የአገር መከላከያ ሰራዊት ” ርዝራዥ” ሲል የሚጠራውን ሃይል መደምሰሱን አስታወቀ። ሃይሉ የተደመሰሰው ድንበር አቋርጦ ወደ ሱዳን ለመሸሽ በሞከረበት ወቅት እንደሆነ ታውቋል። ከተገደሉት በፍተሻ ” የኦሮሞ ማንነት መታወቂያ ተሰርቶላቸው ነበር” ተብሏል።
የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት የግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት የጁንታው አባላት በከፍተኛ ዝግጅት ነበር ከአገር ለመውጣት ሙከራ ያደረጉት። ቀደም ባለው መግለጫቸው በዚሁ ሃይል ላይ በስምንት አቅጣጫዎች በተወሰደ እርምጃ የተርፈው ሃይል ተበታትኖ ከአገር እንዳይወጣ ስራ መሰራቱን አስታወቀው እንደነበር ይታወሳል።
ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ ፣ ርዝራዡ የጁንታው አባላት ወደ ሱዳን ሲሄዱ በቀላሉ ማለፍ እንዲችሉ ያዘጋጁት የኦሮሞ ማንነት እንዳላቸው የሚያስመስል መታወቂያ ነው። ከዚህም በተጨማሪ አለባበሳቸውን ቀይረው ነበር። ይሁን እንጂ አስቀድሞ በተዘረጋ ስልትና እቅድ መሰረት ሃሳቡ ሳያሳካ ቀርቷል። መከላከያ በክትትል ደርሶ እርምጃ ወስዷል። አብዛኞቹ ሲደመሰሱ የተቀሩት ወደ ጉድጓድ መጋታቸው ተገልጿል።
ወደ ሱዳን ለመግባት የተፈለገበት ዋና ምክንያት ሱዳን ተቀምጠው አገር ውስጥ ያሉትን ታጣቂ ሀይሎች በሽምቅ ውጊያ በማሰማራት ሀገር ለመበጥበጥ ባለው ዕቅድ መነሻ እንደነበር ሌ/ጄነራል ባጫ በመግለጫቸው አስረድተዋል። እርምጃ በተወሰደባቸው ሁሉም የጁንታው አባላት እጅ ላይ የሀሰተኛ መታወቂያ እንድተገኘባቸው አመልክተዋል።
- ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበችአሜሪካ ተቀምጠው የኢትዮጵያን ሰላም የሚያውኩ ተፈላጊዎችን ሀገሪቱ አሳልፋ በመስጠት ትብብር… Read more: ኢትዮጵያ በአሜሪካ የሚኖሩ “ተፈላጊዎች” ተላልፈው እንዲሰጧት ጥያቄ አቀረበች
- ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷልፈቃድ ሳይኖራቸው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት አማረ እና ቤተሰቦቹ… Read more: ሃሰተኛ የተባሉ የዩቲዩበር ባለቤቶች ተያዙ፤ በአንድ ተጠርጣሪ ብቻ ስምንት የዩቲዩብ ቻናል ተከፍቷል
- “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረበሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት።… Read more: “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል”፤ የሚለው ዜና የአማራ ፖለቲካን ቀየረ
- Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside… Read more: Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?