በተሾሙ ማግስት “ልቅ” አስተያየት መስጠታቸውን አስመልክቶ ኢትዮጵያ አሜሪካ ባሉት አምባሳደሯ አማካይነት የወርፈቻቸው ልዩ መልዕክተኛ አዲስ አበባን እንደረገጡ “ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሶስቱ አገራት ለሚያደርጉት ድርድር አሜሪካ ቁርጠኛ ድጋፏን ትሰጣለች” ማለታቸው፣ ኢትዮጵያ “ ወይ ፍንክች” በሚል የምታራምደውን አቋም ባደባባይ የመደገፍ ያህል በመሆኑ በበጎ ተስዷል።

ሚዲያዎች እንደየፖለቲካ ፍላጎታቸውና እንደ ገበያው እየጎተቱ የሚያትሙትና አየር ላይ የሚያሰራጩት የጄፍሪ ፌልትማን ጉዞ ላይ የተመረከዘ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መግለጫ የተልዕኮው ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ የተከበረና አንድነቷ የማይሻር መሆኑን አመልክቶ፣ በሌላ በኩል በአገሪቱ የሚስተዋለው ጽንፍ የወጣ ብሄርተኛነት ላይ የተቸከለ ፖለቲካ አሳሳቢ እንደሆነ ለኢትዮጵያዊያን ነግሯል። ይህ የጸጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያን ጉዳይ ሲዘጋ ከተናገረው ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ተመዝግቧል። ለጊዜው ምንም አዲስ ሃሳብ የሌለውና አገር ውስጥም ሆነ ከውጭ በተደጋጋሚ ሲባል የከረመ ሃሳብ ሆኖ ተገኝቷል።

አሜሪካ በምስራቅ አፍሪቃ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ የሰየመቻቸው አቶ ጄፍሪ ፌልትማን ዋና ሪፖርታቸው የሚጠብቀ ሆኖ፣ ለጊዜው በመደባቸው መ/ቤት አማካይነት በተሰራጨው መግለጫ በትግራይ ክልል ያለው ግጭት ባፋጣኝ እንዲቆምና “ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙ” የሚሉዋቸው በህግ እንዲጠየቁ ከዓለም አቀፍ አጋሮቻቸው ጋር እንደሚሰሩ ተጠቁሟል። በህግ ይጠየቃሉ ሲል እነማንን፣ ምን አይነት ሰዎች ላይ እርምጃ የውሰዱ? ከመቼ እስከመቼ ለሚለውና በማይካድራ፣ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና በሁሉም አካል ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙትን በጠቅላላው ስለመሆኑ በመግለጫው አልተብራራም።Related stories   “…ለዛሬ ብለን ነገን ከምናበላሽ፣ ለነገ ስንል ዛሬን እንሠዋ” አብይ አህመድPowered by Inline Related Posts

መግለጫው በኢትዮጵያ የሚጠበቀው ዓይነት ለውጥ እንዳይመጣ  አገሪቱ ውስጥ ቀድሞ የተዘረጋው የዘር ፖለቲካ ታላቅ ተግዳሮት እንደሆነበት ቃል በቃል ባይሆንም በጅምላ ተመዝግቧል። ለበለጠ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ቡድኑ ተመልሶ በቅርቡ ወደ ምስራቅ አፍሪካ እንሚመጣ አስታውቆ የተደመድመው መግለጫ አዲስ ወይም ከዚህ ቀደም ያልተባለ ሃሳብ አልታየበትም።


READ ALSO THIS


አገሪቱ የገጠማት ችግር በየአቅጣጫው ሲደመጥ የነበረውን የ”ሁሉን አካታች ብሔራዊ መግባባት ተግዳሮቶቹ ሊፈቱ ይገባል” ሲል ያስታወቀው መግለጫ፣ የተወሰኑ ክፍሎች ራሳቸውን “ትንቢተኛ” አድርገው በመመልከት ለትንተናና ለማህበራዊ ገጾች ማድመቂያ ከማገለገሉ ውጪ እንዴትና እነማን ? ለሚለው ሃሳብ ክፍት ነገር አይታይበትም።

Related stories   “አቡነ ማቲያስ የሰጡት መግለጫ የግላቸው እንጂ የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ አይደለም”

የአገር ውስጥ ሚዲያዎችም ሆኑ ነጮቹ መግለጫው ስለ ምርጫው በትክክል ምን እንዳለ አላሰፈሩም። ግን በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ግን በአፍሪቃ ቀንድ የሚታየውን እርስ በርሱ የተቆራኘ ቀጣናዊ ቀውስ ከግንዛቤ በማሰገባት /address በማድረግ አሜሪካ የበለፀገና የተረጋጋ ቀጣና እንዲኖር፣ የቀጣናው ዜጎችም በመንግሥት አስተዳደር ድምፃቸው (በምርጫ ነው ድምፅህ የሚሰማው) የሚሰማበትና መንግሥታትም ለዜጎቻቸው ተጠያቂ የሚሆኑበት (ተወካይ መንግሥት ወይም representative government እንዲኖር፣ ይህም የሚሆነው በምርጫ ብቻ ነው) ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር አሜሪካ ድጋፏን ትሰጣለች ይላል መግለጫው።

አስተያየት የሰጡን ገለልተኛ የፖለቲካ አዋቂ “በሌላ አነጋገር በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ምርጫውን የመቀበል /endorse አድርገዋል ማለት ይቻላል” ሲሉ መግለጫውን የተረዱበትን አግባብ ገልጸዋል። አያይዘውም ” ፌልትማን ተወካይ መንግሥት በትግራም ሊመሠረት እንደሚገባ፣ ለዚያ ደግሞ ያለው ቀውስ ሊበርድና የኤርትራ ወታደሮች ሊወጡ እንዲሁም ህዝቡ ተወካዩን በመምረጥ ህግና ስርዓት ሊከበር እንደሚችል ሃሳብ ማቅረቡን ያሳያል” ብለዋል። በትግራይ እንዴት ተወካይ መንግስት ይቋቋማል? እነማንስ ይሳተፉበታል? የሚለው ጉዳይ ሰፊ መከራከሪያ የሚስነሳ ሲሆን ” አሸባሪ” የተባለውና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቁልፍ አመራሮቹን ያጣው ትህነግ ጉዳይ እንዴት ይታያል? የሚለው የህግ ጥያቄ ጉዳይ ነገሩን ከወዲሁ አጓጊ ያደርገዋል።


Leave a Reply