NEWS

ምርጫውን ለማደናቀፍ አዲስ ዘመቻ ተጀመረ፤ በመጨረሻ ሰዓት ከምርጫ የሚወጡ ለማዘጋጀት የተሰራ ነው

ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ስፍር ቁጥር የሌለው ጫና የተፈራረቁበት የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ምርጫ እያኮበኮበ ባለበት ወቅት ምርጫውን ባለቀ ሰዓት ጥለው እንዲወጡ እየተወሰወሱ ያሉ ፓርቲዎች መኖራቸው ተሰማ። ፓርቲዎቹ ” የሽግግር መንግስት” የሚጠይቁት ተባባሪዎችና ወኪሎች መሆናቸውም ተጠቁሟል።

የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ለጊዜው ስሙን ያልጠቀሰውን የፖለቲካ ድርጅት አባል ጠቅሶ እንዳለው ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ከሆኑ ኤምባሲዎች ጋር በሚስጢር የሚሰሩ አሉ። ዓላማውም ምርጫው ሲደርስ ምርጫውን ጥለው እንዲወጡና “ምርጫው ያለተፎካካሪ ተካሄደ” በሚል እንዲጠለሽና ዓለም እውቅና እንዲነሳው ለማድረግ ነው።

በኢትዮጵያ ምርጫ እንዳይካሄድ ሲጠየቅ እንደነበር ይታወቃል። አሁን እስር ላይ የሚገኙትን ጨምሮ ሲያራምዱት የነበረው “ከመስከረም 30 በሁዋላ መንግስት የለም” የሚለውን የትግራይ ነጻ አውጪ መፈክር ነበር። ትህነግ በኢትዮጵያ ከትግራይ ክልል ውጪ ህጋዊ እውቅና ያለው መንግስት እንደሌለ ጠቅሶ ለመንግስት መታዘዝና አብሮ መስራት የሚያቆምበትን ጊዜ ቆርጦም ነበር።

በትህነግ በኩል ተከፋይ ከሆኑት መካከል አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት የዓለም አቀፍ ቀውስ ቡድን (አይሲጂ) ዊሊያም ዴቪሰን ጠቅሶ የጀርመን ድምጽ እንግሊዝኛው ክፍል እንዳስነበበው ከሆነ ምርጫው ሊካሄድ የሚችልበት እድል የጠበበ መሆኑን፣ ለዚህም ምክንያቱ ሰፊ በሚባል ደረጃ አገሪቱ መረጋጋት እንደሌላት ነው።

“አዲስ ፓርላማ ለመምረጥ ኢትዮጵያውያን በሰኔ ወር ድምጽ ይሰጣሉ” ያላል የጀርመን ድምጽ ይቀጥልና የምርጫው ምዝገባ አድካሚነት ጠቁሞ “ተቃዋሚዎች ከምርጫው ተፎካካሪነት ራሳቸውን ለማግለል አቅደዋል” ሲል በመግቢያው ላይ ድምዳሜውን ያኖራል።

ገለልተኛ ምሁራንና አገራቸውን የሚወዱ አንዳንድ የተቀናቃኝ ድርጅት አመራሮች አገሪቱ በየስፍራው በውክልና እንድትበጠበጥ የሚደረገው ዊሊያም ዴቪሰንን የመሳሰሉ ተከፋይ ” ሙያተኞች” እንደሚሉት ምርጫው እንዳይከናወን ለማድረግ እንደሆነ ቀድም ሲል ጀምረው በመናገር ላይ ናቸው።

ከዩ ኤስ አይዲ ጋር አዲስ አበባ ከመጡ የውጭ ሚዲያዎች ጋር በረዳትነት አገር ቤት ገብተው የነበሩ ከወራት በፊት ለዝግጅት ክፍላችን የአማራ ብልጽግናን እንደተቆጣጠሩት በጎንዮሽ ውይይት ለጋዜጠኖቹ ሲናገሩ መስማታቸውን አስታውቀውን መዘገባችን ይታወሳል። የመገናኛ ዘዴዎቹ በውቅቱ ፈቃድ ስለተከለከሉና ወደ ትግራይ መሄድ ስላልቻሉ በጎንዮሽ መረጃ ሲሰበስቡ ካገኙዋቸው መካክለ የአብን ሃላፊዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰን ነበር የዘገብነው።

በሰኔ ይደረጋል የተባለውን ምርጫ ዜጎች እንዳይመዘገቡ ሲቀሰቅሱ የነበሩ አሁን ደግሞ ምርጫው መካሄዱና ታዛቢዎች እንደሚገኙ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ በመጨረሻ ሰዓት ምርጫውን ጥሎ ለመውጣት ከራሳቸው አልፎ ሌሎችን እያግባቡ እንደሆነ ተባባሪያችን መረጃ አሰባስቧል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ ተካሂዶ እውቅና የሚሰጠው መንግስት ተቋቁሞ መሰረታዊ የፖሊሲ ለውጥ እንዳያደርግ የተከፈተው ዘመቻ በኢትዮጵያ ህልውና ላይ አደጋ ይዞ እንደሚመጣ በስፋት በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት አካሄዱ ቅሬታና ፍርሃቻ የጫረባቸው እንዳሉ ተባባሪያችን ሰምቷል። መረጃውንም ያካፈሉት እነሱ ናቸው።

የተለያዩ በስም በሚታወቁ ኤምባሲዎች ጋር በመገናኘት የህንኑ ተግባር የሚያካሂዱ እንዳሉ በማወቅ ሕዝብ በአገሩ ጉዳይ ነቅቶ የግል ውሳኔውን ሊወስን እንደሚገባ እነዚሁ ክፍሎች ጠይቀዋል። ይህ መንግስት በግርግር ወድቆ ማን እንደሚመጣ ማሰብ የማይችል ዜጋ አገር አልባ ሊሆን እንደሚችል ጠንቅቆ ማወቅ እንዳለበትም ተመልክቷል።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያ ላይ እየከረረ የመጣው የተቀነባበረና በመናበብ የሚከናወን ሴራ ወደ መጨረሻው ሲቃረብ በአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ህብረት ፈጥረው በሚሰሩ ሚዲያዎችና ስመ አክቲቪስቶች መካከልም አለመግባባት እየተፈጠረ መሆኑንን የአሜሪካ ተባባሪያችን አመልክቷል።

ጉዳይ ስላልበስለ የሚዲያውን ስምና ስመ አክቲቪስቶቹን ለመጥራት ገና መሆኑንን አስታውሶ ተባባሪያችን እንዳለው ለአንድ ሚዲያ ድጎማ የሚያደርጉ ” ነገሩ አላማረኝም፤ ምን እየተሰራ ነው?” በሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ታውቋል። ሌሎችም ተያያዥነት ያላቸው የጎንዮሽ ክርከሮች እየተካሄዱ በመሆኑ ” ከአየር የሚወርዱ ይኖራል” ሲል ተናግሯል።


Categories: NEWS

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s