By Dejene Assefa

ዛሬ ኤፕሪል 30/2021 የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ተካሂዶ ነበር:: የስብሰባው አጀንዳ የማይናማር ጉዳይ ሲሆን የታየውም በዝግ ስብሰባ ነበር::

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ጉዳይ ባለፈው ሳምንት ኤፕሪል 22 ተዘግቷል:: ቢሆንም ዛሬ ሌላ ነገር ተከሰተ:: እነሆ የኢትዮጵያ ጉዳይ ምንም አጀንዳ ባልታያዘበት ሁኔታ በጠላትነት የያዘችን አሜሪካ የኢትዮጵያን ጉዳይ ዛሬም በፀጥታው ምክር ቤት አነሳች::

በተመድ የፀጥታው ም/ቤት የአሜሪካ አምባሳደር እና የሱዛን ራይስ እና የብሊንከን ቡድን አባል የሆነችው ሊንዳ ቶማስ ዛሬም በኢትዮጵያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣልና እርምጃ እንዲወሰድ ክስ አቅርባለች::

<< በትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን እና የኤርትራ ኃይሎች የኢትዮጵያን ወታደራዊ ዩኒፎርም እየለበሱ መሆናቸውን የሚያሳዩ ዘገባዎች እየመጡልኝ ነው ስትል ከሳለች:: የፀጥታው ምክር ቤትም አስቸኳይ ውሳኔ እንዲያሳልፍ >> ጠይቃለች::

ሆኖም ግን የሁልጊዜም አጋራችን የሆኑት ራሽያ ቻይና እና ህንድ የቀረበው ሃሳብ ከአጀንዳ ውጭ መሆኑን በመግለፅ በጉዳዩ ላይ ውሃ ቸለሱበት!!!! ጭራሽ ዛሬ በተያዘው በዋናው የማይናማር ጉዳይም ጭምር ምክር ቤቱ መስማማት ሳይቻል ስብሰባው ተጠናቋል!!!! ክብር ለራሽያ : ቻይና እና ህንድ እንላለን!!!!!

ይህን ተከትሎም የጁንታው አክቲቪስቶች : ተከፋይ ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ከፍተኛ እሮሮ እያሰሙ ይገኛል:: ዛሬም ድንገተኛ የለቅሶ ቀን ሆኖባቸዋል!!!! ቻይና ፣ ሩሲያ እና ህንድ የትግራይን ጉዳይ ማቃለል የለባቸውም እያሉ እያለቃቀሱ ነው፡፡ እባካችሁ በኢትዮጵያ ላይ እርምጃ ውሰዱ: “ትግራይ ካንትዋይት” አይነት የለቅሶ ድምፅ እያሰሙ ነው!!! .የነሱ ለቅሶ እንደተጠበቀ ሆኖ … በአንፃሩ የተባበሩት መንግስታት ምክትል ሃላፊ የሆኑት ወይዘሮ አሚና መሃመድ ለአለቃቸው አንቶኒዬ ጉቴሬዝ እንኳን ተወለዱ ሲሉ “happy birthday” ብለዋቸዋል!!!! እዚያ ማዶ ለቅሶ ነው! ወዲህ ደግሞ ልደት እየተከበረ ነው!!! ይህ ለጠላቶቻችን ሽንጥ ቆራጭ ነው!!!!
.
ታዲያ ይህን የተረዳው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ የሴናተሮች ቡድን (Foreign Senate) በፀጥታው ምክር ቤት እጅግ ያዘነ ይመስላል:: የቡድኑ ፀሃፊ ቦብ ሜንዴዝ ከሰዓታት በፊት በቱዊተር ገፁ ሃዘኑን “በሌላ መልኩ” ገልጿል:: << ለአሜሪካ አዲሱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልማን የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ትግራይን ለቀው እንዲወጡ ማድረግ እንዳለበት አበክሬ ነግሬዋለሁ:: የኤርትራ ለቅቆ መውጣት እና በኢትዮጵያ የተፈጸመውን ግፍ መፍታት የጀፍሪ የጉዞው ተቀዳሚ ማዕከል መሆን አለበት፡፡” በማለት የአሜሪካ የመጨረሻ ተስፋ የፀጥታው ምክር ቤት መሆኑ ቀርቶ በሚመጣው ዲፕሎማት ላይ መሆኑን አሳይቷል:: ለጁንታው ርዝራዦችም ቀቢፀ ተስፋ ለመስጠት ሞክሯል:: አሜሪካ ውርደታም ሃገር!!!!

ፀጥታው ምክር ቤት ዛሬም ፀጥ ብሏል!!!! ወዳጆቻችን ስለ ኢትዮጵያ ተማምለዋል!!!! ከጎንሽ ነን ብለዋል!!!!
ራሽያ ቻይና እና ህንድ ምስጋናችን ይድረሳችሁ!!!! አሜሪካ ግን ዛሬም ጠላትነቷን ባትተውም ፈጣሪ ግን ከአሜሪካ በላይ ነው!!!!! አንፈራም!!!! አንንበረከክም!!!! ቢበዛ ማዕቀብ ነው!!! ጥሬ ቆርጥመንም ስጋችንን በጥርሳችን ነክሰንም ቢሆን እንሻገረዋለን!!!! ውድ ኢትዮጵያውያን ወንድም እህቶቼ እኛ ብቻ የጠላቶቻችንን ሴራ እንረዳ!!!! እንንቃ!!!! አንድ እንሁን!!!! አንድ ከሆንን ፈጣሪ ያግዘናል!!!! ኢትዮጵያ የሚደግፋት አምላክ በሰማይ አለ!!!! ኢትዮጵያ ትሻገራለች!!!!! #Ethiopia

Leave a Reply