ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የማይካድራን ጭፍጨፋ የመጀመሪያ ሪፖርት ካደረገ በሁዋላ የሚከተለው አካሄድ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ ውስጥ እየገባ ነው። ያለ በቂ ምክንያት የማይካድራው ጭፍጨፋ የጥቅል ሪፖርቱ መዘገየት እየነጋገረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት ኮሚሽነሩ ጫፍጫፉን ሲወራ የነበረውንና ኢትዮ 12 በተደጋጋሚ ስታስገነዝብ የነበረውን ጉዳይ ይፋ አውጥተዋል። መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጭፍጨፋ ጉዳይ ዘግይተዋል ይባላሉ።

የሰብአዊ መብት ኮሚሽን “የግፍ ደረጃ መዳቢ” – የማይካድራ ምርመራ ላይ ደባ እየተሰራ መሆኑ ተሰማ፤ ኮሚሽኑ ምላሽ ከለከለ

ኮሚሽነሩ ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጠቅሶ ሪፖርተር ” … በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የሚደረገው ምርመራ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተጠልለው የሚገኙበትን ሱዳን ይጨምራል” ሲል ዘግቧል። ዶክተር ዳንኤል ከኢትዮ ቲዩብ ጋር ባካሄዱት ቃለ መልልስ በተለያዩ አገራት ሩዋንዳና ኮንጎን ጠርተዋል፣ የዘር ማጥፋት ወነጀል የፈጸሙ ወንጀለኞች ከሰላማዊው ስደተኛ ጋር ተቀልቀለው በስደት ወደ ጎረቤት አገሮች እንደሚሄዱ ደጋገመው አስታወቅው ነበር።

በሌላ ዘገባ ደግሞ ” በማይካድራው ጭፍጨፋ የትህንግ አመራሮች ቀጥተኛ ትዕዛዝ ስለመኖሩ መረጃ የለም ” ሲሉ በአርት ቲቪ በአርትስ ወቅታዊ ፕሮግራሙ ላይ ቀርበው ተናግረው ነበር። ቀደም ሲል ወነጀል ሰርቶ ከስደተኞች ጋር ተቀላቅሎ የመኮብለለ ባህሪ መኖሩንና ወንጀለኞች በዚህ መልኩ ራሳቸውን እንደሚሸሽጉ እንዳስረዱት ሁሉ በአርት ቲቪ ቀርበው ሁለት እርስ በርስ የሚጣላ አስተያየት ሰጥተው ነበር።

በውቀቱ የቲቪው ጠያቂ በግልጽ በሚታወቅ ደረጃ የተፈጸመ ወንጀልን ይህን ያህል ማቆየቱ ለመን አስፈለገ የሚል ይዘት ያለው ጥያቄ ነበር የሰነዘረው። እሳቸውን በተደረገው ማጣራት ክልሉን የሚያስተዳድረው አካል የፖሊስ፣ የሚሊሻና ሳምሪ በሚባል አደረጃጀት መፈጸሙን ማረጋገጣቸውን፣ ሪፖርቱም ይህንን አረጋግጦ ማቅረቡን ካስታወሱ በሁዋላ ” ትዕዛዙ በቀጥታ ከትህነግ ስለመውረዱ የሚታወቅ ነገር የለም” የሚል መልስ ነበር የሰጡት። በዚህ ንግግራቸው መሰረት “ሱዳን ተሸሽገዋል” የሚባሉትን ወገኖች በማካተት አዲስ ሪፖርት ሊወጣ እንደታሰበ በጓሮ ሲነገር የነበረውን ጉዳይ እውን እንደሚሆን ፍንጭ ሰጠተው ነበር።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

በመጨረሻ – ኮሚሽነር ዳንኤል እንደ ትህነግና ኦነግ ዓይነት የሽግግር መንግስት ጥያቄ እንዳላቸው አመላከቱ

See also  ኢንጂነር ስለሺ ሹመታቸው ይፋ ሆነ - ዶ/ር ምህረት ተካተዋል

ሪፖርተር በእሁድ ዘገባው እሳቸውኑ አነጋግሮ እንዳሰፈረው በትግራይ ተፈጸመ የተባለውን የሰብአዊ መበት ጥፈቶች ለማጣራት የሚደረገው ምርመራ ሱዳን ድርረስ እንደሚደርስና የምርመራው አካል ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል። በአጭር ጊዜ፣ በሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች የተጨፈጨፉበት፣ በዝግጅትና እቅድ የተከናወነ፣ አጥፊዎቹ የሚታወቁበት፣ በጥፋቱ መተን በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ማይካድራ፣ የተቸፈቸፉት ሰዎች በስም የሚታወቁ፣ በአድራሻ የሚለዩ ሆነው ሳለ እንደዚህ ለመከዳደን መሞከር በሌሎች አካባቢ የተፈጸሙ ወነጀሎችን ሕዝብ እኩል እንዳያወግዝ እንቅፋት እንደሆኑበት በርካቶች እየተቀሱ ነው። ሪፖርተር በዘገባው እንዲህ ያሉትን ጉዳዮች አጥርቶ በዘገባው ባያካትትም ሃላፊውን ጠቅሶ ምርመራው ወደ ሱዳንም እንደሚዘልቅ ማረጋገጫ ሰጥቷል።

መንግስትና የአማራ ክልል መስተዳድር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አክቲቪስት ነን የሚሉ አካሎች በማይካድራ ጉዳይ መፋዘዝ በማሳየታቸው ምን አልባትም የመጀመሪያው ሪፖርት ሊቀለበስ እንደሚችል ስጋት የገባቸው አሉ። በየትኛውም አካባቢ የተፈጸሙ ወንጀሎች እንዲመረመሩ መደረጋቸው አግባብ ሆኖ ሳለ የማይካድራውን ግልጽ ጭፍጨፋ ለማለሳለስ መሞከር ከምን የመነቸ እንደሆነ ለበርካቶች ግልጽ አይድለም። ኮሚሽነሩም ቢሆኑ በየጊዜው እርስ በርሱ የሚቃረን መረጃ መስጠታቸውን ገለልተኛ ወገኖች አልወደዱላቸውም። ዶክተር ዳንኤል ሲኖሩበት የነበረችው ሁለተኛ አገራቸው እንግሊዝ እንዳለቸው ” የሽግግር መንግስት ይቋቋም” የሚል ይዘት ያለው ሪፖርት ማቅረባቸውም አይዘነጋም።

Related stories   የኢትዮዽያ የቁርጥ ቀን ልጅ “ስለአባይ እውነቱን እንካችሁ” – መካ አደም አሊ

የሪፖርተር ዘገባ እንዳለ ሙሉውን ከታች ያንብቡ።

ሰላሳ አባላት ያሉት የምርመራ ቡድን በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ተብሏል

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ጋር በመሆን፣  በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የሚደረገው ምርመራ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተጠልለው የሚገኙበትን ሱዳን ሊጨምር እንደሚችል ተገለጸ፡፡

ሁለቱ ተቋማት በመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም. አጋማሽ ከመንግሥት የሕግ ማስከበር ዘመቻ በኋላ፣ በትግራይ ክልል ተፈጽሟል የተባለውን የመብት ጥሰት በጋራ ለማጣራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከሁለቱም ወገን ከእያንዳንዳቸው ስድስት የመርማሪ አባላትን ያካተተ የባለሙያዎች ቡድን በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ተመረጡ የትግራይ ክልል አካባቢዎች እንደሚያመራ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ ከተደረገ ጀምሮ የመርማሪ ቡድኑ አባላት ለምርመራ የሚያስፈልጉ የቅድመ መረጃ ማሰባሰብ፣ የቦታ ልየታ፣ የምርመራ ሥልቶችን መለየትና የትራንስፖርት ሁኔታዎች ላይ ሲመክሩ መቆየታቸውን ዋና ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

ከ12 የመርማሪ ቡድኑ አባላት በተጨማሪ የሕግ፣ የሥርዓተ ፆታ፣ የደኅንነትና የትርጉም ባለሙያዎችን ጨምሮ የምርመራ ቡድኑ 30 ያህል አባላት ሊኖሩት እንደሚችል ዳንኤል (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ የምርመራውን ነፃነትና ገለልተኝነት ለማረጋገጥ ሲባል የመርማሪ ቡድኑ አባላት የሚሄዱበትን ቦታና አካባቢ ከመጥቀስ ቢቆጠቡም፣ እንዳስፈላጊነቱ ምርመራው በሱዳን የተጠለሉ ኢትዮጵያዊያንንም ሊያካትት እንደሚችል ግን ጠቁመዋል።

ምርመራውን ለማከናወን ሦስት ወራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ ካለው ሁኔታ አኳያ ከእዚያም በላይ ሊጨምር እንደሚችል አስታውቀዋል።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ መሃማት ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በመጋቢት ወር ባደረጉት ውይይት፣  የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በትግራይ ክልል ተፈጽሟል በተባለው የመብት ጥሰት ምርመራ ለመሳተፍ ፍላጎት ማሳየቱ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ ከአፍሪካ ኅብረት በኩል ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዳልቀረበላቸው ዳንኤል (ዶ/ር)  ተናግረዋል፡፡

See also  አማራ ክልል ክተት አወጀ፣ ልዩነት ወደጎን ሲል የቀደሞ ጦር ኣባላትን ጠራ

‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ምርመራው እንዲከናወን በተስማማው መሠረት፣ በምርመራ ወቅት እንቅፋት እንዳይፈጠር ከፌዴራልና ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር መልካም ፈቃድ አግኝተናል፤›› ብለዋል።

በትግራይ ውጊያ ከተቀሰቀሰበት ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ፣ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና ተመድ የትግራይ ክልልን የሰብዓዊ አያያዝ ሁኔታ በቅርበት ሲከታተሉ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ቀደም ሲልም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በማይካድራና በአክሱም ከተማ አካሄድኩት ባለው ገለልተኛ ምርመራ፣ በርካታ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን እንዳረጋገጠ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

በመንግሥት አነሳሽነት ላለፉት ሁለት ወራት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽንና ከፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተውጣጡ አባላት የተቋቋመ የምርመራ ቡድን፣ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አቶ ፈቃዱ ፀጋ ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረው ነበር፡፡ በተለይም በአክሱም ከተማ የተከናወነውን የመጀመርያ ምዕራፍ የምርመራ ውጤት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ይፋ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡

በትግራይ ክልል በአክሱም ከተማ መንግሥት በጥቅምት ወር ከጀመረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ጋር በተገናኘ 99 ሰዎች በኤርትራ ወታደሮች፣ በሕወሓት ኃይሎችና በመከላከያ ሠራዊት ውጊያ ሰበብ መገደላቸውን ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡


Leave a Reply