ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ገና ከማለዳው የሲ አይ ኤ ቅጥረኛ ምንደኛ ከሀዲ እንደ ነበረ 21/9/62 ቁ1019/18/31 ማህደር ቁ ሀ/1/19 ሠ2 በእንግሊዘኛ ተፅፎ ማህደር ላይ የገኘውን በመጥቀስ ደጃዝማች ተስፋ ሚካኤል ጆርጆ በሌሎች ተጨባጭ ማስረጃዎች አስደግፎ አጋልጦታል።
ከኢትዮጵያ አብዮት ፍንዳታ በኋላ ስልጣን በመሻት የቀበሮ ባህታዊ በጎች መሀል……እንደሉ ወደ ደርግ በመለጠፍ ምንዳ የቆረጠለትን የአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የስለላ ድርጅት ሲ አይ ኤን ማገልገልና ምስጢር መሸቀጡን ተያያዘው።
ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ኢሰፓአኮ እንደ ተመሰረተ፡ የኤርትራ ክፍለ ሀገር ኢሠፓአኮ አንደኛ ፀሀፊ በመሆኑ ስልጣኑን በመጠቀም መሰሪ ተግባሩን በስፋት ተያያዘው። ግርማይ ገብረ የሱስን (አማኑኤል) የርዕዮተ ዓለም ሃላፊ፡ አስማማው ሀይሌን የድርጅት፡ ሀይሌ ወልደ ስላሴን የወጣቶች፡ እቴነሽን(ዕቁባቱ ነሽ) የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ በማድረግ የሲ አይ ኤን የመረጃ ጥማት አረካ።
ምስጢር የመሸቀጥና ለኢምፔሪያሊዝም መረጃ የማቀበል ተግባሩን ለማስፋት ወደ ቀይ ኮከብ ቀዳሚ ዘመቻ መምሪያ እግሩን ማስቀደሙን ያልወደዱት አዛውንቱ የጦር ኃይሎች ኤታማጆር ሹም ሌተና ጄኔራል ኃይለ ጊዮርጊስ ሃብተ ማርያም የዚህ ሰው አካሄድ አላማረኝም ሲሉ ለጄኔራል ገብረየስ ወልደ ሀና ጉዳዩን አማከሩ። የፖለቲካ መምሪያ ሃላፊው ገብረየስ ወልደ ሃናም ስለ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ሴሰኝነትና ማታ ማታ ከሻዕብያ ጋር ያለውን ግኑኙነት ከበርካታ ሀገር ወዳድ መኮንኖች ሪፖርት ደርሷቸው ነበርና ጉዳዩን ለውይይት አቀረቡት። ሆኖም ከተስፋዬ ገብረ ኪዳን ጀምሮ የደንነት ሚኒስቴሩ ተስፋዬ ወልደ ስላሴ ሌሎችም ከጄኔራሉ ጋር ቅራኔ ስላላቸው ነው በሚል አድበሰበሱት። ከጓድ መንግስቱ ኃይለ ማርያም ጋር ተጣብቆ የነበረው አፈ ጮሌው ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስም የማሳሳት ስልቱን ተጠቅሞ የቀይ ኮከብ ዘመቻ እንዲ ከሽፍ ምስጢር ለሲ አይ ኤ በማቀበል ሀገርን ለከፍተኛ ውድቀት መዳረጉን ኦሮማያ የተባለውን የበዓሉ ግርማን መፀሀፍ ለአነበበ ሁሉ ግልፅ ነው።


ይህ ከሀዲና ምንደኛ የሲ አይ ኤ ቅጥረኛ የሆነው ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ የደርግን ምስጢር አፍሶ ለባዕድ ከአቀበለና ኢትዮጵያ ወደ ውድቀት አፋፍ ላይ በሆነችበት ወቅጥት ለሚስኪኑ ረሃብተኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዕርዳታ የተሰበሰበውን ሽልንግ ጠራርጎ በመሸከፍ በቦርሳው አጭቆ እናት ሐገር ኢትዮጵያ በአፍ ጢማ ትደፋ ብሎ ሀገርና ሕዝብን በመክዳት ወደ አሜሪካን ኮበለለ።
ይህ ከሃዲ ግለሰብ ጥገናዊ ለውጦ እንደ ተጀመረና የቀድሞ ወዳጆቹ የወያኔ ጁንታ አመራሮች መንኮታኮት አይቀሬ መሆኑን እንደ ተመለከተ፡ በለመደው ስልት የሲ አይ ኤ ምንደኝነቱን ተልዕኮ ለመወጣት የለውጥ ኃይሎችን ድምፁን ዘለግ አድርጎ በማወደስ እንደ ብርሃነ መስቀል ሁሉ መካሪና ዘካሪ መስሎ ወደ አራት ኪሎ አቀና።
ዳሩ ክህደት ክህደት ነው ለኢትዮጵያ ጠላቶች ቦታ የለመኖሩን ከተረዳና ይሻውን ስልጣን ተቆናጦ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳይሆን ቀጣሪውን የአሜሪካን የስለላ ድርጅት ለማገልገል እንደ ማይችል ሲረዳ፡ አብይ ሀገር መምራት አይችልም አለ። ቀጥሎም አሁን የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎጥ ለማጨፋጨፍ ወለጋ የአማራ ነው ሲል ያላዝን ጀመረ። ይህ ግለሰብ ቤንሻጉልና ጋምቤላ የሱዳን፡ ኦጋዴን የሱማሌ ነው ከማለት የማይመለስ፡ የሲ አይ ኤ ቅጥረኛ፡ የኢትዮጵያ አንድነት ጠላቶች ምንዳ የቆረጡለት፡ በስብዕናው የዘቀጠ ሴሰኛ ነው።
ዳሩ ጅብ በማያውቁት ሀገር ዕንግድነት ገብቶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ ሲባል የሰማን ሁሉ ዳዊትም ለማያውቁት ቅዱስ መስሎ የሚታይ የኢትዮጵያን ሕዝቧ ጠላት ነው።
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!


Leave a Reply

Previous post አማራ ክልል ኮሚሽነር አበረን አገደ፤ ” ከሁለቱም ወገን አሉበት”
Next post “በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት በአንድ ጠባብ ቤት ውስጥ ከ6 እስከ 7 ሰው ይኖራል”
%d bloggers like this: