“ኢትዮጵያ ግድቧን ውሃ ብትሞላም የሚፈጠር ጫና የለም” የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ታላቁ የኢትዮጵያ ግዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በግብጽ ላይ የሚፈጥረው ጫና እንደሌለ ካለም ያንን ለመቋቋመ የሚያስችል በቂ ውሃ እንዳላት የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሽኩሪ ለአገሪቷ ፓርላማ አባላት ገለጹ።

ሑለተኛው ዙር የግድቡ ውሀ ሙሌት በግብጽ ላይ የሚያመጣው ጉዳት እንደሌለ ካለም ለመከላከል መንግስታቸው በቂ ዝግጅት ማድረጉን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ በአስዋን ግድብ በቂ ውሃ መያዛቸውን አብራርተዋል።

“የተደረጉ የቴክኒክ ጥናቶችን ተንተርሼ ነው” ገለጻውን የምሰጣችሁ ያሉት ሚኒስትሩ፤ በዘንድሮው የክረምት ወራት ከፍተኛ ጎርፍ ይጠበቃል፤ ስለሆነም ኢትዮጵያ ግድቧን ውሃ ብትሞላም የሚፈጠር ጫና የለም ከተፈጠረም ጎርፉ ግድባችንን መልሰን ለመሙላት ያግዘናል ብለዋል።ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግብጽ ላይ ጉዳት አያስከትልም።

ነገር ግን ጉዳት የሚያመጣ ከሆነ በዚህ ረገድ እንደ አገር ያንን ለመቋቋም የሚያስችል በሁሉም መስክ አስፈላጊ ሀብት አለን ሲሉም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።ኢትዮጵየ የግድቡ መገንባት በግብጽ ላይ የሚፈጥረው ጫና እንደሌለ በተደጋጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፤ የግድቡ ውሃ አሞላልም የታችኛውን የተፋሰሱ አገራት በማይጎዳ መልኩ እንደምታከናውን መግለጿ አይዘነጋም።(ኢ ፕ ድ)


    Leave a Reply