ጥቃቱ እንደተሰነዘረ ከመቅጽበት ህንጻው ተሽመድምዶ አመድ ሲሆን ይታያል። “ጃላ” የሚባለው ህንጻ በመቆመበት ቦኖ ወደ አመድነት መቀየሩን ተከትሎ የወጡት ዜናዎች ህንጻው የሚዲያዎች መጠቀሚያ መሆኑንን አስታወቁ።

ሕንጻው ወደ አፈርነት ከመቀየሩ ቀደም ብሎ ለባለንብረቱ ስልክ ተደውሎ ነበር። የህንጻው ባለቤት ጃዋድ ሜህዲ ከእስራኤል የደህንነት አለቃ ስልክ ተደውሎላቸው በአንድ ሰዓት ውስጥ ሰዎች ህንጻውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቀዋቸው ነበር። የፈረንሳይ ዜና ወኪል እንዳለው ጃዋድ ለአሶሽየትድ ፕሬስ ዘጋቢዎች በደረሳቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት መልዕክቱን አድርሰው ነበር።

የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ንዑስ ማሰራጫ፣ የአሜሪካ የዜና ወኪል የሆነው አሶሺየትድ ፕሬስ እና ሌሎች ስማቸው ያልተዘረዘር የመገናኛ ዘዴዎች ህንጻው ውስጥ ይሰሩ ነበር። የእስራኤል ጦር ጀት እንድተባለው በአንድ ሰዓት ውስጥ ባለ አስራሶስት ፎቁን ህንጻ በደቂቃ ውስጥ ወደ ብናኝ ቀይራዋለች። የደረሰው የስብአዊና ቁሳዊ ቀውስ ገና በወጉ አልተገለጸም።

Related stories   የመ/ሰራዊትን መለያ ለብሶ ከሱዳን ወደ ወልቃይት ሊገባ የነበረ የትህነግ የሽብር ሃይል ተደመሰሰ፤

የዛሬውን ውሎ አስመልክቶ ዲደብሊው የሚከተለውን አስፍሯል

በእስራኤል እና ፍልስጥኤማውያን መካከል እየተደረገ ያለው ግጭት ዛሬ ቅዳሜም ተጠናክሮ ቀጥሏል። የእስራኤል አየር ኃይል ዛሬ ቅዳሜ በጋዛ ባደረሰው የአየር ጥቃት አብዛኛው ህጻናት የሆኑ በትንሹ አስር ሰዎች ተገድለዋል።

በኢየሩሳሌም የተጀመረው ነውጥም አይሁዳውያን እና አረብ እስራኤሎች ተሰባጥረው ወደሚኖሩባቸው ሌሎች አካባቢዎች ተዛምቷል። በዌስት ባንክ ትናንት አርብ ለተቃውሞ ጎዳና ከወጡ ፍልስጥኤማውያን መካከል አስራ አንዱ በእስራኤል ኃይሎች መገደላቸውን አሶሽየትድ ፕረስ ዘግቧል። ለእስራኤል የአየር ጥቃት በርካታ ሮኬቶች ማስወንጨፉን እና ጉዳት ማድረሱን ሐማስ አስታውቋል።

በሮኬት ጥቃቱ በማዕከላዊ እስራኤል አንድ ሰው መገደሉን ከፖሊስ እና ከሐኪሞች አገኘሁ ያለውን መረጃ ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል። ነገር ግን ስለተወነጨፉ ሮኬቶችም ሆነ ባደረሱት ጉዳት ላይ ከእስራኤል ወገን የተባለ ነገር የለም። ባለፈው ሰኞ በጀመረው ግጭት የእስራኤል ኃይሎች በሰነዘሩት የአየር ጥቃት 39 ሕጻናት እና 22 ሴቶችን ጨምሮ 139 ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት ” ጁንታው” እጅ ሳይገባ ተያዘ

ከእስራኤል ወገን አንድ የ5 ዓመት ህጻንን ጨምሮ 7 ሰዎች ተገድለዋል። ዩናይትድስቴትስ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ወደ ለየለት ጦርነት ከማምራቱ በፊት ያረግቡ ዘንድ ድፕሎማቷን ወደ ስፍራው ልካለች። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤትም በጉዳዩ ላይ ለመምከር ለነገ እሁድ ቀጠሮ ይዟል።


Leave a Reply

Previous post አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት ” ጁንታው” እጅ ሳይገባ ተያዘ
Next post Despite Gaza rockets, Israelis most concerned over internal Jewish-Arab rift
%d bloggers like this: