የኢትዮጵያ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ በግንቦት 2013 የሚካሄድ ሲሆን፣ ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርተውታል። ይህ በጉጉት የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ምርጫ በሀገራችን የሚካሄደው የመጀርሪያው ነጻ እናፍትሐዊ ምርጫ ይሆናል ተብሎ ይታመናል። ከ2010 ዓ.ም. አንስቶ በማስተዳደር ላይ የሚገኘው አመራር የፖለቲካውን ምኅዳር ለማሳፋት እና ዴሞከራሲያዊእና እውቀት ተኮር የሆነ ምቹ ከባቢ እንዲኖር ለማስቻል በቁርጠኝነት የዴሞከራሲያዊነት ጎዳናን ተያይዟል።

ይህ ግብ ያለ ምንም ተግዳሮቶች እውን የሚሆን አይደለም። ይሁን እንጂ፣ የፌደራል መንግሥት ዴሞክራሲያዊነትን ይዞ ለመጓዝ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ሳያመቻምች ቀጥሏል።የቀደመው አስተዳደር ዴሞክራሲያዊ አገዛዝን ለመገንባት ካለመቻሉ የተነሳ፣ ኢትዮጵያ ጠንካራ እና ጤናማ ዴሞከራሲያዊ ባህል እና ልምምድ ይኖራት ዘንድ፣ በአሁኑ ወቅት አስፈላጊዎቹን ተቋማት እና አስተሳሰብ የመገንባት ሁለትዮሽ ፈተናን ተጋፍጣለች።


Read also this

  • በቀጣይ አመት ስንዴን ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው -አቶ ሽመልስ
    በቀጣዩ ዓመት ስንዴን ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ የሚያስችሉ ስራዎች በመኸር እርሻ እየተከናወኑ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ ። የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራና ዱግዳ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማውን የስንዴ ማሳ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደተናገሩት በክልሉ በአጠቃላይ 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን […]

ኢትዮጵያውያንም ሀገራቸው ለታሪኳ እና ለኩሩ ሕዝቧ መሻት በሚመጥን መልኩ፣ እንዲሁም፣ ያላትን የተትረፈረፈ የዕድገት አቅም ባማከለ ሁኔታ፣ ሀገራቸውን ወደ አዲስ የአስተዳደር እና የብልጽግና ዘመን የማሸጋግር ዕድል ቀርቦላቸዋል።እስካሁን ድረስ፣ የፌደራል መንግሥት የመጀርሪያውን ነጻ፣ ፍትሐዊ እና ሰላማዊ መረጫ ለማከናወን ያለው ቁርጠኝነት፣ ይህንን ግብ ለማሳካት በሚያካሂደው ያልተቋረጠ ዝግጅት አማካኝነት የተመሰከረ ነው።

ሰላማዊ እና ሕጋዊ ምርጫ እንዲካሄድ ከፌደራል ፖሊስ፣ ከጠቅላይ አቃቤ ሕግ፣ ከብሔራዊ መረጃና የደህንነት አገልግሎት፣ ከመከላከያ ሚኒስቴር እና ከክልል አመራሮች ተውጣጥቶ ሀገር አቀፍ የምርጫ ደህንነት ኮሚቴ በመንግሥት ተዋቅሯል። ዜጎች በነጻነት የመምረጥ ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ይጠቀሙ ዘንድ የመንግሥት ሚና ምን መሆን እንዳለበት ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል። ግጭት ሊከሰት እንደሚችል ጠቋሚ የሚታይባቸውን አካባቢዎች ለመለየት ኮሚቴው ልዩ ርምጃዎችን ወስዷል።

ከምርጫ ጋር የተያያዙቅሬታዎችን ለማስተናገድም፣ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምርጫ አቤቱታ የሚያደምጥችሎት አቋቁሟል።የፖለቲካ ፓርቲዎች በመላው ሀገሪቱ የምረጡኝ ቅስቀሳ በስፋት እያካሄዱ ይገኛሉ። መራጮች በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ለማድረግ እንዲችሉ፣ ብሔራዊ ጠቀሜታቸው የተመሰከረላቸው ገለልተኛ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበረሰብተቋማት የሚሳተፉበት የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዴሞክራሲያዊነት እንዲስፋፋ ባላቸው የላቀ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ከክልል ፕሬዚደንቶች እና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራሮች ጋር የሚያደርጉትን ስብሰባ በመቀጠል፣ በምርጫ ቅድመ-ዝግጅት ሂደቱ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን እናተግዳሮቶችን ለይቶ የመፍታት ጥረታቸውን ቀጥለዋል።

በዚህም መሠረት፣ በየካቲት 18፣ 2013 ዓ.ም. እና በሚያዝያ 8፣ 2013 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበይነ መረብ በታገዘ ስብሰባ አማካኝነት፣ በየክልሉ የጸጥታና ደህንነት ጉዳዮችን አፈጻጸም እና የምርጫ ጣቢያዎችን የዝግጅት ሁኔታ ተከታትለዋል።ምርጫው ሊካሄድ ጥቂት ሳምንታት የቀሩት እንደ መሆኑ፣ ዜጎች በቀሪው ጊዜ በመጠቀም የምርጫ ካርድ ወሰደው ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን እንዲጠቀሙና በምርጫው አጠቃላይ ሂደት ገንቢ ተሳትፎ በማድረግ ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ ይካሄድ ዘንድ የጋራ ጥረት እንዲያደርጉ ይበረታታሉ።


Leave a Reply