በትግራይ ክልል ኦፍላ ወረዳ አንድ እናት በህመም ሞተዋል፤ “150 ዜጎች በረሃብ ሞቱ የሚለው ግን ፈጠራ ነው”

በትግራይ ኮረም አካባቢ የኦፍላ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አንዲት እናት በህመም ምክንያት ከመሞታቸው በቀር በረሃብ ምክንያት የሰው ሕይወት እንዳላለፈ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ። ይህ የተገለጸው በተጠቀሰው ቦታ 150 ዜጎች በረሃብ ሞተዋል በሚል በሃሰት እየተሰራጨ ያለውን ዜና ለማረጋገጥ በስፍራው በመገኘት ማጣራት ከተካሄደ በሁዋላ ነው።

“I THEN RECEIVED A REPORT JUST THIS MORNING OF 150 PEOPLE DYING FROM HUNGER IN OFLA WOREDA- JUST SOUTH OF MEKELLE.” MR LOWCOCK

ይህንኑ አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ እንዳሉት ኮረም አካባቢ የኦፍላ ወረዳ ቀደም ብሎ የፀጥታ ችግር አለባቸው ተብለው ከተጠቀሱት ሰባት አካባቢዎች ውስጥ ስሙ የሌለ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ የእርዳታ ስርጭቱ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ያለበት ሰላማዊ አካባቢ ነው። የተካሄደው ማጣራትም ይህንኑ ያረጋገጠ ነው።


በትግራይ ክልል 150 ዜጎች በረሃብ ምክንያት እንደሞቱ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑንን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፣ በተጠቀሰው ስፍራ ብቻ ሳይሆን በመላው ክልሉ እየተደረገ ያለው ሰብዓዊ ድጋፍ በተጠናከረ መንገድ እየሄደ መሆኑን አረጋግጠዋል። ዘመቻው የአገሪቱን መልካም ገጽታ የማይፈልጉ አካላት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን በመጠቀም በትግራይ ክልል”በረሃብ ምክንያት 150 ሰው ሞተ” በማለት የሚነዙት ወሬ ሀሰት የሃሰት መረጃ እንደሆነ አመልክተዋል።

“ERITREAN FORCES HAVE ALSO BLOCKED THE MOVEMENT OF HUMANITARIAN STAFF ON THAT ROAD TRYING TO DELIVER URGENT SUPPORT TO CHILDREN WITH SEVERE ACUTE MALNUTRITION.” MR LOWCOCK

የስም ማጠልሸቱና የፈተራው ዜና እንደተሰማ በተደረገው ማጣራት በኦፍላ ወረዳ አንዲት እናት በህመም ምክንያት መሞታቸውን ማረጋጋገጥ መቻሉን እና ከዚህ ውጪ ግን በምግብ አቅርቦት ችግር የሞተ ሰው አለመኖሩን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።የዚህ ሀሰተኛ ዜና ዓላማ “የአገሪቱን መልካም ገጽታ ለማጉደፍ ያለመ እና መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ያላገናዘበ የራሱ ድብቅ ተልዕኮ ያለው መልዕክት ነው” ሲሉም ገልጸዋል።

የእርዳታ ስርጭቱ መሻሻል ማሳየቱን ትግራይ ሄደው ተመልክተው ምስክርነታቸውን እየሰጡ ባሉበትና የጦርነት ዘመቻው ተስፋ እያስቆረጠ ሲሄድ ረሃብን የቅስቀሳ ስልት አድርጎ መውሰድ በአሁኑ ሰዓት ዋንኛ አማራጭ ተደርጎ መወሰዱ በስፋት እየታየ ነው።


 • TPLF says it wants a referendum to decide the fate of Tigray
  A new bellicose state could emerge in Ethiopia as the TPLF is toying with the idea of a referendum to decide the fate of Tigray. Tsedkan Gebretensae, one of the people driving TPLF’s senseless war against the Ethiopian state, had an interview today with BBC World Service. Tsedkan indicated thatContinue Reading
 • Ethiopian Airlines denies shipping arms, soldiers to war-torn Tigray region
  Ethiopian Airlines strongly refutes all the recent baseless and unfounded allegations that are running on social media regarding the airline’s involvement in transporting war armament and soldiers to the Tigray region. It is to be recalled that all flights to and from the Tigray region were suspended since November 2020.Continue Reading
 • Turkey’s Erdoğan discusses bilateral ties with Ethiopian PM
  resident Recep Tayyip Erdoğan discussed bilateral relations with Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed in a phone call, the Presidential Communications Directorate said Sunday. The two leaders discussed spoke about Turkey-Ethiopia relations and regional developments. Erdoğan highlighted that Turkey values Ethiopia’s peace and stability and that Ankara is ready to provideContinue Reading
 • Sudan welcomes GERD talks
   Manila) welcomed an Algerian initiative calling for holding a direct meeting between leaders of Egypt, Sudan and Ethiopia to reach a solution for the differences over the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD). Chairman of Sudan’s Sovereign Council Abdel Fattah Al-Burhan on Saturday met in Khartoum with the visiting Algerian Foreign Minister Ramtane Lamamra. “The leadership in Sudan hasContinue Reading

Leave a Reply