እ.ኤ.አ በ2022 የሚካሄደውን ሁለተኛውን የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባዔን ለማስተናገድ ፍላጎት እንዳላት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ ከሩሲያ-አፍሪካ የትብብር ፎረም ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭን ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል። ውይይታቸው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2022 የሚካሄደውን ሁለተኛውን የአፍሪካ-ሩሲያ ጉባዔን ለማስተናገድ ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ከሩሲያ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት ለክቡር አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ገልጸውላቸዋል።
አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ስለጽ/ቤታቸው ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የአፍሪካና ሩሲያ ኩባንያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል የኢኮኖሚ ትብብር ማህበር መቋቋሙን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመጪው ክረምት ከአፍሪካ ህብረትና ከአፍሪካ አገራት ጋር ምክክር እንደሚደረግም ገልጸዋል።
ሩሲያ ይህንን መድረክ ለመፍጠር የወሰደችውን ተነሳሽነት አድንቀው ሁለተኛውን የአፍሪካ ሩሲያ ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ያላትን ፍላጎት አቶ ደመቀ ገልጸውላቸዋል።በሁለቱ አገራት መካከል በደህንነት፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ በግብርና፣ በኢነርጂ፣ በጤና እና በስነ-ምድር ምርምር ዘርፎች ያላቸውን ትብብር በተመለከተ ምክክር አድርገዋል።
አምባሳደር ኦሌግ ኦዜሮቭ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሩስያ ጉብኝት እንዲያደርጉ የሩስያ አቻቸው ሰርጌ ላቭሮቭ የላኩትን ግብዣ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ኢፕድ እንደዘገበው
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ
- መንግስት ክትግስት በኋላ የሚከሰት ሕግ ማስከበር ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን አስታውሶ ጦርነት ናፋቂዎች አደብ እንዲገዙ አሳሰበ“ካለፈው ስሕተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ሁላችንም ተባብረን… Read more: መንግስት ክትግስት በኋላ የሚከሰት ሕግ ማስከበር ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን አስታውሶ ጦርነት ናፋቂዎች አደብ እንዲገዙ አሳሰበ
- Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia” The Republic of Somaliland, is a sovereign state with its… Read more: Somaliland offended by G7 referring the Republic of Somaliland as “Somaliland Region of Somalia”
- ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያየኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በሌላ መንገድ እየታገሉ ይገኛሉ ያላቸው አካላት… Read more: ” በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን አሁንም ሳይመሽ ቶሎ ወደ ድርድሩ እንዲገቡ በትህትና እንጠይቃለን ” ፕ/ር መስፍን አርአያ