የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነጻነትና አንድነት በጽናት እንደሚያከብር አስታወቀ


የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አባል አገራት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ፣ የፖለቲካ ነፃነትና የግዛት አንድነት እንደሚያከብሩ፣ ማክበር ብቻ ሳይሆን የጸናና ጠንካራ አቋም እንዳላቸው አስታወቁ። በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ያለውን የሰብአዊ ቀውስ ለመፍታት ያለውን ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥም አመክቷል።
የጸጥታው ምክር ቤቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነጻነትና የግዛት አንድነትን በፅኑ እንደሚያከብርም በመግለጫው በማያወለዳ መልኩ አስፍርላ። The members of the Security Council reaffirmed their strong commitment to the sovereignty, political independence, territorial integrity and unity of Ethiopia.
የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ መንግስት በክልሉ ለሚያደርገው የሰብአዊ ድጋፍ እውቅና በመስጠት ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርቧል።የአገሪቱ መንግስት የሚያደርገው የተቀናጀ የሰብአዊ ድጋፍ እንደቀጠለ ቢሆንም በክልሉ ያለው የሰብአዊ ቀውስ ግን አሁንም አሳሳቢ ስለመሆኑም ገልጿል።
የፀጥታው ምክር ቤት ለዓለም አቀፉ የተራድኦ ተቋማት የተባበሩት መንግስታትን የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አሰጣጥ መርሆዎችን ማለትም የገለልተኝነት፣ የሰብአዊነት፣ አለማዳላትን እና ነፃነትን በመከተል ለኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርቧል።
በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር አሁንም የሰብአዊ እርዳታውን በሚፈለገው መጠን ለማቅረብ አዳጋች እንዳደረገው የጠቀሰው ምክር ቤቱ ያለው ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲረጋጋም ጥሪ አቅርቧል።
በክልሉ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት በተለይ ሴቶች ላይ እየደረሰ የሚገኘው የፆታዊ ጥቃት በጥልቅ እንደሚያሳስበው ያስታወቀው ምክር ቤቱ ጥፋተኞችን ለህግ ለማቅረብ ምርምራ እንዲደረግም ጠይቋል።በትግራይ ክልል ተፈፅመዋል የተባሉትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለመመርመር የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን የጀመሩትን እንቅስቃሴ በበጎ እንደሚመለከተው የፀጥታው ምክር ቤት አስታውቋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የሰብአዊ መብት ኮሚሽን እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ ምክር ቤቱ እውቅና በመስጠት ሂደቱ ዓለም አቀፍ ህግጋትን የተከተለ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል። የአፍሪካ ሕብረት እና የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት በቀጠናው ሰላም ለማስፈን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም የፀጥታው ምክር ቤት እንደሚደግፈው ነው ያስታወቀው።
- 125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን…
- «በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!በየትኛውስ አገር ነው የአገሩን ሉዓላዊነትና ነፃነት ለማስጠበቅ የሕዝቡን ዘላቂ ሰላምና ጥቅም ለማስከበር ያለ እረፍት በሐሩርና…
- በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተፈረሙ ወታደራዊ ስምምነቶችን አጽድቋል። ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው…
- የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባትየ25 ዓመታት ሰቆቃ! አቶ አበራ ዓለማየሁ የ68 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው። ከዚህ ውስጥ 25 ዓመቱን…