ ችግር ከአባይ ወንዝ አጠቅላይ ውሃ 50 ቢሊዮን ኪዩቢክ ምንጩ ብሉናይል ነው ይህ ከፍተኛ ውሃ ሚመጣው ደግሞ ለ3 ወር ነው


ማለትም ከጁን አጋማሽ እስከ ሴብቴምበር ግማሽ
ከዚህ በኋላ የውሀው ሀይል ይዳከማል እናም ለግብርና ለኤሌትሪክ ሀይልም ሆነ ለሌሎች ፍላጎት መጠቀም አይቻልም እናም ሱዳን ከውሃው ሚጠቀመው 3 ወር ብቻ ነው።
“ከህዳሴ ግድቡ ማለቅ በኋላ ግን የአባይ ውሃ ፍሰቱን ሳያቋርጥ አመቱን ሙሉ ተስተካክሎ ይደርሱናል
በዚህም ግብፅ በአስዋን ግድብ ተጠቅማ በአመት 3 ግዜ ከእርሻ ምርት እንደምታገኘው ሁሉ ሱዳንም በአመት አንዴ ብቻ የነበረውን 3 ግዜ ማምረት ትችላለች በአመት አንዴ ብቻ እንድንዘራ ያደረገንም የውሀው ፍሰት ለ 3 ወር ብቻ በመሆኑ ነው የህዳሴው ግድብ ግን አመቱን ሙሉ ውሃ እንድናገኝ ያረጋናል።”
“ይህ ብቻ አደለም እንደ እርሻ ምርቱ ሁሉ የአልመረዊ ግድብም የተስተካከለ ኤሌትሪክ ሀይል ማመንጨት ይችላል
የመራዊ ግድብ ከ Feb — April ሀይል የማመንጨት አቅም ደካማ እና የተቆራረጠ ነው ። ከግድቡ የሚለቀቀውን ውሃ ተርባይኖችን ማዞር ስለሚችል የሀይል ማመንጨት አቅሙ የተስተካከለ ይሆናል”

~ ከ 1959 ስምምነታችን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ሱዳን ካላት ከውሃ ዴርሻ 6.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃ መጠቀም አለመቻሏን የቀድሞ ውሀና መስኖ ሚ/ር ከማል አሊ ገልፀዋል ። ከዚህ ሌላ ተጨማሪ 3.5 ቢሊየን ውሃ ከክረምቱ ዝናብ ሃያልነት ከሚገኝ በአጠቃላይ 10 ቢሊየን ኪዩቢክ ውሃ በእየአመቱ ታጣለች። ሱዳን ይህን ለመጠቀም ሞክራ ያልተሳካለት ውሃ በቀጥታ ወደ አስዋን ግድብ ነው ሚገባው።

“የህዳሴው ግድብ ይህን 10 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃ ወደ ግብፅ እንዳይፈስ ስለሚከላከልልን ቅድም ያልኩህን በአመት 3 ግዜ ማምረት እንድንችል እና የኤሌትሪክ ሀይልም በተስተካከለ መልክ እንድናገኝ ያደርጋል”

ጋዜጠኛው በመሀል “መርሳት የሌለብህ እሚሉት እና ሚፈልጉት ከ1959 ሳይሆን ከአሁን ወቅታዊ ወቅታዊ ሁኔታ እንጀምር ነው” ?

“የህዳሴው ግድብ የሱዳንን ውሀ ድርሻ ስለሚያስከብርልን ይህ 10 ቢሊየን ውሃ ወደ ግብፅ መሔድ አይችልም ። ስለዚህ የግብፅ ፍትጊያ ግራ ማጋባት እና ጩኸት መሠረታዊ ምክንያት ይህ የሱዳን ድርሻ የሚያጡት 10 ቢሊዮን ውሃ ነው ስለዚህም ዋናው ችግር ያለው ከሱዳን እንጅ ከኢትዮጵያ ጋር አደለም።
ይህ የሱዳን ጥቅም መጥጠበቅ ሲገለጥላቸው ለምን በሚል አየፈጠረ ያለ ችግር ነው ችግራቸው ሱዳን ለምን ትጠቀማለች ነው”

ጋዜጠኛው “ከውሀ ሚ/ር ሀላፊዎች አሁንም የሱዳንን ከዚህ ግድብ ተጠቃሚነት ሲናገሩ ሱዳን ከኢትዮጵያ በበለጠ ተጠቃሚ እንደሆነች ነው ሚናገሩት” ?

“በሚገባ! ይህን ዶ.ር ማህመድ አቡዘይድ ዶ.ር ሶፍወት አብድ አድዳኢም እና ልሎችም ሀላፊዎች በሚገባ ተናግረዋል።ሌላውን የደለል ጉዳይ ነው። ባለፉት አመታት የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግሮች መንስኤው በከፍተኛ ደለል ክምችት ተርባይኖች ስራ ማቆም መሆኑን ኦፊሴላዊ መግለጫ በባለስልጣኑ መግለጫ ሲነገረን ኑሯል
የህዳሴው ግድብ ይህን የደለል ክምችት በከፍተኛ ደረጃ ይከላከላል ያስቆምልናል። በዚህም የሮዛሬስ እና አልመረዊ ግድቦች ሌሎችም ያለ ችግር ስራቸውን ይሰራሉ።

“የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ዋጋ ከሱዳን አኳያ በጣም ቅናሽ ይኖረዋል እናም ሱዳን እንደ ካጅባር ፣ ሽሬክ ፣ ዳልል እና የመሳሰሉ ግድቦችን መገንባት ሳያስፈልጋት ከኢትዮ ሱዳን የተጀመረውን የኤሌትሪክ ሀይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ አጠንክሮ ሰርቶ በመጨረስ የሀይል ፍላጎታችንን በቅናሽ ዋጋ ከኢትዮጵያ መግዛት ይቻለናል”

“የውሀ ክምችት፣ግብፅ 162 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሀ ክምችት የመያዝ አቅም ነው ያላት። ባንፃሩ ሱዳን ደግሞ የማከማቸት አቅሟ 10 ቢሊዮን ነው (ይህን አቶ ሰኢድም ሊያረጋግጥልህ ይችላል)። በመሆኑም የሱዳን መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተነጋግረው የሱዳንን ውሃ ድርሻ በህዳሴው ግድብ ሀይቅ በማቆየት በብሉ ናይል ግዛት ለመስኖ እርሻ መጠቀም ይቻለናል ።
ወንድም ጧሒር! (አወያዩን) ከህዳሴው ግድብ ሱዳን ምታገኘው ጥቅም ከዚህ ሁሉ ከነገርኩህ በጣም በጣም የበዛ ነው ። ይህ በአለም አቀፍ ህግ የተፋሰሱ ታችኛው ሀገሮች ጥቅም በሚል የተገለፀ ነው ።

አንድ ሀገር የዚህ አይነት ትልቅ ግድብ ሲገነባ የጋራ ተጠቃሚ የሆኑ ሀገሮችን ለግንባታው እንዲያዋጡ ያስገድዳል። በካናዳ እና አሜሪካ እንደሆነው ካናዳ ግንባታውን ስታስብ ወደ USA በመሔድ ግድቡ ሚያስገኘውን የጋራ ጥቅም (ልክ እንደ ህዳሴው ግድብ ) በመግለፅ ለግንባታው የተወሰነውን አስከፍላለች ።
እኛ ምንም አልከፈልንም በዜሮ ነው የጥቅሙ ተጋሪ የሆንነው።

“ገራሚ እና አስደናቂው ነገር ግድቡ ይፈርሳል የሚለው የግብፅ ስጋት ንግግር (ባዶ ወሬ ) ነው። እውነት አሁን የግድቡ ደህንነት ስጋት ግብፅን ከሱዳን በበለጠ አስግቷት ነው ? ይገርማል እኮ! በዓለም ዙርያ ከ 45 በላይ ትልልቅ ግድቦች አሉ ። ባለፉት 20_30 አመታት ውስጥ አንድም መፍረሱን አልሰማንም። “የአስዋን ግድብ አይፈርስም የህዳሴ ግድብ ግን ይፈርሳል” አስቂኝ ተረት ።
መታወቅ ያለበት ነገር የአስዋን ግድብ የተገነባው 60ዎቹ ውስጥ በወቅቱ ኋላ ቀር ቴክኖሎጂ በሩሲያን ነው
የህዳሴው ግድብ እየተገገነባ ያለው ደግሞ በ21ኛ ክፍለ ዘመን በወቅቱን የአውሮፓ የቴክኖሎጂ ነው ።
አስዋን ግድብ ውሃ መያዝ አቅም 162 ቢሊዮን
የህዳሴው ግድብ ደግሞ በግማሽ አንሶ 74 ቢሊዮን
እንዴት ነው ሚገናኙት ? ግብፆች ግድቡ ያረፈበት ቦታ የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት አለበት ይሉናል።ኢትዮጵያ ይህ አይነት ችግር የለበትም ማንኛውንም መፅሐፍ ብትገልጥ ወይም የትኛውም ድረ ገፅ ገብተህ ግብፆች ለሚሉት ሁሉ ማረጋገጫ አታገኝም የላቸውምም”

Mahmud Nuru ነው የትርጉሙ ባለቤት 🙏
የዓባይ ልጅ

 • ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ
  ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸዉና ከምትከበርባቸዉ ሀገራዊ ልዩ እሴቶቿ ዉስጥ አንዱ የዘርፈ ብዙ ልዩነቶች የመቻቻል ምድር መሆኗ ሲሆን ህዝቦቿ በፈረሃ አምላክ የሚመሩ ናቸዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን የሀይማኖት ብዝሃነትን […]
 • Ethiopia tows 2.3bln USD remittance a year less
  ADDIS ABABA – Ethiopian Diaspora Agency disclosed that the country has secured 2.3 billion USD in remittance from the Diaspora over the past eight months. Agency Director-General Selamawit Dawit told the […]
 • Ethiopia, World Bank seal 200 mln USD loan agreement
  ADDIS ABABA—Ethiopia and World Bank signed 200 million USD loan agreements to support the implementation of Digital Foundation project. As to the information obtained from the Ministry of Finance and […]
 • የቆዳ ዋጋ መውደቅና አገራዊ ኪሳራው
  ድሮ ድሮ በደጋጎቹ ዘመን “ጮሌዎቹ” በግ ከአርሶ አደሩ በስሙኒ ገዝተው ቆዳውን መልሰው በስሙኒ በመሸጥ ስጋውን በነጻ “እንክት” አድረው ይበሉ ነበር ይባላል። ታዲያ የስጋን ያህል ዋጋ ያወጣ የነበረ የቆዳ ዋጋ ከቅርብ […]
 • ሕንድ ውስጥ ከኮቪድ ያገገሙ ሰዎች ዓይነ ስውር በሚያደርግ ‘ብላክ ፈንገስ’ እየተጠቁ ነው
  አሁን ደግሞ የሕክምና ባለሙያዎች ከኮቪድ-19 እያገገሙ ባሉና ባገገሙ ሕመምተኞች ላይ ‘ብላክ ፈንገስ’ የተባለ በሽታ እያዩ ነው። በሕክምና ቋንቋ ሙክሮሚኮሲስ የሚሰኘው ይህ በሽታ ሰው ለይቶ የሚያጠቃ ነው። ብዙ ጊዜ ይህ በሽታ […]
 • መልስ የሚሻ ዜግነታዊ ጥያቄ – ሻለቃ ፈይሳ ናኔቻ
  በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭና ጥቁር እኩል መሆኑን በተግባር በሐሳብ ሞግቶ ፣ በአውደ ውጊያ ተዋግቶ ያረጋገጠ ለነፃነትና ክብሩ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ቅንጣት ታህል ወደኃላ የማይል የዓለም ጭቁኖች መብት ተሟጋችነቱን በጥቂቱ ማንሳት […]

Categories: OPINION

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s