በአፍሪቃ ቀንድ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሬይ ፌልትማን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት ጫካ ያለውን የትህነግ ቀሪ አመራር በስልክ እንዳገኙ ተሰምቷል። የኢትዮ 12 የአሜሪካ ተባባሪ ለትህነግን የውጭ አመራሮች ቅርብ ከሆኑ እንደሰማው ከሆነ የስልክ ንግግሩ መመሪያ የመስጠት ዓይነት ነው። መመሪያው የኦነግ ሰዎችን እንዳስደነገጠም ተሰምቷል።

“ካሁን በሁዋላ በጦርነት የምንለውጠው ነገር አለ ብላችሁ አታስቡ” ሲሉ እንቅጩን ነግረዋቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፓርላማ ” አየር ላይ የተበተነ ዱቄት” ሲሉ ትህነግ ተመልሶ ሊገጣጠም እንደማይችል እንዳስረዱት ባይሆንም ፌልትማን ” በቃችሁ” ሲሉ የትግራይ ሕዝብ እርዳታና መልሶ ማቋቋም ስራው ላይ እንዲያተኩር ወደ ድርድር እንዲገቡ አዘዋቸዋል።

ትህነግ ከዛሬ ስድስት ወር በፊት ሁሉም ነገር በእጁ በነበረበት ወቅት ለድርድር ሲጠየቅ እንደነበር የሚያስታውሱ ለተባባሪያችን እንደነገሩት ያ የድርድር መንፈስ ዛሬ የለም። ሮኬት፣ ታንክ፣ ዘመናዊ መሳሪያና ሰፊ በጀት የነበረው ትህነግ ዛሬ ስንቅ በአህያ የሚያመላልስ ድርጅት በመሆኑ ድርድሩ ከመንግስት ጋር እንደማይሆን መገለጹ በውጭ አገር ያለውን ሃይል አሳስቦታል።

May be an image of 2 people, beard and text that says 'Dennis Wadley @denniswadley 3d The Ethiopian Patriarch has tried repeatedly to get his message out about the Tigray genocide, but has been censored. He has asked me to release to the the world a 14 minute video today.'

ጫካ ያለው ሃይል ለቀረበለት ሃሳብ የሰጠው ምላሽ ቃለ በቃል ምን እንደሆነ ባይታወቅም፣ ዴኒስ ዋድሌይ የተባለው “Bridges of Hope International” ድርጅት ዳይሬክተር በራሱ ቲውተር ቪድዮውን እንደቀረጸ አስታውቆ ሚዲያዎች የተቀባበሉት ቪዲዮ ላይ የተሰማው የፓትሪያርኩ ጥሪ ይህንኑ ሃሳብ ለማስቀየር ታስቦ የተሰራ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት ስለመኖሩ አስተያየት የሚሰጡ አሉ። በጥሪያቸው ዓለም አቀፍ ጣልቃ ገብነት እንዲደረገ የተባበሩት መንግስታትን ተማጽነዋሎ። የጸጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እንደሚያከብርና የፖለቲካ ልዕናዋን የማይጋፋ እንዲሁም ሙሉ ክብሯን እንደሚጠብቅ አስታውቆ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። ያን መግለጫ በርካቶች ” የጣላቃ ገብነት ጥሪ በማህተም ተዘጋ” ማለት ነው ብለውትም ነበር።

የአሜርካ ተባባሪያችን ስለጉዳዩ ከሚያውቁ የሚዲያ ሰዎችና የትህነግ ወዳጆች እንዳሰባሰበው መረጃ ከሆነ በውጭ ያለው ሃይል መካከል ድርድር ቢጀመር ማን ትህነግን ይወክላል የሚለው ጉዳይ ልዩነት እንዳያስነሳ ስጋት አላቸው። ትህነግ በሌብነት ወንጅሎ ያገለላቸው አቶ ስዬ አብረሃም አሁን በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ግንኙነታቸውን አድሰዋል። ከነ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ በላይ ከትግራይ ተወላጅ የዲያስፖራ አባላት ጋር ስዬ ተወዳጅተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ አገር ያሉ ህጋዊ አካላት የሚገናኙት ወይም ትህነግ የቀጠራቸው የውጭ ዜግነት ያላቸው አካላት የሚገናኙት ከእነ አምባሳደር ብረሃነ ገብረክርስቶስ ጋር መሆኑ የድርድሩን ሂሳብ ማን ያወራርደዋል? ለሚለው ጥያቄ መልስ ማግነት አያስችልም።

አቶ ስዬ

ምንም ሆነ ምን ዛሬ ትህነግ ያለበት ድርጅታዊ አቋም ከመንግስትነት ወርዶ አሸባሪ ሆኗል። ከከፍተኛና ዘመናዊ ትጥቅ ወርዶ ጎሬላ ሆኗል። በቅርቡ እንደተሰማው ከሰፈርበት አካባቢ አህዮች ተሰብስበው ሲወሰዱበት ስንቅና ትጥቅ ማጓጓዣ በማጣቱ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ የተገደደ ሃይል ሆኗል። ይህን የሚያውቁ በማህበራዊ ሚዲያዎች ” አህያ እንኳን መጠቀም ያልቻለ” ሲሉ ድርጅታዊ ህልውናው ማክተሙን እየገለጹ ነው።

” የካቲት 11 መቀለ እንገባለን” በሚል አስተላልፈውት የነበረው መልዕክት ሃቁን ለማይረዳና ትህነግን በቀድሞው ቁመና ለሚያስቡት ሰፊ ጉጉት የፈጠረ ቢሆንም አልሆነም። ተባባሪያችን እንዳለው የአሜሪካ የምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛ ” በቃ” ያሉት የድርጅቱን ቁመና በመረዳት ስለሆነና የትግራይን ህዝብ ችግር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ድርድሩ የማይቀር ነው።

Captured TPLF Junta mastermind Sebhat, eight others arrive in Addis Ababa – Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C
በህግ ጥላ ስር ያሉት አካላት ስብሃት ነጋን ጨምሮ የስምምነት አካል ስለመሆናቸው አልተሰማም

ድርድሩ ምን ሊሆን እንደሚችል ሲያብራራ ” መንግስት አይደራደርም። ትህነግም ከመንግስት ጋር ለመደራደር ዛሬ ላይ ያለው አቋም አይፈቅድለትም” የሚል ሃሳብ መስማቱን ጠቁሟል። አያይዞም ትህነግ ሰራዊቱ እጅ እንዲሰጥ፣ ትጥቅ እንዲፈታ ይስማማል። ከዛም የተረፉ አመራሮች ምህረት ሊያገኙና ወደ ሶስተኛ አገር ሊሄዱ የሚችሉበት ሃሳብ ሊቀርብ እንደሚችል መስማቱን አመልክቷል። መንግስት ስራው ምህረት መሰጠት ብቻ እንደሚሆን አመልክቷል።

የትህነግ ጉዳይ በዚህ ከተቋጨ አብሮት የሚሰራው ኦነግ እጣ ፈንታው ምን ሊሆን ነው? የሚለው ጉዳይ ንዴት እንደፈጠረ ተሰምቷል። ኦነግ የድርድሩ አካል ስለመሆኑ ምንጮቹ ያሉት ነገር የለም። የአሜሪካ መለዕከተኛ የኦነግ ሰዎችን ስለማነጋገራቸው ይህ እስከተዘገበ ድረስ የታወቀ ነገር የለም። ኦነግን ጨምሮ በኦሮሞ ፖለቲካ ዙሪያ የሚሰሩ ከትህነግ ጋር መግጠማቸው በፖለቲካ ቋንቋ በራሳቸው ላይ ሞት እንዳወጁ እንደሚቆጠር በርካቶች መናገራቸው ይታወሳል። • የህውሃት ጦር አዋጊዎች ሚስጢር
  የህውሃት ጦር አዋጊዎች ሚስጢር  77 —-79 አለህ 79-79-97-97 *አለሁ*79 አለህ*አለሁ*ለ99 እነግረዋለሁ ስሙኝ ትላንት የተደረገ መጥፎ ነገር ሁላቹሁም እንድታውቁት ነው::*እሺ ሸለቆው አከባቢ ያሉ ቤቶችን በሙሉ እየበረበሩ ነው::ስለዚህ እየመራን አይደለንም አካሄዳችንም በደምብ አድርገን እንፈትሽ ይሄ አደጋ  ነው በጣም አደገኛ ነው :: በጣም የሚያስገርም ነው ከአንድ ቤት ትላንት ከእግሩ ላይ ጫማውን አስወልቀው የወሰዱ ታጋዮችም ጭምር አሉ ::ትላንት ሙሉ […]
 • ኢትዮጵያ የተናጠል ጣልቃ ገብነትና ጫና ማሳደር የሚፈልጉ አካላትን እንደማትቀበል ደመቀ መኮንን ገለጹ
  ሰብአዊ መብትን ለፖለቲካ መሳሪያነት መጠቀም ተገቢነት የሌለው ብለዋል። 77ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በድርጅቱ ዋና መቀመጫ ኒው ዮርክ በመካሄድ ላይ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ዛሬ ማምሻውን ንግግር አድርገዋል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዓለም በአሁኑ ሰአት እየተፈተነችባቸው ያሉ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ፈተናዎች ምላሽ ለመስጠት በትብብር መስራት እንደሚኖርበት ገልጸዋል። […]
 • “I Have Seen With My Own Eyes Young People Being Killed By The Leaders Of The TPLF Because They Retreated.”
   Ethiopian News Agency ETHIOPIAN NEWS AGENCY – ADDIS ABABA Addis Ababa September 23/2022 /ENA/ The terrorist TPLF started the recent war on Kobo front to exacerbate the sufferings of the people of Tigray who endured miseries by the offensives of the group for two rounds, Fistum Tsegaye, a journalist of the terrorist group TPLF who […]
 • How the RSF got their 4×4 Technicals: The open source intelligence techniques behind our Sudan exposé
  Today we’re publishing another secret document revealing the financial networks behind Sudan’s most powerful militia – the Rapid Support Forces (RSF). An apparently genuine RSF spreadsheet shows how they bought over 1,000 vehicles, including hundreds of Toyota pickup trucks which the militia frequently convert into armed ‘technicals’. We obtained the spreadsheet via satirical Sudanese online […]

Leave a Reply